Thursday, May 12, 2022

ኢሰመኮ በሶማሌ ክልል አኪሾ ጎሳ አባላት ላይ የተፈጸመጥ ጥቃት አወገዘ

 

ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦምባስ ከተማ በአኪሾ ጎሳ አባላት ላይ በክልሉ መንግሥት የፀጥታ አካላት የተወሰደ መጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም ለሞትና የአካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል ሲል ጥቃቱን አውግዟል።

 

የክልሉ መንግሥት ለሟች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ካሳ የከፈለ ቢሆንም ለተሟላ ፍትሕ የወንጀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ሲል አሳስቧል።

 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ጉርሱም ወረዳ ቦምባስ ከተማ መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2014 .. በባሕላዊ ሥነ ሥርዓት የጎሳ መሪ (ሱልጣን) ለመምረጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ግድያ እና የአካል ጉዳት ስለመፈጸሙ በደረሰው ጥቆማ መነሻነት ከሚያዝያ 7 እስከ 12 ቀን 2014 .. በቦታው በመገኘት  ምርመራ አድርጓል።

 

 

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በሁለቱ ቀናት በክልሉ ፀጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶች 11 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣  ይኸውም  በታጠቁ ሰዎች የተፈጸመ ግድያ እና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም ( excessive use of lethal force) የደረሰ የሕይወት መጥፋት መሆኑን፤ በተጨማሪም ቢያንስ 33 ሰዎች  ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ በምክንያታዊ ሁኔታ አሳማኝ (reasonable ground to believe) ሆኖ አግኝቶታል ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ምርመራውን ለማከናወን የአይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን በግል እና በቡድን በማነጋገር፣ ከሆስፒታል ምንጮች መረጃ በማሰባሰብ እንዲሁም ስለጉዳዩ ማብራሪያና ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ የክልሉ ኃላፊዎችን በማነጋገር ምርመራውን ማካሄዱን ገልጿል።

የአካል  ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል በቡሽማን ቀበሌ 7 ተጎጂዎችን በቤታቸው፣ እንዲሁም በጅግጅጋ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት በመታከም ላይ የነበሩ 5 ተጎጂዎችን በማነጋገር እና ምልከታ በማድረግም ማስረጃ ማሰባሰቡን አሳውቋል።

እንደ ኢሰመኮ ከሆነ፤ በተጨማሪም ቦምባስ ከተማ የሚገኝ የጥቃቱ ሰለባዎች የተቀበሩበትን የመቃብር ስፍራ የጎበኘ ሲሆን፣ በዚህም በመጀመሪያ ቀን ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች የተቀበሩበት አንድ የጅምላ መቃብር እና በሁለተኛው ቀን የተገደለች ሴት የተቀበረችበት መሆኑ የተገለጸ ለብቻው ያለ አንድ ሌላ የመቃብር ቦታ ተመልክቷል፡፡

ከክልሉ የመንግሥት አካላት የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤትና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኢሰመኮን  ያነጋገሩ ሲሆን፣ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ የክልሉ የፀጥታ ቢሮ እና የጉርሱም ወረዳ አስተዳደርን ለማግኘት የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም ሲል ገልጿል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር / ዳንኤል በቀለ የክልሉ መንገግሥት በፀጥታ ኃይሎች የተፈጸመው ግድያ ፈጽሞ ተገቢ እንዳልነበር በመገንዘብ ለተጎጂዎችና ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈል ማድረጉ ጥሩ እርምጃ መሆኑን አስታወስው፤ከዚህ በተጨማሪ የተሟላ ፍትሕ ለማረጋገጥና ለወደፊትም ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል የወንጀል ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ይገባል፤ ስለሆነም በአፋጣኝ የወንጀል ምርመራ ሊጀመር ያስፈልጋልብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

Featured post

ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል

                    የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደር...