ጠንካራ
ሰራተኛ ማህበራት አሉን?
በርካታ
ተቋማት የሰራተኛ ማህበር የላቸውም። ያላቸውም
ቢሆኑ ስለሚያከናውኑት ስራ አንዳንድ ሰራተኞች
ጥያቄ ያነሳሉ።
በርካታ
የግል ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች
ስለሚደርስባቸው ጫና እና የስራ ችግር
የሚከላከልላቸው ማህበር የላቸውም። በተለይም
በአንዳንድ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ላይ የሚሰሩ
ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል
ለማን አቤት እንደሚባል እንኳን አያውቁም።
መብታቸውን እስከምን ደረጃ እንደሚያስጠብቁ
መረጃ የላቸውም። በቦታው ያለው የሰራተኛ
ማህበርም ለሰራተኞች ተደራድሮ ጥቅም የማስከበር
ጉዳይ ላይ ደካማ ነው።
በአገሪቷ
ውስጥ የሚገኙ የሰራተኛ ማህበርም ሆነ የማህበራቱ
ኮንፌዴሬሽን ጠንካራ ናቸው ለማለት አያስደፍርም።
ለዚህም ማሳያው ለሰራተኛው ችግር ከመቅረፍ
አኳያ አርአያ ሆነው መቅረብ የቻሉ የሰራተኛ
ማህበራት ማየት አለመቻሉ ነው።
ስንቱ
ነው የሰራተኞች ቀንን /ሚያዚያ
23/
ዝግ
የስራ ቀን ስለሆነ ብቻ የሚወደው። አብዛኛው
ሰው እረፍት ስለሚኖር እንጂ ስለቀኑ ደንታ
የሚሰጠው የለም።
ጠንካራ
ሰራተኛ ማህበራት ባለመኖራቸው በተለያዩ
ተቋማት ሰራተኛው መብት ላይ ለሚፈጸሙ በደሎች
የሚከራከር እና ለውጥ የሚያመጣ አካል አይኖርም።
በመሆኑም መብት ለማስከበር ከበላይ ሃላፊዎች
ጋር የሚኖረውን ውጥረት በመፍራት እና ጥያቄ
ካነሳሁ ያለአግባብ ከስራ ልባረር እችላለሁ
ብሎ የሚሰጋ ተቀጣሪ በዝቷል። አንድ ሰራተኛ
በግሉ ከአመራሮች ጋር የመብት ጥያቄ አንስቶ
ቢከራከረ አመታት ሊወስድበት ይችላል። የቤተሰብ
አስተዳዳሪ የሆነ ሰራተኛ ደግሞ ሶስት እና
አራት አመታት ከስራ ውጭ ሆኖ የመከራከር
ኢኮኖሚያዊ አቅም ስለማይኖረው መብቱን አጥቶ
እንዲሰራ ይገደዳል። እንደዚህ አይነት ችግር
ላለመግባት ደግሞ አብዛኛው ሰራተኞች ከማኔጅመንት
አካላት ጋር እውነተኛ ያልሆነ ግንኙነት
በመፍጠር እና እያጎበደዱ መሰራትን ምርጫቸው
ያደርጋሉ። ይህም መንፈሱ የተሰበረ ትውልድ
እንዲፈጠር እያደረገ ይገኛል።
አንዳንምድ
አሰሪዎችም ጠንካራ ተከራካሪ እና ስለመብት
ጠያቂ አካል ያለመኖሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት
ሰራተኛው ላይ እንደፈለጉ ሲፈነጩ ይታያል።
በተለይም የእራሳቸው እስር ቤት ያላቸው እና
ሰራተኛን በእርግጫ እና በኩርኩመ የሚያቀዱ
እንዳሉ መታዘብ ይቻላል።ይህ ጉዳይ በተለይ
በውጭ አገራት ባለሃብቶች በሚተዳደሩ የጨርቃጨርቅ
እና ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎች ላይ በብዛት
የሚታይ ችግር ነው። ይህም በአብዛኛው ጊዜ
ሰራተኛውን ተጎጂ ሲያደርገው ይስተዋላል።
በመሆኑም በአግባቡ የሰራተኛውን መብት
የሚያስከብር ማህበር ስለማቋቋም ሊታሰብ
ይገባል። ከአሰሪዎች ጋር ስለደምዎዝዎ፣
የሥራ ሰዓት እና ሌሎች ማናቸውም የሥራ ቅጥር
ግዴታዎችና ደንቦችን በተመለከተ በማህበር
ተደራጅቶ የመደራደር አሰራር አልተለመደም።
ጥያቄ ያለው ሰራተኛ ጉዳዩነ በግሉ ይዞ
ያስፈጽማል።
የሰራተኛ
ማህበራትን ጥቅም የሚረዳ ሰራተኛ ባለመኖሩ
በተቋሙ ውስጥ ማህበሩን አደራጅቶ ለመሳተፍ
ፍላጎት የሚያሳይ ሰራተኛ እምብዛም ነው።
ሰራተኛ ማህበር ቢቋቋም ግን ጥቅሙ ለሰራተኛው
ብቻ ሳይሆን ለአሰሪዎችም ጭምር ነው። ምክንያቱም
በተደራጀ ሁኔታ በማህበር የሚነሱ የሰራተኛውን
ጥያቄዎች ማስተናገድ እና መፍታት ከተቻለ
የባንኩን እድገት ለማፋጠን ይረዳል። በግለሰብ
ደረጃ የሚመጡ ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች ማስተናገድ
ግን ከጊዜም ሆነ ከወጪ አኳያ ተመራጭ አይደለም።
በመሆኑም ሰራተኞች ብቻ ሳይሆን አሰሪዎችም
የሰራተኛ ማህበር ለማቋቋም ጥረት ማድረግ
ይኖርባቸዋል።

No comments:
Post a Comment