በሬ
ካላረሰ ባል ካላጎረሰ ወዲያ ፈቶ መልቀቅ ነው
እንዲሁም ፍቅርና ጉርሻ ሲያስጨንቅ የተሰኙ
አባባሎች በኢትዮጵያ የተለመዱ ናቸው። በርግጥ
ከአባባሎቹ በተጨማሪ የቤተሰብ ጉርሻ እበላ
ያደገውን የትየለሌ በመሆኑ ቤት ይቁጠረው።
የጉርሻ ነገር ሲነሳ ግን ትዝ የሚለኝ ልጅ
እያለሁ የማልወደው የምግብ አይነት እንኳን
ቢሆን አባቴ ካጎረሰኝ እንደሚጣፍጠኝ ነው።
ታዲታ
እንደ ወላጅ እና ዘመድ አዝማድ ሳይሆን ልክ
ምግብ ቤት እንደሚባሉት ጉርሻ ቤቶች ተፍተው
በአዲስ አበባ ውስጥ ስራ ከጀመሩ ሰነባብተዋል።
የዛሬ አራት እና አምስት አመታት ወሬው ሲሰማ
ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ተብሎም ነበው።
አንደኛው ጉርሻ ቤት በተዘጋጀለት ጠባብ
መስኮት አማካኝነት የእማማን በጉርሻ ሁለት
ብርዎች ከፍለው ያገኙታል።
በርካታ
ደንበኞች ያሉት ይህ የጉርሻ ምግብ ቤት ሰባተኛ
ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ ሲሆን «ወረፋ
ደርሶን ካገኘነው የምግብ አምሮታችንን ጋብ
ያደርግልናይ» ይሉታል
የቀመሱት ሰዎች።
ከምግብ
ቤቷ አጠገብ ቁጭ በሰሃን የተቀበለውን አንድ
ጉርሻ ሲያጣጥም ያገኘሁት ወጣት «አቡሌ
እባላለሁ» አለኝ
እኔም
ለማወቅ እንደጓጓ ሰው ጠጋ ብዬ እንዴት ነው
የጉርሻው ነገረ አልኩት።
በየቀኑ
የእማማን አንድ ጉርሻ በሁለት ብር ገዝቼ
መክሰስም በለው ቁርስ ብቻ ተመችቶኛል እያለ
በደስታ አወጋኝ። ሁል ጊዜ እዚህ አካባቢ
ብትመጣ ጉርሻ ባለበት ሰዓት አካባቢው በወጣት
አንዳንዴም በአዛውንቶች ሰልፍ ተሞልቶ
ታገኘዋለኝ አለ። ከዚህ ቀደም ከአምስትና
ስድስት አመታት በፊት አንድ ጉርሻ በ25
ሳንቲም እንበላ
ነበረ አሁን ተወደደ ተብሎ ሁለት ብር ገብቷል
ብሎ አከለበት። እናም ሆድን አስጨንቆ ከመብላት
እንዲህ ጎረስ እያደረጉ መሄድ መልካም ነው
የሚል ቀልድ አዘል ሃሳቡን ጣል አድርጎ ወደ
ስራ መግባቴ በቃ ቻው ብሎኝ እብስ አለ።
አንዱ
ወዳጄ ደግሞ እዛው አካባቢ ዞር ዞር ብትል
ሌላም የጉርሻ አይነት ታገኛለህ አለኝ። ምን
አይነት ደግሞ ከዚህ ሌላ የሚል ጥያቄዬን
ያነሳሁበት ወዳጄ ሲመልስልኝ በመስኮቷ
የሚሸጠውን ጉርሻ ምግቡን የሚሰሩት እዚያው
ምግብ ቤቱ ውስጥ ነው። ሌላኛውን የጉርሻ
አይነት ግን ከሆቴሎችና ከዩኒቨርሲቲዎቸ
ተርፎ ከሚመጣ ምግብ ላይ የሚሸጥ ነው አለኝ።
እናም በፌስታል በፌስታል ምግቡ ይቀመጣል
አንድ አንድ ጊዜ መጉረስ ነው ቀጣዩ ተግባር
እያለ አስረዳኝ። የተረፈው ምግብ ከተለያዩ
አይነቶች ተቀላቅሎ የሚመጣ በመሆኑ ከየትኛው
የምግብ አይነት እንደሆነ የተሰራው እርግጠኛ
መሆን ባይቻልም እድል ካለ ግን ስጋ ሊገኝበት
ይችላል ብሎኛል ወዳጄ።
ነገር
በአይን ይገባል ነውና ጉዳዩን ለመመለከት
ወደስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ጎራ ብዬ
ነበር። «በተለምዶ
'ቡሌ'
ይሉታል ወጣቶቹ
ይህ ምግብ እኛ ደግሞ በመሸጥ መተዳደሪያችን
አድርገነዋል» አሉኝ
ከትልቅ ፌስታል ለተመጋቢው በጭልፋ እያወጡ
ምግቡን የሚሸጡት አንድ ባልቴት። እናም
«ጎራሽ
ሞልቷል ግን ደህኗ ጎራሽ የተባሉ ወጣቶች
በመምጣታቸው አሰራሩ እንዲቀየር ምክንያት
ሆኗል» ሲሉ
ገለጹልኝ።
እንዴት?
አልኳቸው
አሰራሩ መቀየሩን እንዲያብራሩልኝ
በፊት
በፊት ጉራሹ በሙላ ገንዘቡን ይከፍልና እራሱ
ነበር ከፌስታሉ ውስጥ የሚያነሳው። አንዳንድ
ወጠምሻ ጎራሾች ግን በአንዴ የሚያነሱት ከፍተኛ
መጠን ያለው ምግብ በመሆኑ ለኪሳራ እየተዳረግን
ተቸግረን ነበር። በመሆኑም አንድ መላ ተዘይዶ
እየተሰራነት ይገኛል። ይኀውም እኛ እራሳችን
ማለትም ሻጮች በእጃችን ልክ ለተመጋቢው አንድ
አንድ ጉርሻ እያነሳን እንሰጣቸዋለን። ከፈለጉ
በሰሃን ይወስዳሉ ከፈለጉ በእጃቸው ተቀብለው
ይጎርሳሉ። ይህ ታዲያ እኛንም ከኪሳራ ተመጋቢውንም
ከአድልኦ አሰራር አርቆናል ማለት ነው።
ቆይ
ምግቡን ገዝታችሁት ነው የምታመጡት?
ማለቴ ለኪሳራ
ተዳረግን ስላሉኝ ነው።
ከየሆቴል
ቤቱ የተረፈውን ምግብ እየገዛሁ ነው በተጨማሪ
ሌሎች ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰሩ ምግቡን
ስለሚያወጡት እነሱ እንኳን በነጻ ነው። ብቻ
አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ
አካባቢ ብትመጣ ምድሩን ሁሉ ጉርሻ ተመጋቢ
ሞልቶት ታገኘዋለህ።
«የምግቡ
ጣዕም ሽታው እርጉዞች ሳይቀር የሚያሰኛቸው
እና የሚያምራቸው ነው አንዳንዴ እኛ ብቻ
ሳንሆን ነፍሰ ጡሮችም መጥተው ይጎርሳሉ»
ሲል የነገረኝ
ደግሞ በዩኒቨርሲቲው አካባቢ ለጉርሻ ተሰልፎ
ያገኘሁት ወጣት ነው። «እኔ
እንኳን እራቴን እዚሁ ሁለት ጉርሻ በልቼ ነው
ወደ ማደሪያዬ የምሄደው በየቀኑ ይህን ስለማደርግ
ደንበኛ አሉኝ። አንዳንድ ጊዜ ከጉርሻው
ካልተመቸን ሰብሰብ ብለን ከጓደኞቼ ጋር
አዋጥተን ምግቡን እንገዛና በህብረት እንመገባለን።
ይህም በሽሚያ እና በጥድፊያ የሚከናወነ በመሆኑ
በርታ ብሎ እጁን ያልሰደደ ከአንድ ጉርሻ በላይ
የማያነሳበት አጋጣሚ ይፈጠራል። ስለዚህ
በህብረት በምንመገብበት ጊዜ በደንብ አድርጌ
ነው ጉርሻዬን የማነሳው»
ሲል የአመጋገቡን
ልምድ ገልጾልኛል።
ህጻን
ልጇን ይዛ ምግቡን ስትገዛ የነበረች እናት
ደግሞ «እኔ
ከልጄ ጋር አረፍ ብዬ መብላት ስለምፈልግ
ለሁለታችንም የሚሆነውን በአምስት ብር እገዛና
መንገድ ዳር ሆኜ እመገበዋለሁ። ጎዳና ላይ
የማድር በመሆኑ ለእኔም ለልጄም የሚቀርብልን
ርካሹን ምግብ ገዝተን እየተመገብን እንኖራለን
ትላለች። ጉርሻ ስፈልግም እዛው በልቼ እሄዳለሁ።
አሁን ምግብ ሻጮቹ እራሳቸው የሰፈሩትን
ስልሚሰጡት እኩል እኩል ይደርሰዋል ሁሉም።
ብላለች። የወጣት ወንዶች የሰልፍ ላይ ግፊያና
ጩኀት ስለሚያስቸግራትም በጊዜ መጥታ ተራ
እንደምትይዝ ነው የነገረችኝ።
ምግቡን
በመሸኝ የምትተዳደረውን ወጣት እዚ አካባቢ
በጣም ፍቅር አለ አንዱ በርከተ አድርጎ የገዛውን
ለሶስት ለአራት ይበላል። በሌላ በኩል እኛም
ለቸገረው አንሰስትም መርቀን ነው የምንሰጠው
ብላኛለች። አንድ ጉርሻ በእኔ ወጪ ተመገብ
ብላ የጋበዘችኝን ወጣት እኔም ላመስግናት
ካላት ላይ ቀንሳ ለሌላው መስጠቱን በተግባር
ላሳየች። መልካም ጊዜ

No comments:
Post a Comment