ከድጡ
ወደ ማጡ የሆነው የትምህርት ጥራት
በኢትዮጵያ
በግሉም ሆነ በመንግስት
የትምህርት ተቋማት
የተማረ የሰው ኃይል ለማፍራት ጥረት እየተደረገ
ይገኛል። ይሁንና የትምህርት
ጥራት
ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ
መድረሱን ባለሙያዎች ይገለፃሉ።
ሰሞኑንም በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት
በተካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የትምህርት
ጥራት ጉባኤ ላይ ባለሙያዎች
በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳብ አቅርበዋል።
የከፍተኛ
ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ ዋና
ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ ሙህዬ፣ የትምህርት
ጥራት በሚጠበቀው ደረጃ አለመሆኑን የሚያሳዩ
መረጃዎች እየተገኙ መሆኑን ይጠቁማሉ። ለዚህም
ማሳያው በ2008ዓ.ም
ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከሶስት ነጥብ ሁለት
በላይ አምጥተው የተመረቁ ተማሪዎች ላይ ፈተና
መሰጠቱን ይጠቁማሉ። ለፈተና ከተቀመጡ ስድስት
ሺ ተመራቂዎች መካከል 50
ነጥብ እና
ከዚያ በላይ ማምጣት የቻሉት ግን 24
በመቶ ብቻ
ናቸው። የተሻለ ነጥብ ያላቸው ተመራቂዎች
አነስተኛ ውጤት ካሳዩ ቀሪዎቹ በዩኒቨርሲቲ
ውጤታማነታቸው ደካማ የነበሩት ተማሪዎች
በባሰ መልኩ አነስተኛ ውጤት እንደሚኖራቸው
መገመት እንደሚቻል ያስረዳሉ።
እነደ
ዶከተር ተሰፋዬ ገለጻ፤ የተሰጠው ፈተና
በገለልተኛ አካላት የወጣ ቢሆንም አንዳንድ
ነባር ዩኒቨርሲቲዎች አነስተኛ ተመራቂዎቻቸው
ብቻ ማለፍ ችለዋል። ዪኒቨርሲቲዎቹ ለፈተናው
ያቀረቡት ተማሪዎች ቁጥር የተለያየ ቢሆንም
ፈተናውን ካለፉ ተመራቂዎች መካከል በመቶኛ
ሲሰላ ከተቋቋሙ ጥቂት ጊዜ ያስቆጠሩ አንዳንድ
ዩኒቨርሲቲዎች ከነባር ዩኒቨርሲቲዎች በላይ
ውጤት ማስመዝገባቸው ታውቋል። ይህም አዳዲስ
ዩኒቨርሲቲዎች በአግባቡ ከሰሩ ጥራት ያለው
ተማሪ ማፍራት እንደሚችሉ ያሳየ አጋጣሚ ነበር።
ይሁንና እንደ አጠቃላይ ፈተናውን ማለፍ የቻሉት
ቁጥራቸው አነስተኛ መሆኑ ሲታይ የአገሪቷነ
የጥምህርት ጥራት አደጋ ላይ መውደቁን የሚያሳይ
ሆኗል። መንግስት ለ2009
ዓ.ም
ለዩኒቨርሲቲዎች ከ36
ቢሊዮን ብር
መድቧል። የተለያዩ መመሪያዎችን በማውጣት
እና ተከታታይ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም የከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት አሳሳቢ
ደረጃ ላይ መድረሱን መገንዘብ ይቻላል።
በመሆኑም
በቀጣይ ጊዜያት የዩኒቨርሲቲ አመራሮች
ቁርጠኝነት ያስፈልጋል የሚሉት ዳይሬክተሩ፤
በተለይም ቀጥተኛ የስራ አጀንዳዎችን በመያዝ
ወደትግበራ መግባት እነደሚያስፈልገ ይጠቁማሉ።
እነደ እርሳቸው በዋናነትም የመምህራንን
የአዕምሮ ዝግጁነት ማዳበር ያስፈልጋል።
መምህራኑ በዕውቀት እና በምግባር ከተማሪው
ከፍ ብለው በመገኘት አርአያ ሆነው መቅረበ
አለባቸው። በዚህም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ
የሚገኙ መምህራን ለተማሪዎቻቸው የሞራል
ውድቀት የሚያስተላልፉ እንዳይሆኑ ጥረት
ማድረግ ይገባል። የስራ ፍቅር ያለው መምህር
በሌለበት ተቋም የሚማሩ ወጣቶች የትምህርት
ፍቅር ሊያድርባቸው አይችልም። በመሆኑም
በመጀመሪያ መምህሪ ለስራው ፍላጎት እና ፍቅር
እንዲኖረው ማድረግ የእያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ
አመራር ቀጣይ ስራ ይሆናል። በተጨማሪም
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የውስጥ ግንኙነት
መጠናከር አለበት። በዚህም ከዩኒቨርሲቲ
ፕሬዝዳንት ጀምሮ እሰከ ትምህርት ክፍል ድረስ
በመግባባት እና በጋራ የመስራት መንፈስ ሊዳብር
ይገባል። በሌላ በኩል የሚኘውን ግብዓት እና
የአካባቢውን ሃብት በማጣመር ተገቢው የሃብት
አጠቃቀም መተግበር ጥራቱ የተጠበቀ ትምህርት
ለመስጠት ዋነኛ አሰራር መሆኑን መገንዘብ
ያስፈልጋል።
ከስዊድኑ
አፕሳላ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ፕሮፌሰር ተከስተ
ነጋሽ በበኩላቸው፤ በቀድሞ ጊዜ ትምህርት
ጥራት ቢኖረውም ተገቢነት ያለው ትምህርት
እንዳልነበረ ያስታውሳሉ። በ1960ዎቹ
ላይ በአገሪቷ የተመረቁ የኮሌጅ ተማሪዎች
ስድስት ሺ ብቻ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት ተገቢው
እና ከአገሪቷ ሁኔታ ጋር የሚያያዝ ትምህርት
እየተሰጠ ሲሆን በሚሊዮኖች ተመራቂ ተማሪዎች
እንደሚገኙ ይገልፃሉ። ነገር ግን ትምህርት
በኢትዮጵያ በብዛት ላይ እንጂ በጥራት ላይ
ያልተመሰረተ ሆኗል ባይ ናቸው። በከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት
በእንግሊዘኛ ቢሆንም በአብዛኛው የመግባቢያ
ቋንቋው አማርኛ መሆኑን ማጥናታቸውን ያስረዳሉ።
«አማርኛ
በትምህርት ተቋማት በጓዳ በር ገብቶ አገልግሎት
እንዲሰጥ ከማድረግም በትክክለኛው መንገድ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስተማሪያ ቋንቋ
ተደርጎ ቢወሰድ ለትምህርት ጥራት መሻሻል
አስተዋጽኦው ከፍተኛ ይሆናል»ይላሉ።
በአዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርትና ጥናት ምርምር
ተቋም የትምህርት ዘርፍ አጥኚ የሆኑት ዶክተር
ዋና ሌቃ በበኩላቸው እንደሚገልፁት፤ የትምህርት
ጥራት መጓደል የተከሰተው የተማሪው ቁጥር
እየጨመረ በመምጣቱ ነው። ለሶስት ሰው የተዘጋጀ
ምግብ ለሃያ ሰው ቢቀርብ ጥራቱ የተጓደለ
እንደሚሆን ሁሉ የትምህርት ዘርፉ ላይ ተማሪው
ቁጥሩ ሲያድግ የማስተማሪያ ግብአቶች በዛው
ልክ ማደግ ይኖርባቸዋል። በተመሳሳይ
የአስተማሪዎች እና የመማሪያ ክፍሎች በመጣጣኝ
ሁኔታ መቅረብ ይኖርበታል። ተጨማሪ ትምህርት
ቤቶችን በየጊዜው በመስራት እና ብቁ መምህራንን
በብዛት በማፍራት ጥራቱን ማስተካከል ይቻላል።
በሌላ በኩል የተማሪውን ፍላጎት እና አስተዳደግ
ከግምት ውስጥ ባስገገባ መልኩ ትምህርቱን
በማስቀጠል የተማሪውን የመቀበል ችሎታ ማሳደግ
ይቻላል። በዚህም ጥራቱን የተሻሻለ ትምህርት
ለማቅረብ ይቻላል።

No comments:
Post a Comment