Thursday, April 27, 2017
Tuesday, April 25, 2017
አበበች ጎበና
ድካም
ድካም ያላቸው «ዘመን
ተሻጋሪዋ እናት»
ሴትየዋ
ጠንካራ ናቸው። ውልደታቸው በ1938ዓ.ም
ነው። በተለይም «እማማ»
እያሉ
የሚጠሯቸው ልጆች የእናትነት ፍቅርን ከእርሳቸው
ያለስስት እንዳገኙ ይመሰክራሉ። ወይዘሮ
አበበች ጎበና በ1972
ዓ.ም
ሃይማቶታዊ በዓል ለማክበር ለንግሥ ወደ ግሸን
ማርያም በሄዱበት ወቅት በኢትዮጵያ በነበረው
ድርቅ ምክንያት ከሞት አፋፍ የነበሩ ሁለት
ህፃናት ያገኛሉ። አላስችል ያላቻው ወይዘሮ
ታዲያ ህጻናቱን ወደ ወደ ቤታቸው ይዘው በመመጣት
የህጻናት ማሳደጊያ ስራቸውን «ሀ»
ብለው
ይጀምራሉ። ለ39
አመታትም
በሺዎች የሚቆጠሩ ወላድ አልባ ህጻናትን
ሳይታክቱ ለዘመናት አሳድገዋል።
በዚህም
የክብር
ዶክተር ማዕረግ የተሰጣቸው ወይዘሮ አበበች
ጎበና
በህጻናት ላይ በሚሰሩት በጎ ተግባር «አፍሪካዊቷ
ማዘር ቴሬሳ»
በሚል
ውብ ስም የሚጠሯቸውም
አሉ።
አሁን ግን ያ ጠንካራ ጉልበት ደክሟል፤ ጤናቸውም
አስጊ ደረጃ ላይ ይገኛል። በመኖሪያቸው
አካባቢያቸው ጉዳዬ ብሎ የሄደ ሰው ወይዘሮ
አበበች የቀድሞውን ጊዜ እንኳን በቅጡ ማስታወስ
ተስኗቸው ውል የሌለው ንግግር ሲያደርጉ
ሊያደምጥ ይችላል።
ህይወታቸውንም
በእራሳቸው እገዛ ብቻ መመራት የማይቸሉበት
ደረጃ ላይ ናቸው። በመሆኑም ዘወትር አልጋቸው
ላይ ጋደም እንዳሉ ነው። እርጅናውም ተጫጭኗቸዋል።
ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም አስፈላጊውን
እንክብካቤ የምታደርግ ሞግዚት ከአጠገባቸው
አትጠፋም። የጤናቸውንም ሁናቴ በየጊዜው
የሚከታተል የህክምና ባለሙያዎች ተመድቦላቸዋል።
ይሁንና ጤናቸው ባልታወቀ ሁኔታ ታውኮ አልጋ
ላይ መዋል ከጀመሩ አመት ከአመት በላይ መቆጠሩን
በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ይገልፃሉ። ህጻናት
ማሳደጊያውን መምራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ
ናቸው።
የአበበች
ጎበና ህጻናት እንክብካቤና ልማት ማህበር
ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የወይዘሮ አበበች
የስጋ ዘመድ የሆኑት አቶ እሸቱ አረዶ እንደሚናገሩት፤
ህጻናት ማሳደጊያውን የመሰረቱት የወይዘሮ
አበበች የጤና መታወክ ቢገጥማቸውም ድርጅቱ
በቦርድ የሚመራ በመሆኑ ስራው እንደቀጠለ
ይገኛል። ቦርዱ አምስት አባላት ያሉት ሲሆን
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተርም በአሁኑ ወቅት
ወይዘሮ አበበች ጎበና ናቸው። መስራቿ ጤናቸው
ታውኮ አስተዳዳሪ ተደርገው የተቀመጡትም
ከሞራል ጋር በተያያዘ መንገድ ሲሆን በተጨማሪም
ጤናቸው በጊዜ ሂደት ይሻሻላል ከሚል ግምት
የመነጨ ነው። ይሁንና በቦርዱ ውክልና መሰረት
ማንኛውንም ስራ እየመሩ ያሉት አቶ እሸቱ
ናቸው።
«ወይዘሮ
አበበች ከሰባት አመታት በፊት ፍርድ ቤት
ቀርበው ነበር»
የሚሉት
አቶ እሸቱ፤ በጊዜውም 'እኔ
ስሞት ድርጅቱን መንግስት ይረከበው'
የሚል
ኑዛዜ ማቅረባቸውንም ይናገራሉ። ይሁንና ይህ
ኑዛዜ በህግ ደረጃ እንደማይደገፍ ይገልፃሉ።
ይህን የተናዘዙትም ድርጅቱ በግለሰብ እጅ
ገብቶ አሰራሩ እንዳይበላሽ እና ገንዘብ
እንዳይባክን ከሚል ስጋት የመነጨ እንደሚሆን
ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። የኢፌዲሪ የበጎ
አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ህግ
ግን ማንኛውም ተተኪ እስከመጣ ድረስ ስራው
እንዲቀጥ ማድረግ እንደሚችል ይጠቁማሉ።
የህጻናት
ማሳደጊያው የአስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ
ቸሩ በቀለ በበኩላቸው እንደሚገልፁት፤ በፍቼ፣
ጉደር ፣ ቡራዩ እና በአዲስ አበባ ላይ ባሉ
ቅርንጫፎችም ከ250
በላይ
ሰራተኞች ተቀጥረው ለማህበረሰቡ ድጋፍ
እየተደረገ ይገኛል። በህጻናት ማሳደጊያ
ማዕከል ውስጥ ሰላሳ አራት ህጻናቶች ይገኛሉ።
በማህበረሰቡ ውስጥ ድጋፍ የሚደረገላቸው
በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ይገኛሉ። በተለይ
ሴቶቹ የተለያዩ የሙያ ስልጠና በመስጠት ወደ
ሰራ እንዲሰማሩ ይደረጋል። ብድር እና ቁጠባ
ላይ ድጋፍ የሚያገኙ ሴቶች አሉ።
«በማዕከሉ
ስለሚያድጉ አዲስ ህጻናትን ላይ ትኩረት
አይደረግም»
የሚሉት
አቶ ቸሩ፤ ይለቁንም በማህበረሰቡ ውስጥ ሆነው
ድጋፍ የሚያሻቸው ህጻናት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ
ይገልፃሉ። ይህም የሚሆነው ህጻናትን በማዕከል
ውስጥ ከማሳደግ ይልቅ ከማህበረሰቡ ጋር ቀላቅሎ
ማሳደገ በስነልቦና እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ
አዋጭ መሆኑ በመታመኑ መሆኑን ያስረዳሉ።
በመሆኑም በቀጣይ ጊዜያት አስገዳጅ ሁኔታ
ካልተፈጠረ በቀር ህጻናትን በማዕከሉ ውስጥ
ለማሳደግ እንደማይሞከር ይናገራሉ።
የተረሳው ግድብ «አልዌሮ»
የተረሳው ግድብ «አልዌሮ»
የጋምቤላው
አልዌሮ ግድብ እንደሃውልት እያዩ የሚያደንቁት
ብቻ ይመስላል። ሃውልትም
ተጎብኝቶ ገንዘብ ያመጣል የአልዌሮ ግድብ
ነገር ግን ከዚህም የተለየ ነው። ይፈሳል ዛሬም እነደፈሰሰ ነው። ነገም ይነጉዳል፤ ከልካይም
የለው። ግርማ ሞገሱ በዛ ሞቃታማ አካባቢ
ያለውን ሃሩር ያስረሳል። ግና ምን ያደርጋል
ሩብ ምኝተ አመት አለፈ እንኳን ሊሰራበት ቀርቶ
ስሙን እንኳን በአግባቡ መስማት እስከማይቻልበት
ደረጃ ደርሷል። ከጋምቤላ ወላጆች ውጪ የሆኑ የከተማ
ነዋሪዎች ግድቡን ታውቁታላችሁ?
ተብለው ቢጠየቁ
እንኳን ማስታወስ ይከብዳቸዋል። ለነገሩ
በምን ያስታውሱት አሳ በብዛት አYሰገርበት
ወይም እርሻው ተስፋፍቶ አልተሰራበት ደግሞም
ቱሪስት እነዲጎበኘው አልተደረገ።
ጋምቤላውያን
ከልጅ ልጅ ያስተላለፉት አንድ ተረት አላቸው።
ተረቱም በአንድ ወቅት በጋምቤላ ክልል በአንዲት
ቀበሌ ውስጥ ይኖሩ ስለነበሩ የአንድ ቤተሰብ
አባላት ላይ የተመሰረተ ነው። በቤተሰቡ ውስጥ
ያለው ወጣት ስራ የማይሰራ ሲሆን ተፈጥሮ
የለገሰችውን ፍራፍሬ ብቻ እየቆረጠ በመመገብ
መኖርን የመረጠ ነበር። በየወቅቱም በተፈጥሮ
የሚያፈሩ የተለያዩ ምግቦች ቢኖሩም ከዚህም
ላይ የሚያነሳው የምግብ ፍላጎቱን ለማርካት
የሚበቃውን ያህል ብቻ ነበር። መሬቱ ትንሽ
ቆፍረው ቢዘሩበት ትርፍ ምርት እንደሚያስገኝ
ግን ሳይገነዘብ ቀርቶ አልነበረም። አባት
በልጃቸው ስንፍና በማዘን ይበሳጩ ነበር፡፡
አቅማቸው ደክሞ ሞት አፋፍ ላይ በደረሱ ጊዜ
የቅርብ ወዳጃቸውን ያስጠሩና እንዲህ ብለው
ኑዛዜያቸውን ይናገራሉ። ለወዳጃቸውም “እኔ
ስሞት ቀብሬ ከተፈጸመ በኋላ ፍራፍሬዎቹን፣
ከብቶቼን እና እርሻውን አቃጥላቸው። ወንዱ
ልጄ በጣም ሰነፍ ስለሆነ ከሞትኩ የእኔን
ንበረት እነዲወርስ አለሻም»
ይሉታል፡፡
«ከሞትኩ
በኋላ ምንም ሳትፈራ ልጆቼና ሚስቴን አስቀርተህ
ቤቴን፣ ንብረቴንና እንዲሁም ፍራፍሬዎቹን
አቃጥላቸው፡፡ ሁሉንም ነገር አቃጥልና ለሰነፉ
ልጄ ወንድምና እህቶቹን ከእናታቸው ጋር
አስረክበው። በዚህም እራሱንና ቤተሰቡን
ማስተዳደር እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ ይየው»
ብለው ይናዘዛሉ።
መሬቱ ሳይዘሩበት የሚያበቅል ቢሆንም ሲቃጠል
ግን ካልተዘራበት እና ካልታረሰ ምንም ፍሬ
እንማያፈራ ገልፀው ንግግራቸውን ያጠናቅቃሉ።
አባት ከሞቱ በኋላ ልጃቸው ንብረት እንዲወርስና
ሰነፍ ሆኖ እንዲቀጥል አልፈለጉም፡፡ በዚህም
ምክንያት ነበር ኑዛዛያቸውን መራራ ያደረጉት።
እናም
ጓደኛው እንደተባለው አደረገ፡፡ በአካባቢው
ያሉ የተፈጥሮ ፍሬዎች የወደሙበት እና መጠለያ
ያጣውና ኮበሌ የሚላስ የሚቀመስ ባለማግኘቱ
የግድ መስራት እንዳለበት ያምናል። የተለያዩ
ፍራፍሬዎችን ተክሎ በመንከባከብ ከእራሱ
አልፎ ለአካባቢው ሰዎች እየሸጠ ቤተሰቡን
ማስተዳደርም ቀጠለ። ብዙ ምርት ስላመረተና
ሃብትም ስላፈራ የአባቱ አገልጋዮችም በእርሱ
ሥር ሆኑለት፡፡ በዚህም ጠንክሮ የመስራትን
ዋጋና ከበሬታ አገኘ፡፡
ይህ
ታሪክ አልፏል ነገር ግን በክልሉ አሁንም
ጥንካሬን በተግባር የሚያስተምሩ አካላትን
የሚያሻ ክስተት መኖሩ ይስተዋላል። የተፈጥሮ
ሃብት በተንጣለለበት መልካም መሬት ላይ ውሃ
ሌት ተቀን ይገኛል። ከዚህም ለአገር የሚተርፍ
የአሳ ምርት ለገበያ ማቅረብ ይቻላል።
አልዌሮ
ግድብ ከጋምቤላ ከተማ አርባ አራት ኪሎ ሜትር
ርቃ ከምትገኘው አቦቦ ወረዳ አቅራቢያ ይገኛል።
በአካባቢው ለደቂቃ ቆም ብለው ቢመለከቱ ከሰፊው
የውሃ አካል ውስጥ ብቅ እያሉ የሚሰርጉ አሳዎችን
በተደጋጋሚ ይመለከታሉ። ዝም ብሎ ለታዘባቸውም
ሰው በሌለበት ቤት እንደሚርመሰመሱ አይጦች
'ግዛቱ
የእኛ ነው' የሚሉ
ይመስላል። ምክንያቱም አስጋሪዎች ያልተመለከቱት
የአሳዎች ሰፈራ መሆኑን ሁኔታው ይነግረናል።
ግድቡን
በቅርበት የሚያውቁት አቶ ኡሞድ ኡቦያ በአቦቦ
ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ናቸው። እርሳቸው
እንደሚናገሩት፤ አልዌሮ እና ሂሩ
ወንዞች በአንድነት ወደ ግድቡ ይገባሉ።
ግድቡ በደርግ ዘመነ
መንግስት ሲገነባ 10
ሺ ሄክታር
መሬት እንደሚያለማ ታቅዶ ነበር። በተያያዘም
ሰፊ የአሳ ሃብት የሚገኝበት እድል እንዳለው
ይታሰብ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ግድቡ የአሳ
ሃብት ክምችት አለበት። ነገር ግን እስከ አሁን
ድረስ ግድቡ ላይ አሳ የሚያጠምዱት አርባ
የአካባቢው ነዋሪዎች ብቻ ሲሆኑ፤ የሚጠቀሙትም
ኋላ ቀር መሳሪያዎችን ነው። በየቀኑም ሀያ
የሚደርሱ የእንጨት ጀልባዎች በማሰማራት
እስከ አንደ ሺ አሳዎችን ያጠምዳሉ። ይህም
የሚከናወነው በሌሊት ወቅት ነው።
«በየዕለቱ
በአማካይ ስድስት ሺ ኪሎ ግራም የሚመዝን የአሳ
ምርት ይገኛል» የሚሉት
አቶ ኡሞድ፤ ይህም ከግድቡ የአሳ ሃብት እምቅ
አቅም ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛ መጠን
መሆኑን ነው የሚያስረዱት።
ቆሮሶ
የተባለው የአሳ ዝርያ በማህበረሰቡ የተለመደ
ምግብ መሆኑን ይናገራሉ። አጥማጆችም ዋነኛ
ትኩረታቸው በዚሁ ዝርያ ላይ ብቻ ነው። ይሁንና
ጥናት ቢደረግበት በርካታ የአሳ ዝርያዎችን
አቅፎ የያዘ ግድብ መሆኑ አያጠራጥርም።
ምክንያቱም ውሃው ውስጥ የተለያዩ አሳዎች
በአንድነት እና በብዛት ሆነው ሲንቀሳቀሱ
በየጊዜው መመልክት ይቻላል። በመሆኑም በቂ
ጥናት ሊደረግበት እንደሚገባ ይጠቁማሉ።
እንደ
አቶ ኡሞድ ገለፃ፤ በተለይም ክልሉ ዘመናዊ
ጀልባዎችን እና የማጥመጃ ግብአቶችን ለማቅረብ
ያደረገው ጥረት አነስተኛ በመሆኑ አመራረቱ
ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ለሚገፋው ማህበረሰብ
ተገቢውን ጠቀሜታ እያገኘ አይደለም። ግድቡ
ላይ ሳውዲ ስታር የተሰኘው ኩባንያ በመስኖ
ለማልማት የቦይ ካናሎችን ጥገና እያደረገ
መሆኑ አበረታች ነው። እንደ ግብርናው ስራ
ግን ለአሳ ሃብት ልማት ትኩረት ያስፈልገዋል።
በዋነኛነትም ዘመናዊ የሞተር ጀልባዎችን
ተገዝተው ለተደራጁ ወጣቶች ሊተላለፉ ይገባል።
በአሁኑ ወቅትም ወጣቶች በዘርፉ ለመስራት
ፍላጎት እንዳላቸው እየጠቆሙ ይገኛል። ከዚህ
ጋር ተያይዞ ለአስጋሪዎችን የዘመናዊ አመራረት
ስልጠና መስጠት ተገቢ ነው። ይህም ለአገር
የሚተርፍ የአሳ ምርት ለማምረት ያግዛል።
Tuesday, April 18, 2017
Monday, April 17, 2017
Stop Animal Cruelty
The people Who beat animals should be beaten back
Ethiopia's animal welfare, animal transport, animal handling, market, supply chain is against animal welfare. You will sea a man with donkey or horse prodding it with a long stick to surge forward. And beating the the pack animal giving him service harshly. It is normal in Ethiopia to watch this kind of scene every day.
In Ethiopia, due to various reasons, animals' right is often violated here and there. Absence of legal document and lack of awareness animal welfare, among others, are attributable to the problem
Animal Walfare
Animal protection Law in Ethiopia
Article 822 in the Criminal Code Proclamation No. 414/2004
states that in a public place, or a place open to the public or which
can be viewed by the public, it is an offence to commit acts of cruelty
towards animals or inflict upon them ill-treatment, revolting violence
or brutality.
It is also an offence to organise shows or entertainments in which animals are treated with cruelty, are mutilated or killed, whether it be fights between animals or with animals, shooting of captive animals or other offences of a similar kind. “Animal” is not defined in the Criminal Code.
It was reported in late 2012 that the government was considering producing the country’s first law to protect animals and promote their humane care and use, entitled the Directive for Animal Welfare. As at the date of this report, it is not clear whether this is being progressed and whether the proposed draft will extend the current scope of protection for animals.
The existing legislation (Article 822 Criminal Code) presents a basic level of protection by which animals are only protected from human-inflicted suffering that is carried out in public.
Therefore the current legislation is not fully effective to make animal welfare and the issues associated with the suffering of animals of mainstream concern in Ethiopia. There is no protection relating to conduct in private or for negligent behaviour. It has been said that attention to animal welfare can improve the livelihoods of people who are dependent on animals , and the government is encouraged to consider such issues when developing future policy, legislation and awareness raising tools.
Subscribe to:
Comments (Atom)
Featured post
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደር...
-
ባህል የአንድን ማህበረሰብ የእምነት ፍልስፍና ጥበብ የአስተሳሰብ እሴቶች ያካተተ ነው። ውስብስቡ እሳቤ በቁሳዊ ባህሎቹ እና ልማዶቹ በማህበራዊ ግንኙነቶቹ እና በተለያዩ ትውፊቶቹ አማካኝነት ተጨባጭ አሰራር ይኖረዋል።...
-
ድካም ድካም ያላቸው « ዘመን ተሻጋሪዋ እናት » Abebech Gobena <<Africa's Mother Theresa>> ሴትየዋ ጠንካራ ናቸው። ውልደታቸው በ 1938 ዓ . ...
-
እንኳን ሰው ይቅርና እግር እና እግር ይጋጫል እንደሚሉ አበው በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ህይወት አለመግባባት ሊከሰት ይችላል። ግጭት ካልበረደ ደግሞ አካላዊ፣ስነልቦናዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ብቻ ሳይሆን ክቡር የሆነዉን የሰ...
-
By Getnet Tesfamariam The issue of universal food security is at the heart of many of the ethical issues related to GM technol...
-
ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በ 1917 ዓ . ም ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትን ሲመርቁ እንዲህ ብለው ነበር የሀገሩን ትምህርት ጽህፈት ቋንቋ እንደሚገባው የማያውቅ የውጭውን እማራለሁ የሚል ምሳሌው ቀዛፊ እንደሌለው ታንኳ ነው...
-
Domadol Addicted drug in Ethiopian Schools ሱስ ም እንደፋሽን ተከታዩ በዝቷል :: ትውልድ ም እንደቀልድ ለሙከራ በጀመረው ስህተት አየተጠለፍ በሱስ ሰንሰለት ታስሮ መውጫ ቀዳዳ አጥቶ ...
-
ነቀምቴ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ትገኛለች። እንደ አካባቢው አባቶች የስሟ ትርጓሜ «የታጨች» እንደማለት ነው። በከተማዋ ከሚገኙ መስህቦች ውስጥ ደግሞ ባለ ግርማ ሞገሱ እና ሁለት ነጥብ አምስት...
-
በመኪኖች ጭስ እንደታፈኑ ውለው ከሚያድሩት የአዲስ አበባ ሃውልቶች እና ቅርሶች መካከል የሚመደበው የ አፄ ቴዎድሮስ አደባባይ ዙሪያ ገባውን በላስቲክ ሸራ ተሸፍኗል። አይን የለውም እንጂ አይን ቢኖረውማ እዚህም እዚያ...
-
ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደውን የአስፋልት መንገድ ይዘው ሲጓዙ ፍቼ፣ ደብረ ጉራቻ፣ጎሀ ጽዮን ከተሞችን አልፈው የዓባይን በረሃ ካጠናቀቁ በኋላ የደጀን ከተማን ያገኛሉ፡፡...
-
የኪነጥበብ ስራዎች ልክ እንደ መስታወት በዘመናቸው ያለውን ከሃድ ቁልጭ አድረግው ያሳያሉ ። መስታወቅ ጉድፍንም ውበትንም በግልጽ ፊት ለፊት እነደሚያቀርብልን የሥነጽሁፍ ስራዎችም እነዲሁ ናቸው። እ ን ደ ሐዲስ አለ...




