ከአዲስ
አበባ ምስራቅ
አቅጣጫ
500
ኪሎ
ሜትሮችን ቢጓዙ
የእራሳቸው
ቀለማት ያላቸውን የሐረሪዎችን
ከተሞች ያገኟቸዋል።
የሐረሪ
ክልል መዲና ሐረር
በአብዛኛው
በስነህንፃ
ውበቶቿ
በተለይም በጀጎል
ግንብ ታዋቂ
ብትሆንም የክልሉ
ባህላዊ አልባሳቶች፣
መገልገያ
ዕቃዎች
እና በቤቶች ውስጥ ያረፉትን የዕደ ጥበብ
ውጤቶች ደግሞ ከአዕምሮ ሊጠፋ የማይችል ትዝታን
የየመፍጠር አቅም አላቸው።
ሐረሪዎች
ጥንታዊ የዕደጥበብን ከቤተሰብ እየተቀባበሉ
ያደጉ ናቸው::
የሐረሪ
የዕደ ጥበብ ውጤቶች ለቤት ማስጌጫነት እና
ለውበት ማድመቂያነት ይውላሉ::
በተለይ
ስፌት ሙያ የሌላት ሴት ቤቷን ለማስጌጥ እና
ባህሏን ለማከበር ያላት እድል ዝቅታ በመሆኑ
ከዘመድ አዝማድም ሆነ ከጎረቤት ሙያውን
ለመልመድ ከፍተኛ
ጥረት ታደርጋለች::
የእደጥበብ
ውጤቶች በተለይም የስፌት እና የማስዋቢያ
እቃዎች በአንድ አካባቢ ውስጥ እንደባህል
ተወስዶ የሚለመደው ማህበረሰቡ በአንድ ቦታ
ተረጋግቶ መኖር ከጀመረ በኋላ ነው ይላሉ
የዘርፉ ባለሙያዎች::
ምክንያቱም
የማስጌጫ እና የቅንጦት እቃዎችን ጥበብ
ማስፋፋት የሚቻለው ለማህበረሰቡ አስፈላጊ
የሆኑ መሰረታዊ ጉዳዮችን ማሟላት ከተቻለ
በኋላ መሆኑን እንደ
ማስረጃነት ያቀርባሉ::
ይህ
አባባልም ሐረሪዎች የስፌት ጥበባቸውን እና
ቤት ማስጌጫዎቻውን መስራት የጀመሩት ዘመናዊነት
ከገባቸው እና ዘመናዊነትን ከተላመዱ ቆየት
ያለ ጊዜ እንዳስቆጠሩ
ማሳያ ይሆናል::
የክልሉ
ርዕሰ መዲናም ሀረር
ከፍተኛ የስልጣኔ እድገት ደረጃ ላይ በደረሰችበት
በ16ኛው
ክፍለ ዘመን ላይ
የምስራቅ
አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት እና
የንግድ ማዕከል በመሆን
ግልጋሎት ሰጥታለች፡፡
ይህም የበርካታ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች
እንዲሁም
ረቂቅ የእጅ ጥበብ ያረፈባቸው መገልገያዎች
ባለቤት
እንድትሆን አድርጓታል የሚሉ
የታሪክ ምሁራንም በርካታ ናቸው፡፡ ከቤት
አሰራሩ ጀምሮ እስከ ምንጣፋቸው ድረስ ለአይን
በሚማርክ መልኩ ማዋቀርን ተክነውበታል::
ከሐሪሪዎች
መኖሪያ ብንነሳ የእጅ ጥበብ ምን ያህል ዋጋ
እነዳለው መረዳት ይቻላል::
የሐረሪዎች
ባህላዊ ቤት ጌይ ጋር ይባላል::
ቤቱን
የአገሩን ባህል የማያውቅ ጥበበኛ ካልሆነ
በቀር ማንኛውም የግንባታ ባለሙያ አሳምሮ
ሊሰራው ያዳግተዋል::
በሐረሪዎች
ጌይ ማለት ከተማ ሲሆን ጋር ማለት ደግሞ ቤት
ነው::
ከፍቺው
የምንረዳው ጌይጋር ማለት የከተማ ቤት እንደማለት
ይሆናል::
ከተሜዎቹ
ሐረሮች ደግሞ ቤቶቻቸው ግድግዳ ላይ በርከት
ብለው የሚንጠለጠሉ የዕደጥበብ ወጤቶችን
እንደማስጌጫነት ይጠቀማሉ::
የክልሉ
ነዋሪ አቶ መሃመድ ካሊድ እንደሚሉት፤
በወይን ጠጅ፣ቀይ፣ አረንጓዴ እና ሌሎችም
ህብረ ቀለማት የተጌጡ ሰፌዶች፣ ኢራዝ ሙዳይ
እና ሌሎች የስፌት አይነቶችም በሐረሪዎች
ቤት የማይጠፉ የዕደጥበብ ውጤቶች ናቸው::
ሁሉም
የየእራሳቸው አገልግሎት ቢኖራቸውም ከአገልግሎታቸው
በተጨማሪ ግን ለውበት መገለጫነት እንዲያገለግሉ
በሚል በስነውበት ደረጃቸው ከፍ እንዲል ተደርጎ
ይዘጋጃሉ::
በመሆኑም
ለዳቦ እና ቆሎ ማቅረቢያነት የሚውል የስፌት
እቃ እንኳን በግድግዳ ላይ ቢቀመጥ ጀርባው
ውብ ሆኖ ለሰው መታየት አለበትና በሐረሬዎች
እጅ በጥልቅ ዲዛይን እንዲዋብ መደረጉ አይቀሬ
ነው::
በአሁኑ
ወቅት የሐረሪዎች የስፌቶቻቸው ቅርፅ እና
ዲዛይን ስነ ውበት የላቀ ደረጃ ከመድረሱም
ባሻገር የተለያዩ ጎብኚዎችን ቀልብ መሳብ
እየቻለ ይገኛል::
በተለያዩ
ቀለማት ደምቀው እና ተውበው የተሰናዱት የዕደ
ጥበብ ውጤቶችን ለተመለከተም ሐረሪዎች ምን
ያህል የቀላማትን ህብር የመጠቀም ችሎታቸው
የላቀ መሆኑን እንዲረዳ ያስገድደዋል::
ዕደ
ጥበባቱ ለሐረሪዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው::
ምክንያቱም
አንድም ለመገልገያነት ሲጠቅማቸው በሌላ
በኩል ደግሞ ለጌጥ እና ማስዋቢያነት ጥቅም
ላይ ይውላል::
ከዚህ
ባለፈ ግን ለህብረተሰቡ ተምሳሌትነት እና
ምልክት ሆኖ በመቅረብ እያስተዋወቃቸው
ይገኛል::
ከእደ
ጥበብ ውጤቶቻቸው መካከል በውበቱ ትልቁን
ስፍራ የሚይዘው አለላ ነው::
አለላ
የሐረሪ ሴቶች አሳምረው የሚሰፉት የሳሎን
ሞሰብ አይነት የዕደጥበብ ውጤት ነው::
የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ባህል ማዕከል የህዝብ ግንኙነት እና
አለም አቀፍ ዳይሬከተሯ ወይዘሮ ሰብለ አበበ
እንደሚሉት፣ የሐረሪዎች ሞሰብ ከሌሎቹ የአገሪቷ
ክፍል ከሚሰሩት የተለየ በመሆኑ ተፈላጊነቱ
እየጨመረ ይገኛል::
በህብረቀለማት
ከማጌጡም በላይ ደግሞ አለላው ከገብስ አገዳ
መሰራቱ ከሌሎቹ ተመራጭ እና የተለየ ለመሆኑ
አይነተኛ ሚና አበርክቷል::
በተለያዩ
የኢትዮጵያ ክፍላት የሚዘጋጁት መሶብ እና
ሙዳዮች ከሰበዝ ወይም ስንደዶ ከተባለ የሳር
ዝርያ የሚዘጋጁ ናቸው::
ነገር
ግን የሐረሪዎቹ አለላ በጥንቃቄ በተዘጋጁ
የገብስ ተረፈ ምርት የሚሰሩ በመሆኑ በዋጋም
ውድ ናቸው::
በሐረሪ
ባለሙያ ሴት የተሰፋ አለላ በአሁኑ ወቅት
ከአራት እና አምስት ሺ ብር በላይ ያወጣል::
የማህበረሰቡ
ዲዛይንም ተወዳጅ እና ለአይን የሚማርክ በመሆኑ
በቤት ውስጥ እንደ ማስጌጫነትም ያገለግላል::
በመሆኑም
ይህን የዕደጥበብ ውጤት በሰፊው በማስተዋወቅ
ሴቶች በገቢ ደረጃ አቅማቸውን የሚያሳድጉበት
የስራ መስክ ማድረግ ያስፈልጋል::
ሌላው
የሐረሪዎች የእጅ ጥበብ ያረፈባቸው መታወቂያቸው
የባላዊ አልባሳቶቻቸው ናቸው::
ጠይ ኢራዝ
የሚባለው ባህላዊ ልብስ በጥቁር ጨርቅ ላይ
በተለያዩ ዲዛይኖች የሚዋበው ነው::
የባህል
ልብሱ ልክ እንደ ነጭ የሐበሻ የአገር ባህል
ልብስ የእራሱ የሆኑ ባለሙያዎች አማካኝነት
በአግባቡ ይዘጋጃል::
ነገር
ግን የሚለብሱት ያገቡ እና የዕድሜ ባለፀጋ
የሆኑ ሰዎች ብቻ ናችው::
በአንዳንድ
የኢትዮጵያ ክፍላተ አገራት ላይ ያላገቡ ሰዎችን
እና ያገቡ ሰዎች ለመለየት የጸጉር አቆራረጣቸው
እንደሚመሰክረው ሁሉ በሐረሪዎች ዘንድም
የትዳር እና የእዕሜ ሁኔታን ለመለያየት
የሚያገለግል የባህል አልባስ ሆኖ እየተዘወተረ
ይገኛል::
ልጃገረዶች
እና ሙሽሮች ደግሞ አጥላስ የተሰኘውን ባህላዊ
ልብስ ይዋቡበታል::
ባህላዊ
ልብሱ ደማቅ ቀለማትን የያዘ ሲሆን በአብዛኛው
ጊዜም ለስላሳ ሆኖ በአረንጓዴ እና ቀይ ቀለማት
ባላቸው ጨርቆች ይዘጋጃል::
በተለይ
በጥልቅ የጥልፍ ዲዛይን እና በአበባ ቅርጽ
የተጠለፉ ወርቃማ ክሮች ያሉበት ልብስ በመሆኑ
በሰርግ ወቅት ሙሽሪት እና ሚዜዎቿ ተውበው
ህዝብ ፊት ሲቀርቡበት ሐረሪዎች ውብ ባህል
እንዳላቸው ምስክር የመሆን አቅም አለው::
ወንዶቹ
በጌይ ከሎይታ ወይም ነጭ ኮፍያ መዋብ ከፈለጉ
በባህላቸው የተዘጋጀ ቆብ ይዘጋጅላቸዋል::
ኮፍያዎቹ
በብዛት ከክር የሚሰሩትን እና ለየት ባለ የስነ
ውበት ደረጃ የተዘጋጁ ሲሆኑ ወንዶችም ከሐይማኖትም
ሆነ ከባህል አንፃር በጭንቅላታቸው ላይ
በማድረግ በከተማዋ ሲዘዋወሩ ይታያሉ::
ኮፍያዎቹ
በማህበረሰቡ የዕደጥበብ ባለሙያዎች የሚዘጋጁ
ናቸው:: የተለያየ
አሰራር ያላቸው ሲሆን አሩዘ ከይሎታ/የሙሽራ
ኮፍያ/፣
ነጪሕ ከሎይታ/ነጭ
ኮፍያ/ እና
ሌሎች ስያሜዎችንም የያዙ ናቸው::
አንዱን
በጥልቅ የጥልፍ ጥበብ የተሰራ ኮፍያ ለመስራት
ሳምንታት ወይም አንድ ወር ሊፈጅ ይችላል::
በተለይ
የሙሽራ ኮፍያ ከሆነ በጥንቃቀዌ የሚሰራ በመሆኑ
እስከ አራት ሺ ብር ድረስ ሊያወጣ ይችላል::
በዘርፉ
የተሰማሩ የሐረሪ ሴቶችም ጥሩ ገቢ የሚያገኙበት
የዕደጥበብ ውጤት ነው::
ከአለላ
እና አልባሳት ወጣ ስንል ደግሞ የተለያዩ የእጅ
እና የአንገት ጌጦችን በሐረሪ የዕደጥበብ
ውጤቶች ውስጥ እናገኛለን::
አንደኛው
ቀርማ የሚባው ሲሆን በግንባር ጫፍና በፀጉር
መሐከል ላይ የሚደረግ ውብ ጌጥ ነው::
ጌጡ
በተለያዩ ሐይማኖታዊ ባህላት፣ ባህላዊ ዝግጅቶች
እና በሰርግ ወቅት ይደረጋል::
ቀርማ
ከብር ማዕድን በቀጭኑ ተዘጋጅቶ በተለያዩ
ገበያዎች ላይ ለሽያጭ ይቀርባል::
ሌላው
ደግሞ በውበቱ እና ግርማ ሞገሱ ከሌሎች ጌጠች
ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠው ወቅሪ የተባለው ጌጥ
ነው:: ጌጡ
በክብ ንብ ቀፎ አምሳያ የሚዘጋጅ ከብር የተሰራ
የአንገት ላይ ማጌጫ በመሆን ያገለግላል::
አሰራሩ
በአንድ በኩል የሚከፈት እና የሚዘጋ ሲሆን
አንገት ላይ በሚያርፍበት ጊዜም በውስጡ
የተለያዩ መኳኳያዎችን እና መሃረብንም ለመያዝ
አመቺ ነው::
በመሆኑም
ሴቶች በጭፈራ እና ጭብጨባ ወቅት በቀላሉ
ከደረታቸው ላይ ወሰደው ውበታቸውን እንዲያገኙ
ይረዳል:: ወቅሪ
ከብር የተሰራ ጌጥ ቢሆንም የተለያዩ ተንጠልጣይ
ዲዛይኖች የሚኖሩት በመሆኑ በግምት ከ150
ግራም
በላይ የብር ማዕድን ሊፈጅ ይችላል::
ይህ ውድ
የዕደ ጥበብ ውጤትም ታዲያ የሚዘጋጀው በጥበበኞቹ
ሐረሪዎች ነው::
ተዝቆ
ከማያልቀው የሐረሪዎች የዕደጥበብ ውጤቶች
መካከል እነሆ የተወሰኑትን አቀረብንላችሁ
እነጂ በርካታ ናቸው::
እኛም
ይህን ጥበብ ወደ ሃብት በመቀየት የሴቶቹን
አቅም ማሳደግ ይገባል እንላለን::
Ethiopian Harar peoples 