የተረሳው ግድብ «አልዌሮ»
የጋምቤላው
አልዌሮ ግድብ እንደሃውልት እያዩ የሚያደንቁት
ብቻ ይመስላል። ሃውልትም
ተጎብኝቶ ገንዘብ ያመጣል የአልዌሮ ግድብ
ነገር ግን ከዚህም የተለየ ነው። ይፈሳል ዛሬም እነደፈሰሰ ነው። ነገም ይነጉዳል፤ ከልካይም
የለው። ግርማ ሞገሱ በዛ ሞቃታማ አካባቢ
ያለውን ሃሩር ያስረሳል። ግና ምን ያደርጋል
ሩብ ምኝተ አመት አለፈ እንኳን ሊሰራበት ቀርቶ
ስሙን እንኳን በአግባቡ መስማት እስከማይቻልበት
ደረጃ ደርሷል። ከጋምቤላ ወላጆች ውጪ የሆኑ የከተማ
ነዋሪዎች ግድቡን ታውቁታላችሁ?
ተብለው ቢጠየቁ
እንኳን ማስታወስ ይከብዳቸዋል። ለነገሩ
በምን ያስታውሱት አሳ በብዛት አYሰገርበት
ወይም እርሻው ተስፋፍቶ አልተሰራበት ደግሞም
ቱሪስት እነዲጎበኘው አልተደረገ።
ጋምቤላውያን
ከልጅ ልጅ ያስተላለፉት አንድ ተረት አላቸው።
ተረቱም በአንድ ወቅት በጋምቤላ ክልል በአንዲት
ቀበሌ ውስጥ ይኖሩ ስለነበሩ የአንድ ቤተሰብ
አባላት ላይ የተመሰረተ ነው። በቤተሰቡ ውስጥ
ያለው ወጣት ስራ የማይሰራ ሲሆን ተፈጥሮ
የለገሰችውን ፍራፍሬ ብቻ እየቆረጠ በመመገብ
መኖርን የመረጠ ነበር። በየወቅቱም በተፈጥሮ
የሚያፈሩ የተለያዩ ምግቦች ቢኖሩም ከዚህም
ላይ የሚያነሳው የምግብ ፍላጎቱን ለማርካት
የሚበቃውን ያህል ብቻ ነበር። መሬቱ ትንሽ
ቆፍረው ቢዘሩበት ትርፍ ምርት እንደሚያስገኝ
ግን ሳይገነዘብ ቀርቶ አልነበረም። አባት
በልጃቸው ስንፍና በማዘን ይበሳጩ ነበር፡፡
አቅማቸው ደክሞ ሞት አፋፍ ላይ በደረሱ ጊዜ
የቅርብ ወዳጃቸውን ያስጠሩና እንዲህ ብለው
ኑዛዜያቸውን ይናገራሉ። ለወዳጃቸውም “እኔ
ስሞት ቀብሬ ከተፈጸመ በኋላ ፍራፍሬዎቹን፣
ከብቶቼን እና እርሻውን አቃጥላቸው። ወንዱ
ልጄ በጣም ሰነፍ ስለሆነ ከሞትኩ የእኔን
ንበረት እነዲወርስ አለሻም»
ይሉታል፡፡
«ከሞትኩ
በኋላ ምንም ሳትፈራ ልጆቼና ሚስቴን አስቀርተህ
ቤቴን፣ ንብረቴንና እንዲሁም ፍራፍሬዎቹን
አቃጥላቸው፡፡ ሁሉንም ነገር አቃጥልና ለሰነፉ
ልጄ ወንድምና እህቶቹን ከእናታቸው ጋር
አስረክበው። በዚህም እራሱንና ቤተሰቡን
ማስተዳደር እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ ይየው»
ብለው ይናዘዛሉ።
መሬቱ ሳይዘሩበት የሚያበቅል ቢሆንም ሲቃጠል
ግን ካልተዘራበት እና ካልታረሰ ምንም ፍሬ
እንማያፈራ ገልፀው ንግግራቸውን ያጠናቅቃሉ።
አባት ከሞቱ በኋላ ልጃቸው ንብረት እንዲወርስና
ሰነፍ ሆኖ እንዲቀጥል አልፈለጉም፡፡ በዚህም
ምክንያት ነበር ኑዛዛያቸውን መራራ ያደረጉት።
እናም
ጓደኛው እንደተባለው አደረገ፡፡ በአካባቢው
ያሉ የተፈጥሮ ፍሬዎች የወደሙበት እና መጠለያ
ያጣውና ኮበሌ የሚላስ የሚቀመስ ባለማግኘቱ
የግድ መስራት እንዳለበት ያምናል። የተለያዩ
ፍራፍሬዎችን ተክሎ በመንከባከብ ከእራሱ
አልፎ ለአካባቢው ሰዎች እየሸጠ ቤተሰቡን
ማስተዳደርም ቀጠለ። ብዙ ምርት ስላመረተና
ሃብትም ስላፈራ የአባቱ አገልጋዮችም በእርሱ
ሥር ሆኑለት፡፡ በዚህም ጠንክሮ የመስራትን
ዋጋና ከበሬታ አገኘ፡፡
ይህ
ታሪክ አልፏል ነገር ግን በክልሉ አሁንም
ጥንካሬን በተግባር የሚያስተምሩ አካላትን
የሚያሻ ክስተት መኖሩ ይስተዋላል። የተፈጥሮ
ሃብት በተንጣለለበት መልካም መሬት ላይ ውሃ
ሌት ተቀን ይገኛል። ከዚህም ለአገር የሚተርፍ
የአሳ ምርት ለገበያ ማቅረብ ይቻላል።
አልዌሮ
ግድብ ከጋምቤላ ከተማ አርባ አራት ኪሎ ሜትር
ርቃ ከምትገኘው አቦቦ ወረዳ አቅራቢያ ይገኛል።
በአካባቢው ለደቂቃ ቆም ብለው ቢመለከቱ ከሰፊው
የውሃ አካል ውስጥ ብቅ እያሉ የሚሰርጉ አሳዎችን
በተደጋጋሚ ይመለከታሉ። ዝም ብሎ ለታዘባቸውም
ሰው በሌለበት ቤት እንደሚርመሰመሱ አይጦች
'ግዛቱ
የእኛ ነው' የሚሉ
ይመስላል። ምክንያቱም አስጋሪዎች ያልተመለከቱት
የአሳዎች ሰፈራ መሆኑን ሁኔታው ይነግረናል።
ግድቡን
በቅርበት የሚያውቁት አቶ ኡሞድ ኡቦያ በአቦቦ
ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ናቸው። እርሳቸው
እንደሚናገሩት፤ አልዌሮ እና ሂሩ
ወንዞች በአንድነት ወደ ግድቡ ይገባሉ።
ግድቡ በደርግ ዘመነ
መንግስት ሲገነባ 10
ሺ ሄክታር
መሬት እንደሚያለማ ታቅዶ ነበር። በተያያዘም
ሰፊ የአሳ ሃብት የሚገኝበት እድል እንዳለው
ይታሰብ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ግድቡ የአሳ
ሃብት ክምችት አለበት። ነገር ግን እስከ አሁን
ድረስ ግድቡ ላይ አሳ የሚያጠምዱት አርባ
የአካባቢው ነዋሪዎች ብቻ ሲሆኑ፤ የሚጠቀሙትም
ኋላ ቀር መሳሪያዎችን ነው። በየቀኑም ሀያ
የሚደርሱ የእንጨት ጀልባዎች በማሰማራት
እስከ አንደ ሺ አሳዎችን ያጠምዳሉ። ይህም
የሚከናወነው በሌሊት ወቅት ነው።
«በየዕለቱ
በአማካይ ስድስት ሺ ኪሎ ግራም የሚመዝን የአሳ
ምርት ይገኛል» የሚሉት
አቶ ኡሞድ፤ ይህም ከግድቡ የአሳ ሃብት እምቅ
አቅም ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛ መጠን
መሆኑን ነው የሚያስረዱት።
ቆሮሶ
የተባለው የአሳ ዝርያ በማህበረሰቡ የተለመደ
ምግብ መሆኑን ይናገራሉ። አጥማጆችም ዋነኛ
ትኩረታቸው በዚሁ ዝርያ ላይ ብቻ ነው። ይሁንና
ጥናት ቢደረግበት በርካታ የአሳ ዝርያዎችን
አቅፎ የያዘ ግድብ መሆኑ አያጠራጥርም።
ምክንያቱም ውሃው ውስጥ የተለያዩ አሳዎች
በአንድነት እና በብዛት ሆነው ሲንቀሳቀሱ
በየጊዜው መመልክት ይቻላል። በመሆኑም በቂ
ጥናት ሊደረግበት እንደሚገባ ይጠቁማሉ።
እንደ
አቶ ኡሞድ ገለፃ፤ በተለይም ክልሉ ዘመናዊ
ጀልባዎችን እና የማጥመጃ ግብአቶችን ለማቅረብ
ያደረገው ጥረት አነስተኛ በመሆኑ አመራረቱ
ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ለሚገፋው ማህበረሰብ
ተገቢውን ጠቀሜታ እያገኘ አይደለም። ግድቡ
ላይ ሳውዲ ስታር የተሰኘው ኩባንያ በመስኖ
ለማልማት የቦይ ካናሎችን ጥገና እያደረገ
መሆኑ አበረታች ነው። እንደ ግብርናው ስራ
ግን ለአሳ ሃብት ልማት ትኩረት ያስፈልገዋል።
በዋነኛነትም ዘመናዊ የሞተር ጀልባዎችን
ተገዝተው ለተደራጁ ወጣቶች ሊተላለፉ ይገባል።
በአሁኑ ወቅትም ወጣቶች በዘርፉ ለመስራት
ፍላጎት እንዳላቸው እየጠቆሙ ይገኛል። ከዚህ
ጋር ተያይዞ ለአስጋሪዎችን የዘመናዊ አመራረት
ስልጠና መስጠት ተገቢ ነው። ይህም ለአገር
የሚተርፍ የአሳ ምርት ለማምረት ያግዛል።

No comments:
Post a Comment