Saturday, October 17, 2020

የግብርና ምርቶችን በቅናሽ ለማቅረብ በ350 ሚሊዮን ብር ሱፐርማርኬቶችን ሊገነባ መሆኑን ሚድሮክ አስታወቀ

 

የግብርና ምርቶችን በአነስተኛ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ የሚረዱ ሱፐርማርኬቶችን በ350 ሚሊዮን ብር ሊገነባ መሆኑን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አስታወቀ።

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃላፊ አቶ ጀማል አህመድ እንደገለጹት፤ የግብርና ውጤቶችን በቅናሽ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ ሱፐርማርኬቶች በ350 ሚሊዮን ብር ወጪ ለመገንባት እቅድ ተይዟል። የገበያ ሰንሰለቱን በማሳጠር የሚሰሩ ሱፐርማርኬቶችን በማጠናከር ሸማቹ ህብረተሰብ በቅናሽ ዋና የአርሶአደሩን ምርቶች እንዲያገኝ ይደረጋል።

እንደ አቶ ጀማል ገለጻ፤ ተቋሙ በስሩ ባሉት 10 የኩዊንስ ሱፐርማርኬት አና አዲስ ሆም ዴፖ ቅርንጫፎች አማካኝነት የመጀመሪያ ደረጃ የግብርና ውጤቶችን እና የተለያዩ ምርቶችን ለህብረተሰቡ በቅናሽ ዋጋ ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል። የሱፐርማርኬት ዘርፉን በማስፋት የህብረተሰቡን የምግብ አቅርቦት ለማስፋት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ይገኛል። በአዲስ አበባ አገልግሎት እየሰጡ በሚገኙ የኩዊንስ ሱፐርማርኬቶች ላይ የማስፋፊያ ስራ የሚከናወን ሲሆን፤ በተለያዩ የምግብ ምርቶች የታየው የሸማቾችን ፍላጎት ለማሟላትም በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተጨማሪ ሱፐርማርኬቶች ይሰራሉ። በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ 13 ትላልቅ የሱፐርማርኬት አገልግሎት መስጫ ፋሲሊቲዎች ይገነባሉ።

ከመንግስት ጋር በተቀናጀ አሰራር የግብርና ውጤቶችን ለተጠቃሚዎቸ በስፋት እንዲቀርቡ ይደረጋል ያሉት አቶ ጀማል፤ የምርት ሽያጩንም አሰራር በቴከኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የገንዘብ ኖት ንክኪን በሚቀንሱ አሰራሮች አስተማማኝ ግብይት ለማከናወን የሚያስችል ትግበራ መጀመሩን ተናግረዋል። እንደ እርሳቸ፤ ለዚህ አሰራር ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባባር የግዥ ስጦታ ካርድ ተዘጋጅቷል። ካርዱ በየጊዜው የሚሞላ የገንዘብ መጠን የሚኖረው ሲሆን ሸማቾች በተፈቀዱ ሱፐርማርኬቶች በኩል ያለጥሬ ገንዘብ እንዲገበያዩ ይረዳል። በካርዱ ላይ የተጫነው ገነዘብ ሲያልቅ በማንኛውም የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ በማስሞላት ለተጨማሪ አገልግሎት ማዋል የሚያስችል አሰራርን ይዟል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ እንደገለጹት ደግሞ፤ በአቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት የሚመጣ ችግርን ለመቅረፍ የሱፐርኬቶች ድርሻ ከፍተኛ ነው። ከተማ አስተዳደሩ የግብርና እና የተለያዩ ምርቶችን ለህብረተሰቡ ከሚያቀርቡ የሱፐርማርኬት ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት አለው። የከተማው ነዋሪ የግብርና ውጤቶችን በቅናሽ ዋጋ  እና በአፋጣኝ እንዲያገኝ የከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ መዋዕለ ነዋያቸውን ለሚያፈሱ የግል ባለሃብቶች ምቹ የአሰራር ሁኔታዎችን አዘጋጅቷል።

እንደ አቶ አብዱልፈታህ ገለጻ፤ በዝቅተኛው የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል የምግብ እና ሸቀጣሸቀጥ አቅርቦትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውጤታማ ለመሆን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን መከተል ይገባል። በዚህ ረገድ የዲጂታል ካርዶችን ጥቅም ላይ በማዋል እና ከጥሬ ገንዘብ ንክኪ የሆኑ አሰራሮችን በመከተል ረገድ የተጀመሩ መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋት ያስፈልጋል። ከተማ አስተዳደሩም የንግድ ዘርፉን የማዘመን ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል። 

በጌትነት ተስፋማርያም

Thursday, July 30, 2020

Awareness before practice is vital for Gm food issues


By Getnet Tesfamariam

The issue of universal food security is at the heart of many of the ethical issues related to GM technology.  According to a new United Nations report being launched in 2017 stated that the current world population is expected to reach 8.6 billion in 2030, 9.8 billion in 2050 and 11.2 billion in 2100.
               When we come to the horn of Africa, According to the Ethiopian statically Agency data the population of Ethiopia is estimated more than 129 million at 2130. This data shows there will be huge challenges for global food production in the coming years. if the amount of food production is not increased. Now a a days 1 of every 10 people around the world experience chronic hunger, which is more than 815 million people are currently chronically hungry. But an Advocates of GM crop argues that supplementary development of Bio technology is vital to meet this challenge.

Gm food crops are becoming choice of consumption for consumers

Biotechnology is offering peoples with broad options for how they can use agricultural and commercial forestry lands. The cultivation of genetically modified (GM) crops on thousands of hectares of lands and their addition into food chain is a huge global genetic experiment. Considering the fast rate of knots of new advances in the production of genetically modified crops, Marketers, farmers and policymakers and consumers worldwide are confronted to reach a consensus on a clear vision for the future of world food supply.

According to food science scholars the current food biotechnology debate illustrates the serious conflict between two groups. The first groups are Agri-biotech investors and their affiliated scientists who consider agricultural biotechnology as a solution to food shortage, the scarcity of environmental resources and weeds and pests infestations. And the second groups are independent scientists, researchers, farmers and consumers who notify that genetically modified food introduces new dangers to food security, the environment and human health.

The first group said that GM is vital for supply of food in the world to meet the demand of consumption and population increase. But the second groups ignores their ideas and believes GM foods are risks for humans, loss of biodiversity , and degrading natural appearance of living animals. They also argue that GM can cause for the emergence of super weeds and super pests, food allergies and other more scary side effects. 
           When we come to East Africa especially in Ethiopia, The knowledge about GM foods is in controversial way. Some peoples believe it’s like devil cultivation but scientists and agricultural employees believe it as a good choice of food. And I planned to make an interview for 7 peoples in Addis Ababa and Adama cities. The aim of the interview was to know the level of knowledge crop consumers and attitudes about GM foods.


         I selected the inter-regional cross transport bus stations, because it helps to get peoples who come from different directions of the country.   The first 4 interviewee at Addis Ababa city didn’t know about GM foods and even some of them related it with Canadian aid maize and other crops. These results suggest that the overall attitude of the cities consumers is not cautious of GM food. The other three respondents that were interviewed at Adama city where Shashemene, Assela and Mojo cities residents. All of them didn’t know about GM foods and the laugh when they interviewed, because of they don’t heard it before.
        
           Mr. Alemu who is living in Shashemene said that, I don’t know what is GM, but he guess it will be food that is useful for animals. This shows that the knowledge level of the society is at zero level about GM foods. Only researchers and some politicians are talking about it but I doughty the majority of the farmers in Ethiopia are far beyond the GM technology. In the absence of sufficient understanding of biotechnology, the public’s attitude towards GM food safety can be misleading. 

           The majority of the farmers and consumers knowledge about GM in Ethiopia is approximately  at zero level. Even they didn't have bio-technological cotton farming which is cultivated in Afar region.I was searching and informally interviewing peoples about their reflection on GM foods. In Ethiopia most of Consumer and farmers attitudes about GM food are complex and interwoven with the consumer’s knowledge of the science, lifestyle and public perception.
There has been a general lack of fundamental studies on the public’s scientific perception and policy interpretation of GM food in Ethiopia. The only institutions that promote GM in Ethiopian more strategically are Ethiopian Agricultural Research institute and Ethiopian biotechnology institute. But before intruding the practice of Gm food crops the transformation of knowledge about GM will comes first.  When the farmers and consumers are aware of GM foods they can practice it on their land and home. But practicing it first before making awareness is just like advancing the cart before the horse.
It is better to make awareness about GM before public tends to build upon its negative impression of GM food due to face of wrong information on social medias.  Written documents, advertisements, documentaries and educational courses about GM should be made widely available through various Medias. And mainly the GM issue should be well articulated and included in the new Ethiopian educational and training road map.


Sunday, April 5, 2020

ከእኛ የተረፈውን መብላት ሲገባት ከእርሷ የተረፈውን እንበላለን


የሰው ልጅ ከፍጥረታት ሁሉ ብልህ እና አርቆ አሳቢ ነው። ከጥንት የጋርዮሽ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ሲጠቀም ኖሯል። በቤቱ ውስጥም እንስሳትን እያላመደ ያቆያል። ነገር ግን አንድ ለማዳ ሳትሆን በቤቱ ውስጥ የምትራመስ ጎጆዋን በሰው ጎጆ ቀልሳ የምትኖር እንስሳን ጨርሶ ማራቅ አልቻለም። ብዙዎች ስሟን እንኳን ለመጥራትን ሲቀፋቸው ይስተዋላል። አይጥ በእንግሊዘኛው አጠራር mouse ወይም rat አፈጣጠሯ ከአጥቢ እንስሳት መካከል ትመደባለች። እንዲሁም በፈጣን እንቅስቃሴዋ እና በማሽተት ችሎታዋ ከፍተኛነት ትታወቃለች።
የአይጥ እድሜ 18 ወራት ሲሆን፤ በርካታዎቹ ግን በተለየዩ አደጋዎች ምክንያት አንድ አመት ሳይሞላቸው ይሞታሉ። በአብዛኛው በእንጨት እና ከአፈር በተሰሩ ቤቶች ውስጥ በቀላሉ ገብታ ለመኖር የሚያስችላል ጠንካራ ጥርሰንም ታድላለች። አንዳንዴም በድንጋይ እና በብሎኬት በተሰሩ ቤቶች ውስጥ ከገባች ዘሮቿን በማብዛት ተደላድላ ለመኖር አትቸገርም። እናም በኢትዮጵያ ደግሞ አብዛኛው ቤቶች የተሰሩት ከአፈር እና ከእንጨት በመሆኑ በእያንዳዱ ጓዳ ውስጥ አለች ቢባል ማጋነን አይሆንም። አለቃ ገብረሃናም ምግብ በሚበሉበት ቤት ውስጥ ትንሿ እንስሳን ከእንጀራ ማስቀመጫው ስፍራ በማየታቸው ከሞሰቡ አይጡ ብለው መቀኘታቸውን ታሪክ ይነግረናል። ነገሩ ጥንትም ትንሿ እንስሳ እንደ ድመት ከሰዎች ጋር ተላምዳ ቤት ውስጥ እንትኖር አይፈቀድላት እንጂ በእያንዳንዱ ቤት ግን በየስርቻው የመገኘቷን ጉዳይ ያሳያል። ያለፈቃድ በቤት ውስጥ የመገኘቷ ጉዳይም ብዙዎችን ሲያንገበግባቸው ይኖራል።
በተለይ የሰፈራችን እድሜ ጠገብ ልብስ ሰፊ አቶ አክሊሉ እንስሳዋን ክፉኛ አይወዷትም። በአንድ ወቅት በቤታቸው ራዲዮናቸውን ከፍተው አረፍ በአሉበት ያለአንዳች ምክንያት ከዘራቸው ላይ ተጠምጥማ ስታበቃ ወደ ጉድጓዷ የገባችበት ጊዜ ለእርሳቸው እንደ ህልም ነው። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ላገኙት ሰው ሁሉ ይቺ ከይሲ ፍጥረት ከዘራዬን አረከሰችው እያሉ ለለቅሶ እና ለጥየቃ በየሄዱባቸው በቦታዎች ሁሉ ሲያንቋሽሿት ይውላሉ። አጥይ ብለው እንኳን ደፍረው መጥራት ስለማይሆንላቸው «ስሟን ቄስ ይጥራውና» እያሉ ነው ወጋቸውን የሚጠርቁት። እናም በየዕለቱ ወጥመድ ቢያዘጋጁ፤ መርዝ ቢነሰንሱ መንታ የመሰሉ ዝርያዎቿን ይገድላሉ እንጂ ጭራሽ ልትጠፋ አልቻለችም። አይጥ አዳኝ የተባሉ ድመቶችን በቤታቸው ውስጥ ቢያሰማሩም ድመቶቹ ከመንደሩ በሚቃርሙት ትርፍራፊ ምክንያት ሆዳቸውን እየነረቱ የቤቱ አሮጌ ሶፋው ላይ መገላበጡት ተያይዘውታል። በመሆኑም እንስሳዋን ከቤታቸው ለማጥፋት አዲስ መላ በአዕምሯቸው እስኪመጣላቸው ድረስ እንደተናደዱ ይኖራሉ።
አንድ ቀን ታዲያ አዛውንቱ ከስራ ወደ ቤታቸው ገብተው አረፍ እንዳሉ ባለቤታቸው ምግብ ለማቅረብ ሞሰቡን ከፈት ቢያደርጉት አጅሪት ተስፈንጥራ ወጥታ በአልጋቸው ስርቻ ውስጥ ተደበቀች። አቶ አክሊሉም የዛን ቀን እህል አልበላም ብለው እስክ ምሽቱ ሶስት ሰዓት ድረስ ሲገላገሉ ቆይተው ደረቅ ዳቦ አስገዝተው ተመገቡ። አቶ አክሊሉ ነገሩ የከነከናቸው እርሳቸው ያልበሉትን እንጀራ እንዴት አይጧ ቀድማ ትመገበዋለች የሚለው መበለጥ ነበር። ባለቤታቸው ደግሞ «የዛሬን ነው እንዴ አይጧ ሁሌስ ሽር የምትለው ከሞሰቡም አይደል እንዴ» ብለው ንዴታቸውን የሚያባብስ ንግግር አከሉላቸው። «እንዴት በተከበርኩበት አገር አንዲት መናኛ ጅራታም እንስሳ ለፍቼ ያገኘሁትን ምግብ ቁጭ ብላ ትሰለቃለች» በሚል እልህ እንስሳዋን ለግድያ ሲፈልጓት አደሩ። ቤቱን አመሰቃቅለው ያገኙት ግን በሶስት ክፍል ቤታቸው ውስጥ የሚገኙ አስር ጉድጓዶችን ብቻ ነበር። አስር ጉድጓዶች ስትፈለፍል እኔ የት ነበርኩ ብለው እራሳቸውን ቢጠይቁም መልስ አላገኙም። ምክንያቱም አንድም ቀን ከቤታቸው ውጪ አድረው አያውቁም ነበር። ከተማሰው ቤታቸው ይልቅ ግን የአባወራነታቸው ቀድሞ የመመገብ ክብር መደፈሩ አልዋጥ ብሏቸዋል።
አዛውንቱ ሚስት ከአገቡ ወዲህ ዶሮ ወጥም ይሰራ፣ እንጀራም ይጋገር ምንአለፋችሁ ማንኛውም ምግብ ከተሰራ ቀደሞ የሚቀርበው ለእርሳቸው ነበር። አሁን ግን ስሟን እንኳን በወጉ በማይጠሯን እንስሳ ተቀድመዋል። ለአቶ አክሊሉ ከአይጧ ጋር የያዙት እልህ አስጨራሽ ትግል ቀድሞ የመብላት እና ያለመብላት ነው። በመሆኑም ጉዳዩ ለእርሳቸው የሞት እና የሽረት ያክል ሆኗል። ነገን አግኝቿት ልኳን ካሳየኋት በኋላ አባወራነቴን አስከብራለሁ በሚል ሃሳብ ሌት ተቀን እንስሳዋን የሚያጠፉበት መንገድ እንዳሰላሰሉ ናቸው። እርሷም ቀድማ ምግቡን መቀማመሷን አላቆመችም።
እናም አማካሪም ሆነ ሁነኛ ባለሙያ ሲያፈላልጉ ሰባት የሰቆቃ አመታትን ያሳለፉት አዛውንት ያለፈው እሁድ እለት ልባቸው እንደተረጋጋ የሰማ ጎረቤት ሁሉ ቤታቸውን ከአፍ እስከ ገደፉ አጥለቅልቆት ሰንብቷል። ላገኙት ሰው ሁሉ ይችን እርኩስ መና የሚያስቀር ቴክኖሎጂ አጊኝቻለሁ እያሉ ይናገራሉ። ቀድመው በቤታቸው ለመመገብ የሚያስችላቸውን እድል የተነፈጉ አባወራዎች ሁሉ የቴክኖሎጂው ተቋዳሽ ለመሆን ጓጉተዋል። አቶ አክሊሉ ግን መፍትሄውን በቤታቸው ከሚያስነግሩ ይልቅ በእድር ጡሩንባ ወይም በራዲዮን ቢያስነግሩ ነበር አንጀታቸው የሚርሰው።
ነገር ግን የሰፈሩ ሰው ጉትጎታ ስላላፈናፈናቸው ይፋ ለማድረግ ከተሰብሳቢው መካከል እንደተወካይ የሚያገለግሉ አራት ሰዎች መርጠው መደ ቤታቸው ጓደ ይዘዋቸው ገቡ። ኩራት በተላበሰ አነጋገር «ይህ የምትመለከቱት ከብረት የተሰራ መሶብ አንድም እንስሳ የማያስገባ ከመሆኑም በላይ ቁልፉ በባለቤቴ እጅ ላይ ብቻ ይገኛል። ሲፈለግ በኩልፍ ይከፈታል ሳይፈለግ ደግሞ ይዘጋል። በመሆኑም ያች እርኩስ እንስሳ ከእኔ የተረፈውን ወዳድቆ ታገኝ የሆን እንጂ ቀድሞ የመብላቷ ጉዳይ አበቃለት» ብለው በክብ ቅርጽ የተሰራውን መሶብ እንደተዘጋ አሳዩ። አራቱ አባወራዎች አዲሱን ግኝት በአድናቆት ከተመለከቱ በኋላ ሳሎን ለተሰበሰበው ሰው ለማስረዳት በሽግድምድሞሽ እርምጃ ቀኝ ኋላቸውን ያዙ። ለተብሳቢውም አዲሱ ግኝት በሰበዝ ከሚሰራው መሶብ ይልቅ የተሻለና አይጥም ሆነ በረሮ ሊያሳልፍ እንደማይችል አጠናክረው የአይን እማኝነታቸውን በየተራ አቀነባብረው አሰሙ። 
GT
አባ አክሊሉ እና ቀድሜ እንድበላ
 
ከወደ መስኮቱ ስር የተሰበቡት ወይዛዝርቶች ግን አዲሱ ግኝት ላይ ፊታቸውን እነደማዞር አደረጉበት። የብረት ሞሰቡ ሙቀት ሲነካው እንጀራውን በፍጥነት የማሻገት እድሉ ሰፊ ስለሚሆን ምግቡን በየቀኑ ማሞቅ እነደሚኖርባቸውና ለተጨማሪ ስራ እንደሚዳርጋቸው ቅሬታ በማንሳት ማጉረምረም ጀመሩ። አቶ አክሊሉ በዚህ ጊዜ ግኝታቸው እንዳይዋደቅባቸው በመስጋት በፍጥነት ተነስተው በከፍተኛ ድምጽ ምግቡ እንዳይበላሽ ካስፈለገ ወደ ፊት የብረቱ መሶብ ማቀዝቀዣ ያለው እንዲሆን ከባለሙያዎች ጋር መነጋገር እንደሚቻል ተናገሩ። ለአሁኑ ግን ለአንገብጋቢው ችግሩ መፍትሄ መገኘቱን በማብሰር ጉዳዩን በአጭሩ ደመደሙት። መሶቡንም «ቀድሜ እንድበላ» የሚል ስም ካወጡለት በኋላ ሁሉም በየቤቱ ቢጠቀምበት አይነተኛ ዘዴ መሆኑን በመንደሩ ነዋሪ ፊት ማስታወቂያ ሰሩለት።
«ቀድሜ እንድበላ» የተሰኘው መሶብ በአቶ አክሊሉ ቤት ግልጋሎት ላይ እየዋለ ቢሆንም በተቀሩት የመንደሩ ሰዎች ቤት ግን ጥቅም ላይ ለማዋል የአዛውንቱ ባለቤት ተሞክሮ መረጋገጥ ስለነበረበት ጥቂት ቀናት ለመጠበቅ የግድ ሆኖ ነበር። የአቶ አክሊሉ ባለቤት ግን ሩህሩህ እና አይጥም እንስሳ ነው ምን በልቶ ያድራል የሚል አስተሳሰብ የያዙ በመሆናቸው የቀድሜ እንድበላን ጥቅም በሙሉ ልባቸው ወደ መንደሩ ለማስተላለፍ አልቻሉም። ደግሞም ሁል ጊዜ መሶብ እየቆለፉ እና እየከፈቱ ምግብ ማውጣት እና ማስገባት አሰልቺ መሆኑን በመረዳታቸው እስከዛሬ የኖርኩበት ነው ያገኘሁትን በመሶብ አስቀምጬ ብበላ ይሻለኛል የሚል ሃሳብ እንዳደረባቸው መገመት አያስቸግርም። እናም የአዲሱ ግኝት ጥቅም በወይዘሮዋ ማረጋገጫ ማጣት እና በአንዳንድ ቸልተኛ አባወራዎች ቀድሞ የመብላት ፍላጎት ማነስ ምክንያት ሳይስፋፋ ቀረ። አቶ አክሊሉ ግን ባለቤታቸው ላይ ባሳደሩት ጫና ምክንያት ከሚጠሏት እንስሳ በፊት በቤታቸው ቀድሞ የመብላትን ደስታ በየቀኑ ማጣጣማቸውን ቀጥለዋል። እውነት ግን እንደ አዛውንቱ ከእኛ የተረፈውን መብላት ሲገባት ከእርሷ የተረፈውን መብላታችን የሚያስቆጨን ስንቶቻችን እንሆን።

Featured post

ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል

                    የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደር...