Saturday, June 10, 2017
መቅደላ አምባ የታሪክ ማህደር
መቅደላ አምባ
«መቅደላ
አፋፉ ላይ ጩ ከት በረከተ የሴቱን አናውቅም
ወንድ አንድ ሰው ሞተ»
የተባለላት
መቅደላ አምባ ከአካባቢው ተራሮች በላይ እራሷን
ጎፍራ ተቀምጣለች። የመቅደላ አምባ ዙሪያውን
የሚገኙ ስፍራዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል
መልከአምድር የያዘ በመሆኑ ጦርነት ለመምራት
መቺ እንደሆነ መገመት ይቻላል። የጻውሎስ
ኞኞ አፄ ቴዎድሮስ መጽሃፍ እንደሚያትተው
ከቦታው ጥንታዊ የብራና መጽሃፍት፣ የወርቅና
ብር ዋንጫዎች፣ አክሊሎችና ሌሎች የአፄ
ተዎድሮስ እና ንጉስ ሚካኤል ቅርሶች ከመቅደላው
ጦርነትና ከአፄ ቴዎደሮስ እረፍት በኋላ
በናፒዬር የተመራው የእንግሊዝ ጦር በግመል
አስጭኖ ወደ አገሩ ወስዷቸዋል። በአሁኑ ጊዜም
በእንግሊዝ አገር የተለያዩ መዘክሮች ውስጥ
ተቀምጠው ከሚገኙ ቅርሶች ውጪ መድፎች እና
የቤተመንግስቱ ፍርስራሶች በቦታው ይገኛሉ።
ታሪካዊው
የመቅደላ አምባ ተራራማው በሆነው የአማራ
ክልል ተንታ ወረዳ ውስጥ ይገኛል። ቦታው
ለመድረስም ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ አቅጣጫ
157ኪሎ
ሜትር ርቀት መጓዝ ይጠይቃል። በቦታው እንግሊዞችን
የተዋጉባቸው መድፎች መካከለል አንዱ በቆርቆሮ
በተሸፈነ አጥር ተከልሎ ይገኛል። አጥሩ
ዙሪያውን ሐረግ የወረሰው ሲሆን ጽዳት
እንደሚያስፈልገው ያየው ሁሉ ይመሰክራል።
አምባው ላይ ሲወጡ የአፄ ቴዎደሮስ እራሳቸውን
ያጠፉበት ቦታ ተከለሎ ያገኙታል። በ2000
ዓ.ም
የተገነባው መቃብራቸውም በአካባቢው ታሪክን
ያወሳል። የንጉሱ እቃ ግምጃ ቤትና እንግሊዞች
በርካታ ብራና መጻህፍትን የዘረፉበት የመቅደላ
መድሃኒአለም ቤተክርስቲያንም ፍርስራሹ ብቻ
በቦታው ይገኛል። በአካባቢው እንደ አስጎብኚም
እንደ ጥበቃም ሆነው የታዩት የአካባቢው
ነዋሪዎች ናቸው።
Subscribe to:
Comments (Atom)
Featured post
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደር...
-
ባህል የአንድን ማህበረሰብ የእምነት ፍልስፍና ጥበብ የአስተሳሰብ እሴቶች ያካተተ ነው። ውስብስቡ እሳቤ በቁሳዊ ባህሎቹ እና ልማዶቹ በማህበራዊ ግንኙነቶቹ እና በተለያዩ ትውፊቶቹ አማካኝነት ተጨባጭ አሰራር ይኖረዋል።...
-
ድካም ድካም ያላቸው « ዘመን ተሻጋሪዋ እናት » Abebech Gobena <<Africa's Mother Theresa>> ሴትየዋ ጠንካራ ናቸው። ውልደታቸው በ 1938 ዓ . ...
-
እንኳን ሰው ይቅርና እግር እና እግር ይጋጫል እንደሚሉ አበው በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ህይወት አለመግባባት ሊከሰት ይችላል። ግጭት ካልበረደ ደግሞ አካላዊ፣ስነልቦናዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ብቻ ሳይሆን ክቡር የሆነዉን የሰ...
-
By Getnet Tesfamariam The issue of universal food security is at the heart of many of the ethical issues related to GM technol...
-
ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በ 1917 ዓ . ም ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትን ሲመርቁ እንዲህ ብለው ነበር የሀገሩን ትምህርት ጽህፈት ቋንቋ እንደሚገባው የማያውቅ የውጭውን እማራለሁ የሚል ምሳሌው ቀዛፊ እንደሌለው ታንኳ ነው...
-
Domadol Addicted drug in Ethiopian Schools ሱስ ም እንደፋሽን ተከታዩ በዝቷል :: ትውልድ ም እንደቀልድ ለሙከራ በጀመረው ስህተት አየተጠለፍ በሱስ ሰንሰለት ታስሮ መውጫ ቀዳዳ አጥቶ ...
-
ነቀምቴ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ትገኛለች። እንደ አካባቢው አባቶች የስሟ ትርጓሜ «የታጨች» እንደማለት ነው። በከተማዋ ከሚገኙ መስህቦች ውስጥ ደግሞ ባለ ግርማ ሞገሱ እና ሁለት ነጥብ አምስት...
-
በመኪኖች ጭስ እንደታፈኑ ውለው ከሚያድሩት የአዲስ አበባ ሃውልቶች እና ቅርሶች መካከል የሚመደበው የ አፄ ቴዎድሮስ አደባባይ ዙሪያ ገባውን በላስቲክ ሸራ ተሸፍኗል። አይን የለውም እንጂ አይን ቢኖረውማ እዚህም እዚያ...
-
ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደውን የአስፋልት መንገድ ይዘው ሲጓዙ ፍቼ፣ ደብረ ጉራቻ፣ጎሀ ጽዮን ከተሞችን አልፈው የዓባይን በረሃ ካጠናቀቁ በኋላ የደጀን ከተማን ያገኛሉ፡፡...
-
የኪነጥበብ ስራዎች ልክ እንደ መስታወት በዘመናቸው ያለውን ከሃድ ቁልጭ አድረግው ያሳያሉ ። መስታወቅ ጉድፍንም ውበትንም በግልጽ ፊት ለፊት እነደሚያቀርብልን የሥነጽሁፍ ስራዎችም እነዲሁ ናቸው። እ ን ደ ሐዲስ አለ...



