Domadol Addicted drug in Ethiopian Schools
ሱስም
እንደፋሽን ተከታዩ በዝቷል::
ትውልድም
እንደቀልድ ለሙከራ በጀመረው ስህተት አየተጠለፍ
በሱስ ሰንሰለት ታስሮ መውጫ ቀዳዳ አጥቶ
ይማስናል::
ከሲኤምሲ
ወደ አያት እየተጓዘኩ ሳለሁ
ከፊት
ለፊቴ ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ከመግባታቸው
በፊት መድሃኒታቸውን መግዛት እንዳለባቸው
እያወሩ
ነው::
አንዷ
ተማሪ
50
ብር
ከቦርሳዋ
አውጥታ
ፊት ለፊቷ ከሚገኘው መድሃኒት መደብር ገባች።
ከገዛችው
መድኃኒት ውስጥ
ለሶስቱም
ጓደኞቿ አንድ አንድ አነስተኛ
ካርቶን አከፋፈለቻቸው::
ሶስቱም
ተማሪዎች
በአንድነት ከካርቶኑ ያወጡትን አምፒሲሊን
መሰል መድሃኒት የቻሉትን ያህን አራትም
አምስትም ፍሬ ከማሸጊያው ላይ እየፈለቀቁ
ወደአፋቸው ላኩት::
ከዚያ
በኋላ ራሳቸውን
መቆጣጠር እስኪሳናቸው ድረስ ተንገዳገዱ::
ሌሎች
አልፎ ሂያጅ ተማሪዎች ግን እነርሱን እያዩ
ይሳሳቃሉ::
መድሃኒቱን
ለማወቅ ያለኝ ፈላጎት ጨመረ::
ወደመድሃኒት
ቤቱ ሄጄ ሳጣራ ግን የህመም ማስታገሻ መድሃኒት
ቢሆንም የማነቃቃት ባህሪ ያለውና ሱስ የሚያስይዝ
እንክብል መሆኑንና
ተማሪዎች በብዛት አንደሚጠቀሙት ተረዳሁ::
ከመድኃኒት
ወሳጆቹ መካከል ሐያት
/ስሟ
የተቀየረ/
ትገኝበታለች::
አዲስ
አበባ ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኘው ዲቦራህ
ትምህርት
ቤት የአስረኛ ክፍል ተማሪ ናት::
ዕድሜዋ
በግምት
17
ሰባት
ይሆናል::
በየቀኑ
አዕምሮዋ አምጪ አምጪ የሚላትን መድሃኒት
ካልወሰደች ድብርትና ድካም ይጫጫናታል፤
አዕምሮዋ ይረበሻል::
ምክንያቱም
መድሃኒቱን በተደጋጋሚ በመውሰዷ ልክ እንደ
ጫት እና ሲጋራ እሱን ካላገኘች እረፍት
አይሰጣትም::
ቤተሰቦቿ
ስለ ጉዳዩ ስለማያውቁ ሁሌም ደህና እንደሆነች
ነው የሚያስቡት::
እሷም
ችግሯን ለመናገር አልደፈረችም።
ከመድኃኒቱጋር
የተዋወቁት የዛሬ አራት ወር ገደማ እንደሆነ
ትናገራለች። የትምህርት ቤት ጓደኛዋ ዶናዶል
የሚባል መድሃኒት እንዳለ
እና እንደሚያነቃቃ ከሰማች በኋላ ለመሞከር
ትወስናለች::
ወዲያውም
መድሃኒቱን ገዝተው ጥቁር
እና ቀይ ቀለማት የያዘውን እንክብል አምስት
አምስቱን
በአንድ ጊዜ ይውጡታል::
ሁለቱም
ተዝለፍልፈው መውደቃቸውን ታስታውሳለች::
በትምህርት
ቤቱ አካባቢ የነበሩ ወጣቶች በእጃቸው ላይ
የነበረውን መድሃኒት ቀድሞም ስለሚያውቁት
ደጋግፈው አንድ ጥግ ያሳርፏቸውና ምንም
እንዳልተፈጠረ
የመጀመሪያችሁ ስለሆነ ነው አይዟችሁ በሚል
አበረታተዋቸው ይሄዳሉ::
በዚህ
የተጀመረው ሱስ አሁን ላይ በየቀኑ ሶስት እና
አራት የትራማዶል/ዶናዶል/
እንክብሎችን
እስከማስዋጥ እንዳደረሳት ትናገራለች::
በየቀኑም
ከደብተር
ቦርሳዋ ውስጥ
በምትይዘው
ትራማዶል
የተሰኘውን
መድሃኒት
በትምህርት
ቤት ምሳ ሰዓት ላይ ሶስት
እንክብሎችን በአንዴ እንደምትውጥ
ትናገራለች::
ማታም
እንዲሁ
ከቤተሰቦቸ ተደብቃ ትደግመዋለች::
ይህ
በየቀኑ የሚደረግ ልምድ ወደሱስነት እንደተቀየረ
ብትረዳም ለመተው ተቸግራለች::
በየቀኑ
ኬኒኑን
መውሰድ
ሱስ ቢሆንባትም
እስከ
መቼ እንደዚህ ሆና እንደምትቀጥል
ግን
ለእራሷም
ግራ ገብቷታል::
አሁን
አሁን
ሱስ አስያዡን ካሻው
መድሃኒት መደብር ሸምቶ በየቀኑ የሚቅመው
ተማሪ
ተበራክቷል::
እኔ
ብቻ አይደለሁም አብዛኛው ተማሪዎች ይወስዱታል
በማለት ችግሩ የእርሷ ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው
የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች እንደሆነ አስተውላላች::
በዚሁ
መድሃኒት ባለፈው ወር ብቻ በአንድ ጊዜ አስር
ተማሪዎች እራሳቸውን ስተው መውደቃቸውንም
ትናገራለች::
መድሃኒቱ
በ10
እና
15
ብር
በየፋርማሲው ያለማዘዣ
የሚገኝ
በመሆኑ የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ሳይቀሩ
እይተጠቀሙት በመሆኑ አንድ መፍትሄ እንዲፈለግለት
ትማፀናለች::
እኔም
የሻጮቹ
ጉዳይ እውነት መሆኑን ለማጣራት በአካባቢው
ከሚገኘው ሊዲያ
ወርቅነህ ወደ ተሰኘው
መድሃኒት
መደብር አመራሁ::
ያለምንም
የሐኪም ማስረጃ ይህንን ሱስ አስያዥ
መድሃኒት በ15
ብር
ከዝቼ ደረሰኝ ተቀበልኩ::
ከገዛሁ
በኋላ ግን ፋርማሲስቷን እንዴት
ያለ ማለዣት
ሸጭልኛለሽ
ብላት መልሷ
አንገት
ማቀርቀር ብቻ ሆነ::
ጥፋት
እንደሆነ ብታውቀውም ገንዘብ ነውና
በየቀኑ
ለጠየቃት
ሁሉ ትቸበችበዋለች::
ነገሩ
ቢከነክነኝ ጉዳዩን
ይዤ
ወደ ተቆጣጣሪው ባለስልጣን አመራሁ::
ትራማዶል
ወይም
በአምራች ስሙ ዶናዶል
የተባለው የመድሃኒት አይነት ሰውነት ውስጥ
ከገባ በኋላ
ወደ ሞርፊንነት የሚቀየር መድሃኒት
መሆኑን የገለጹልኝ
ደግሞ የአዲስ
አበባ የምግብ፣
የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን
ፋርማሲስት
አቶ
ይመር
ሁሴን ናቸው::
እንደ
እርሳቸው ገለፃ መድሃኒቱ ያለ የሐኪም
ማስረጃ መሸጥ
የሌለበት ቢሆንም በየመድሃኒት መደብሩ በግላጭ
እንደሚቸበቸብ ይገልጻሉ::
መድሃኒቱ
ሱስ ከማስያዙ በላይ ተማሪዎቹ ላይ የጉበት
እና አደገኛ የመተንፈሻ አካላት በሽታ የማስከተል
አቅም እንዳለው የሚናገሩት አቶ ይመር፤
መሸጥ
ካለበትም
በሐኪም የታዘዘለት ታካሚ ብቻ ነው::
ነገር
ግን ትክክለኛ አሰራር ተከትለው የሚሸጡ
መደብሮች ቁጥራቸው አነስተኛ
በመሆኑ በየቦታው እየተቸበቸበ ይገኛል::
ከሚታሰበው
በላይ በርካታ ተማሪዎች እየወሰዱት ያለ
መድሃኒትም ሆኗል::
መስሪያ
ቤታቸው ተከታትሎ እርምጃ ለመውሰድ ያለው
አቅም እና ክትትል ደካማ በመሆኑ በርካታ
መድሃኒቶች ያለማዘዣ
በመሸጥ ላይ መሆኑን ታዝበዋል::
በመሆኑም
መድሃኒት መደብሮች ያለሐኪም ማስረጃ
የትኛውንም
አይነት መድሃኒት እንዳይሸጡ
ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚያስፈልግ
አቶ ይመር ያሳስባሉ::
የአዲስ
አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ስለጉዳዩ ምንነት
እና ስለሱስ አስያዡ መድሃኒት እና ስለተማሪዎች
ግንኙነት ባለማቀወቃቸው መልስ ለመስጠትም
አልተቻላቸውም::
የስነ
አዕምሮ
ህክምና ስፔሺያሊስት
/ሳይኮሎጂስቷ/
አስመረት
ወልደብርሃን
(ዶ/ር)
እንደሚሉት፤
መድሃኒቱ
ኦፖይድ የሚባል ሶስ አምጪ ንጥረ ነገር አለው።
መድሃኒቱ የካንሰር ክመም፣ የመገጣጠሚያ
በሽታ፣ ከቀዶ ጥገና በኋላ እና ለሌሎችም ህመም
ሲያጋጥም ስቃይን ለመቀነስ ይረዳል። በአግባቡ
ለህክምና ጥቅም ሲውል በአግባቡ ይሰራል።
ነገር ግን ተማሪዎች
በዘፈቀደ
ሲወስዱት
አካላዊ እና ሰነልቦናዊ
ጉዳት የማስከተል
አቅም አለው። በመድሃኒቱ
ምክንያት ሱስ ውስጥ የገቡ ወጣቶችም ልክ
እነደማን'ውን
የሱስ አየነት አስፈላጊው የስነአዕምሮ ህክምና
ያስፈልጋቸዋል። ከሱሱ
መላቀቅ
ከፈለጉም የስነልቦና ሃኪሞች ጋር ቀርበው
ተከታታይ
ህክምና
ማድረግ ይገባቸዋል። መድሃኒቱን
በማቋርጥበት ወቅት ምን ችግር ይደርስብኛል
ብለው ለሚሰጉም በሚሰጠው ህክምና አማካኝነት
ከችግሩ
የሚያላቅቁ አጋበጊዜያቶች
ሂደት ከሱሱ ለመላቀቅ
የሚያግዙ
መድሃኒቶችንም ያገኛሉ። ለአብነት ዶናዶልን
ሲያቋርጡ እንቅልፈ እጦት ካጋጠማቸው በምትኩ
የእንቅልፍ መድሃኒት፤ ድብርት ካጋጠማቸው
ደግሞ ዘና የሚያደርጉ ጤነኛ መንገዶችን
ለአማራጭነት ከሃኪሞች ማግኘት ይችላሉ።
በመሆኑም የሱስ ተመራጭ የለውምና ተማሪዎቹ
ላይ የሚታየውን ችግር ተረባርቦ መቅረፍ
ለአገርም ይበጃል።

No comments:
Post a Comment