ድሮ
ድሮ ያኔ መጽሃፍ በጥራዝ መታተም በጀመረበት
አፍላ የዘመናዊነት ጊዜ ነው አሉ። ልጆች
ከዘመናዊ ትምህርት ቤት ይልቅ ከብት ማገድ
እና ወላጅ ማገዝን ብቻ ስራዬ ባደረጉበት ጊዜ።
አንድ ጊዜውን በእርሻ ስራ እና በማህበራዊ
ኑሮ እያሳለፈ ከሰኔ እስተ ሰኔ የቤተሰቡበ
ቀለብ ለመሸፈን ውሎው ከማሳው ላይ ያደረገ
አርሶ አደር ነበር። ቀን ከእርሻው መልስ
ሲያሻው ጫካ ለአደን ሲያሻው ደግሞ የግቢው
እጥር በማጠባበቅ ሲታትር የሚውለው ይህ በስራ
የተወጠረ ሰው ማታም ቤቱ ሲገባ አባወራነቱ
ይመጣል መሰል ሁሌም ኮስታራ ፊቱን ለልጆቹ
እንዳሳየ ነው።
እንዳሁኑ
ቴሌቪዥን ወይም ራዲዮን ያለ የሚዝናናበት
አማራጭ ባለመኖሩ ነው መሰል አብዛኛውን ጊዜ
እስኪተኛ ድረስ ቤቱን በብርሃን በምትሞላው
ኩራዝ ላይ ያፈጣል። አሊያም እርስ በርስ
የሚጨቃጨቁ ሶስት ልጆቹን በቁጣ አደብ እንዲገዙ
ሲነታረክ ወይም ቀን ምን ምን ስራ እንዳከናወኑ
ሲጠይቅ መተኛ ሰዓቱ ይደርስለታል። ነገም
እንደዛው ከነገወዲያም ብቻ ምን አለፋችሁ
የዘመድ ወይም የጎረቤት ሰርግ ከሌለ በስተቀር
ጨዋታ እና ቀልድ ባለፉበት የማለፍ እድል
የለውም።
ሚስቱም
ብትሆን ኮስታራ ፊቱን በመፍራት ይሁን ከአክብሮት
ብቻ ሰው ፊት አብራው ስትጫወት እና ስትስቅ
አትታይም። እንደውም አስፈላጊውን ነገር
ማለትም እጅ ማስታጠቡን፣ ምግብ ማቅረቡን፣
አንዳንድ ለቤቱ አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን
ከማማከር ውጪ አደግድጋ ነው በአንቱታ ጥሪ
ታጅባ ነው የምትቀበለው። እናም ከዕለታት
በአንደኛው ቀን ለአገሩ እንግዳ የሆነ ከተሜ
ኑሮውን ሳይታሰብ በድንገት አኮፋዳውን ብቻ
ይዞ ከተፍ ይላል። አጅሬ ምስኪን አርሶ አደር
ቀን ለስራ የተጠቀመበትን ሞፈር እና ቀምበር
ከነበሬዎቹ እየነዳ ወደ ገቢው ሊገባ ሲል ፊት
ለፊት ይገጣጠማሉ። የአገሩ ደንብ ነው እና
እንግዳውን አንዳንድ ጥያቄ ካነሳሳለት በኋላ
በቤቱ እንዲያድር ግብዣ አቀረበለት። እንግዳውም
በሃሳቡ ተስማምቶ በጎጇቸው ለማደር ተስማማና
ወደ ውስጥ ዘለቁ።
እንግዳው
ጨዋታ አዋቂ የሚባል ሰው ነበርና እናም ቀስ
በቀስ መግባባቱ መላመዱ ሲቀጥል ጨዋታው
የጣማቸው መላው የቤተሰቡ አባላት በደስታ
ተሞልተው ወጋቸውን ያጣጥሙ ጀመር። አርሶ
አደሩም እሰከዛሬ አይቶት የማያውቀውን የልጆቹን
ሳቅ ባየ ጊዜ ይበልጥ የልጆቹ ፍቅር ጨመረበት።
በዚህም ጊዜ ለእንግዳውም አንድ ወግ ሊያጫውተው
ልቡ ሻተና ንግግሩን ቀጠለ።
«ይገርምሃል
ንጉሱ ከአመት በፊት ቀዬውን ሊጎበኙ መጥተው
ከተዋወቁኝ በኋላ አንድ ጥያቄ በባለሟላቸው
አማካኝነት ላኩብኝ። መልዕክቱም 'ከሶስቱ
ልጆችህ መካከል አንዱን ላንተ አስቀርና ሁለቱን
መሃል አገር ወስጄ ላስተምራቸው በቅርቡ
የተከፈተ ጥሩ ትምህርት ቤት አለና እዚያ
እውቀት እየገበዩ ቢያድጉ ለአገር መከታ
ይሆናሉ። ክረምት ክረምትም እየመጡ እንዲጎበኙህ
አደርጋለሁ' የሚል
ነበር። ወዲያው እንደሰማሁ ምን ሃብት አለኝና
ሃብቴም ልጆቼ ናቸው እንቢኝ አሻፈረኝ በሚል
መንፈስ ለባለሟሉ ትንሽ ይደጉ ብዬ ነው እንጂ
ልድራቸው አስቤ ነበር የሚል መልዕክት ላኩላቸው።
አዬ ንጉስ ታዲታ ጉብኝታቸውን ሲጨርሱ አስጠርተውኝ
አሻፈረኝ ማለቴ እርሳቸውን አለማክበር ብቻ
ሳይሆን የልጆቹንም እድል ማበላሸት መሆኑን
ተናግረው። በሃይለ ቃል 'ያንተን
እድል ብታበላሽም የሌሎቹን ልጆች ወስጄ
አስተምራለሁ ምን ይጎልብኛል። ሌላ ጊዜ ስመጣ
ግን ብትከለክለኝ ውርድ ከራሴ'
ብለው ከፊታቸው
እንድጠፋ በቁጣ አንባረቁብኝ»
ይለዋል
ቀጠል
አድርጎም «ስንቱ
ልጁን ለከተማ አስኳሏ ሲያስሞሽር እኔ ሚስቴን
እና ልጆቼን ባለማማከሬ እድል አበላሸሁ።
ይሁንና መች ይመጣሉ እያልኩ በጉጉት ሰጠብቅ
የትምህርት እድሜያቸው አልፎ የዋሸሁለት
ተዳር እንዳይደርስ ፈራሁ»
በማለት
ያጫውተዋል።
እንግዳውም ነገሩን
ካዳመጠ በኋላ የልጆቹ ከተማ መሄድ እንደሚጠቅመው
ያስረዳው ጀመር። ልጆቹን ንጉሱ ለትምህርት
መውሰዳቸው ነው እንጂ ከተማ ቢሄዱ ስራ
እንደሚያገኙ እና ሃብት በሃብት ሆነው ኑሮውን
እንደሚያሻሽሉለትም ይመክረው ጀመር። በተለይም
ትንሹ ልጁ ሲያየው ቀልጣፋ እና ንቁ በመሆኑ
አይኑን አሳርፎበታል።
«በጣም
ስለወደድኩህ እና በመስተንግዶህም ስለተደሰትኩ
አንደ ውለታ ልውልልህ እፈልጋለሁ። ይኸውም
ትንሹ ልጅህን ለማይረባ ጉዳይ ለትምህርት
ሳይሆን ለደህና ቁም ነገር አስቤልሃለሁ።
ያንተን ፍቃደኝነት ላጣራ ብዬ ነው እንጂ ከተማ
ለሱ የሚሆን ብዙ ስራ አለ። በተለይም ብዙ
ገንዘብ የሚያሳፍሱ ቀላል ስራዎች በመኖራቸው
ወደፊት በልጅህ አማካኝነት ዲታ የምትሆንበት
አጋጣሚ አለ። እናም ትንሹን ልጅ ልውሰድና
ሃብታም ላድርገው»
ይለዋል።
ነገሩን
በጥሞና ሲያዳምጥ የነበረው አርሶ አደር «ድሮም
ለልጅ ገንዘብ ሳይሆን እውቀት ነው የሚያስፈልገው
በፊት ተሳስቼ ባስቀራቸው አሁን ልሰጥህ
አልችልም። ስላሰብክልኝ አመሰግናለሁ ግን
ካንተ ሃሳብ ይልቅ የንጉሱ ቁጣ ይሻለኛል»
በማለት አሳፍረው
መለሱት። አጅሬ እንግዳ ለካ ሲጣራ በየቤቱ
እየገባ ህጻናትን ለስራ የሚመለምል ኖሯል።
እናም ሰው እንዴት ልጅ ወልዶ ለሰው ልጅ አያዝን
በሚል አጀብ ተባለ በአገሩ።
No comments:
Post a Comment