እንደ
መሪጌታ ልሳነወርቅ ከሆነ "የኖኅ
ልጆች የሆኑትን ሴም፣ ካምና ያፌት ኣብረን
እያለን ሳንበታተን ስማችን የምናስጠራበትን
እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንገንባ ብለው
በምድረ ሰናኦር ያገኙትን ሰፊ ቦታ ጡብ በእሳት
እየጠበሱ ጡብም ድንግያ ስለ ሆነላቸው ዓስር
ክንድ ቁመት፣ ሶስት ክንድ ወርድና ሶስት ክንድ
ጎድንን ያለው ጡብ ሲሰሩ ነበር፡፡ እግዚኣብሔርም
የልቦናቸው መጥፎ ክፋት ተገንዝቦ እያንዳንዳቸው
እንዳይስማሙ ቋንቋቸው በታተነባቸው"
የሚል
የመጽሃፍ ቅዱስ ታሪክ ማስረጃ አለ። የግእዝ
ቋንቋ የባቢሎን ግምብ/ጥቅመ
ሰናኦር/ ሲፈርስ
ከነበሩት 72
ቋንቋዎች
አንዱ ነው፡፡ ከዚያም በየመን እና ቀይ ባህር
አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። ቋንቋ ይወለዳል
ያድጋል ይሞታል እንደሚባለው ግዕዙም በኢትዮጵያ
እያደገ ከአራት ሺ አመታት በፊት ጥቅም ላይ
ቢውልም አሁን ላይ ቋንቋውም ሆነ ቁጥሮቹ
በአዲሱ ትውልድ የማይታወቁበት ደረጃ ላይ
ደርሰዋል።
የታሪክ
መምህሩ አቶ ደርብ አለሙ እንደሚሉት፤ አሁን
ላይ የግዕዝ ቁጥሮች በዕለት ተዕለት የህይወት
ክዋኔው ውስጥ የሚጠቀም ሰው አለ ለማለት
ይከብዳል። አብዛኞቹ የዓለም አገራት ታሪካቸውን
በጥልቀት ተረድተው ለመሰነድ ከቃላዊ ትውፊት
ለመፃፍ በሚቸገሩበት ጊዜ ኢትዮጵያ ግን ከአራት
ዘመናትን ያስቆጠረውን ጽሑፋዊ መረጃ ባለቤት
ሁና ቆይታለች፡፡ ዘመናት ተሻግረው እኛጋር
የደረሱትን የግእዝ ቁጥሮች ምን ያህል አጥንተን
ጥቅም ላይ አውለናቸዋል የሚለው ደግሞ ሌላ
ጥያቄ የሚያጭር ጉዳይ ነው። ነገር ግን እነዚህ
ቁጥሮች የአሁኑ ትውልድ የሚሰጡትን ጠቀሜታዎች
ባለመገንዘብ የራሱን እየተወ የሌላውን ቁጥር
ሲገለገል ይታያል፡፡ ድሮ የተማሩትና የቤተ
ክህነት እውቀት ያላቸው ሰዎች ካልሆኑት
በስተቀር የግእዝ ቁጥሮች አገልግሎት እምብዛም
ነው፡፡ በተለይም የአሁኑ ትውልድ ከግእዝ
ቁጥሮች ተጠቅሞ ሒሳብ ማስላት እና መጠቀም
ባለመቻሉ ከቁጥሮቹ ጋር ሆድና ጀርቧ ሆኗል።
በወልቂጤ
ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው አራተኛው አመታዊ
የግዕዝ ጉባኤ ላይ ዲያቆን ካሕሳይ አብርሃ
ያቀረቡት ጥናት ደግሞ ቁጥሮቹን እንዴት ለሒሳብ
ደህንነት ማዋል እንደሚቻል ያሳየ ነበር።
እንደ እርሳቸው፤ የአገሮችን ዕድገት እየጨመረ
በሚሄድበት በትሪልዮን፣ ኳትሪልዮን የሚጀምር
የብድርና የገንዘብ ዝውውር አለ። በተጻፈው
የገንዘብ መጠን ልክ ደግሞ ከቁጥሮቹ በፊትና
ኋላ ተጨማሪ ቁጥር በመጻፍ ለምዝበራ በር ከፋች
በመሆኑ እያንዳንዱ የገንዘብ መጠን በአሃዝና
በፊደል እንዲጻፍ አስገድዷል፡፡ በአሃዝና
በፊደል ለመጻፍ የሚፈጀውን ጊዜ፣ ኃይልና
ቦታ ደግሞ ትልቅ ነው፡፡ ነገር ግን የግእዝ
ቁጥሮች ይህን ችግር የሚቀርፉ የቀደምት አበው
ፍልስፍና ጥግ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ዓለም
እየተራቀቀች በምትሄድበት ጊዜ በሌሎች ሰዎችን
ላብ መኖር የለመዱትን ኣካላት ለስርቆት
እየተራቀቁ በሚሄዱበት ጊዜ ለገንዘብ ዋስትና
ሲባል አንድ ነገር ተፈለሰፈ፡፡ እሱም ከገንዘብ
ጋር ንክኪ ያለቸው ነገሮች በአሃዝና በፊደል
ካልተጻፈ ሕጋውነዊት የሌለው መሆኑ የሚገልጽ
ነው፡፡ ስለ ሆነም የገንዘብ መጠን በአሃዝና
በፊደል ካልተጻፈ የሚያስተናግድ የፋይናንስ
ተቋም እንደሌለ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ የሆነበት
ዋናው ምክንያት በተጻፉት ቁጥሮች በፊት ይሁን
በኋላ ቁጥር ከመጨመር አልፎ ለተጻፉትን
እያንዳንዱ ቁጥሮች በመቀየርም የማጭበርበር
ስራ ስለ ሚሰራበት ነው፡፡ ለምሳሌ በቼኩ
የተጻፈውን የገንዘብ መጠን 3000
ብር ከሆነ
የግድ በፊደል ሶስት ሺህ ብር ተብሎ መጻፍ
ኣለበት፡፡
የገንዘብ
ነክ ጉዳዮች በዓረብ ቁጥሮች ያለው አደጋና
በግእዝ ቁጥሮች ያለው ደኅንነት በንጽጽር
ለማሳየት እላይ "ሶስት
ሺህ ብር"
የሚለውን
የገንዘብ መጠን ለአብነት መመልከት ይቻላል፡፡
ይህ የገንዘብ መጠን በግእዝ ቁጥሮች ሲጻፍ
፴፻ ሲሆን በዓረብ ደግሞ 3000
ብር ተብሎ
ይጻፋል። ነገር ግን በዓረብ ቁጥር3
የነበረው
ወደ ሊቀየር ይችላል፡፡ በተለይም 0
የነበረው
ወደ 6፣
8 እና
9 በቀላሉ
ተቀይሮ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አልፎ ተርፎም ብዙ
ዜሮዎች እየተጨመሩበት ሲሄዱ መጠኑ እያደገ
ስከሚሄድ የማጭበርበሪያ መንገዱ ከግዕዙ
ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ያደገ ነው።
በአረቡ
የተጻፈውን 3000
ቁጥርን
ወደ 8999 ለመቀየር
ይቻላል። ነገርግን ሶስት ሺ በግእዝ ሲጻፍ
፴፻ ነው የሚሆነው፡፡ ከግእዝ ቁጥሩ ላይ ቅጥያ
ቢጨመርም ሌላ ቁጥር የመምሰል እድሉ ስለማይኖረው
የማጭበርበር ስራው ወዲያውኑ ይጋለጣል።
በተመሳሳይ በዓረብ ቁጥር 4000
የነበረውን
ዜሮ በመጨመር ወደ 40‚000
ሊያድግ
ይችላል፡፡ በግእዝ ቁጥሮች ግን ዜሮ የሚጨመር
የለም። እንዲሁም 3000
/፴፻/
የነበረውን
የገንዘብ መጠን 3001
/፴፻፩/
ተደርጎ
ከተጻፈ ከፊትም ይሁን ከኋላ ማንኛውንም ቁጥር
ለመጨመር አይቻልም፡፡ የግእዝ ቁጥሮች ወደ
ማንም በፈለገው መልኩ የማይቀየሩ ከመሆናቸው
በተጨማሪ በቁጥሮቹ ፊት ይሁን ኋላ ሌላ ቁጥር
የማይጨመርላቸው በዓለማችን ልዩ ከሆኑት
ቁጥሮች ስለሚመደብ ለአጭበርባሪዎቸ የተመቻቸ
አይደለም።
ሌላው
የግዕዝ ቋንቋ ከአረቡ ጋር ሲነጻጻር በቁጥር
አነስተኛ ናቸው። በዓረብ ቁጥሮች በስድስት
አሃዝ የተፃፈ በግእዝ በሶስት አሃዝ ነው
የሚገለጸው፡፡ በሌላ በኩል3000
የነበረውን
የገንዘብ መጠን ከፊቱ 4
ቁጥር
ከጨመርንለት 43000
ይሆናል፡፡
ይህ ቁጥር በግእዝ ሲጻፍ ግን ፴፻ የነበረውም
ወደ ፬፼፴፻ ስለ ሚቀየር ለማጭበርበር እድል
አይሰጥም፡፡ ይህ በመሆኑ በዓረብ ቁጥሮች
የሚጻፉ በመላው ዓለም የሚገኙትን የፋይናንስ
ተቋሞች በገንዘብ ይሁን በሰነዶች ላይ በህትመት
ይሁን በእጅ ጽሑፍ ሲዘጋጁ ለከፍተኛ የማጭበርበር
ኣደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡
ይህ
በመሆኑ የፋይናንስ ተቋሞች ከአደጋ ለማምለጥ
ሲሉ የገንዘቡ መጠኑን በአሃዝና በቁጥር ለማጻፍ
ተገደዋል። የግእዝን ቁጥሮች ግን ከዚህ አይነቱ
የፋይናንስ አደጋ ለማምለጥ አመቺ ሆነው
የተዘጋጁ ናቸው። የግእዝ ቁጥሮች ወደ ተፈለገው
ቁጥር መለወጥ የማይቻል በመሆናቸው በተለይ
የገንዘብ ነክ ጉዳይ ሲያጋጥም በአሃዝና በፊደል
ለመጻፍ ከሚባክን ጊዜና ጉልበት እንዲሁም
ከመጭበርበር ይታደጋሉ። ምክንያቱም በዓለም
ደረጃ የሚታዩትን ዘራፊዎች ምንም ቢሆን ቢራቀቁ
በግእዝ ቁጥሮች ግን ሊያጭበረቡሩበት የሚችሉበት
እድል ጠባብ ይሆናል። በመሆኑ የግዕዝ ቁጥር
ከኢትዮጵያም አልፎ ለሌላም ዓለም የሚተርፍ
ልዩ ሃብት ነው፡፡
የግእዝን
ቁጥሮች በገንዘብ ደኅንነት ያላቸውን የላቀ
ድርሻ ከግምት በማስገባት ለነዚህ ችግሮች
የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ በጥቅም ላይ
ለመዋል የሚያዳግት ጉዳይ አለመሆኑን አጥኚው
ያስረዳሉ። እንደ እረሳቸው፣ የግእዝ ቁጥሮች
በገንዘብ ደህንነት ያላቸውን ፋይዳ ከግምት
በማስገባት በበለጠ ልንጠቀምባቸው ያስፈልጋል።
የአስተሳሰብ ለውጥ ካለ የወላጆቻችን የግዕዙ
ቁጥር ከቻይናውያን ፊደሎች በላይ አስቸጋሪ
አለመሆኑንና በቁጥሮቻችን ለመጠቀም እንችላለን።
የግዕዝ ቁጥሮች እስከሚለመዱ ድረስ አሁን
በአሃዝና በፊደል እንደሚጻፈው ጎን ለጎን
በዓረብና በግእዝ አሃዞች እየጻፉ መለማመድ
ይገባል።
እንደ
ዲያቆን ካሕሳይ አብርሃ ከሆነ፣ በአሁን ጊዜ
ከቦንድ ሽያጭ ጀምሮ የተለያዩ ተቋማት ምርቶቻቸውን
የሚያስተዋውቁበት የዘመን ኣቆጣጠር /ካላንደር/
አዘጋጅተው
የኢትዮጵያን ኣቆጣጠር በግእዝ የፈረንጆቹን
ደግሞ በዓረብ ቁጥሮች እየጻፉ የሚያቀርቡበት
መንገድ ቁጥሮቹ እንዲለመዱ አስተዋጽኦው
ቀላል አይደለም። እንደ አገር የእራሳችን
ቁጥር እያለን በሌሎች አገራት ቁጥሮች መጠቀሙ
ለራስ ዋጋ አለመስጠት ነውና ለጥንት አባቶቻችን
ምርምር ክብር እንዲኖረን የግዕዝ ቁጥሮችን
በስፋት መጠቀም ያስፈልጋል። በዋናነት ደግሞ
የማንነታችን አሻራ የያዘውን የግእዝ ቁጥሮች
በገንዘብ ነክ ጉዳዮችን ያለው ሁነኛ መፍትሔ
ኅብረተሰቡን ተገንዝቦ እንዲጠቀምባቸው ህግ
ማበጀት ያስፈልጋል፡፡
No comments:
Post a Comment