ባዮቴክኖሎጂ
እና ኢትዮጵያ
ጌትነት
ተስፋማርያም
በኢትዮጵያ
ያለው የባዮቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዕድሜ አጭር
ጊዜ ያስቆጠረ ነው። በተለይ በአፋር ክልል
ባለው የግብርና ምርምር አማካኝነት የጥጥ
ባዮቴክኖሎጂ ምርት ሙከራ በጥሩ ሁኔታ እይተካሄደ
እንደሚገኝ
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር በተለያዩ ጊዜያት
ገልጾታል።
በተለያዩ
ቴክኖሎጂዎች ላይ እንደታየው ባዮቴክኖሎጂ
ብዙ ባህላዊ,
ኢኮኖሚያዊ፣
አካባቢያዊ፣
ስነምግባር፣
ፖለቲካዊ
እና ማህበራዊ ስጋቶችን እያጋጠሙት
ይገኛል። ከባዮቴክኖሎጂ ጋር
የተያያዙ ክርክሮችን ከሌሎች ቴክኖሎጂዎች
ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ከፍተኛ ሆነው
እናገኛቸዋለን። በተለይ አንዳንድ ሰዎቸ
በባዮቴክኖሎጂ አማካኝነት የተመረቱ ምግቦችን
የሚጠቀም ትውልድ ጆሮው ትላልቅ አስተሳሰቡ
ዘገምተኛ ይሆናል የሚሉ እና የተለየያዩ
ማስፈራሪያዎች የሚሰነዝሩበት ወቅት አለ።
ባዮቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የተመረተ
የግብርና ምርት ዘርን በማኮላሸት ለመሃንነት
ያጋልጣል፣ የባዮቴክኖሎጂ
አሰራር የተከተለ ምግቦችን
የተመገበ ትውልድ ለተለያዩ የጤና እክሎች
ስለሚዳረግ ለአውሮፓውያኑ የህክምና ወጪ
መዳረጉ አይቀርም የሚል መላ ምት የሚስነዝሩ
አካላት አሉ። ይሁን እንጂ
ሁሉም ባዮቴክኖሎጂዎች በአጠቃላይ ጎጂ ናቸው ተብሎ መገመት የለበትም።.
ለአብነት
በአውሮፓ ውስጥ የሕክምና እና
የፋርማሲው ባዮቴክኖሎጂዎች ውጤቶች
ተቀባይነታቸው
ከፍተኛ ቢሆንም የምግብ እና
የእርሻ ባዮቴክኖሎጂዎች በጣም ጥብቅ ቁጥጥር
ይደረግባቸዋል።
የግብርና
ምርትና ምርታማነት ከባዮቴክኖሎጂ
ውጪ በሆኑ መደበኛ ዘዴዎች
መጠቀም የተለመደ ቢሆንም
ባዮቴክኖሎጂም ተጠቅመው ከፍተኛ ምርት
የሚያመርቱ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ስነልቦናዊ
ጫና ለቴክኖሎጂው እድገት እንቅፋት እንዳይሆን
ያሰጋል። ምክንያቱም በባዮቴክኖሎጂ ተጠቅሞ
የተመረተ ቲማቲም ላይ የሚደረገው ቁጥጥር
ከፍተኛ ከሆነ እና ገበያተኛውም ምርቶቹ
በጤናችን ላይ ችግር ያመጣል ብሎ ካሰበ አምራቹ
በመደበኛው የእርሻ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ወደማምረት
ሊመለስ እንደሚችል የእንግሊዙ ኤቲ የተሰኘ
የምርምር ጥናት ቡድን መረጃ አውጥቷል።
ዘመናዊ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ዘዴዎች እምብዛም ዋጋ አለማግኘታቸው አሳሳቢ ቢሆንም ቅሉ በሌላ በኩል የሕክምና እና የፋርማሲ እንዲሁም የፋብሪካ ግብአት የሚመረትባቸው ባዮቴክኖሎጂዎች ካላቸው በአነስተኛ ቦታ ሰፊ ምርት የማስገኘት ጥቅም ጋር ተያይዞ ተመራጭነታቸው እያደገ ይገኛል። ህንድ እና ቻይና ብቻ ካላቸው የጥጥ ማምረቻ ቦታዎች በባዮቴክኖሎጂ በመታገዝ እጥፍ ማምረት እንደቻሉ እና ከፋብሪካ ግብዓቶቻቸው አልፈው ወደውጭ ንግድ መላክ መቻላቸው ተጠቃሽ ይሆናል።
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ ቅድሚያ ትኩረት የሚደረገውው የምግብ ዋስትና እና ራስን መቻል ላይ ነው። የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ሳይንስ ደግሞ በአነስተኛ ቦታ ሰፊ ምርት ለማምረት የሚያስችል እድል የሚሰጥ አሰራር አለው። ምንም እንኳን የባዮቴክኖሎጂ ዘር ማለትም በላብራቶሪ የበለጸገ እና ከመደበኛው ዘር የተሻለ ምርት የሚሰጥ ለማድረግ በሚሊዮኖች አንዳንዴም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያስፈልጋል። ከዚህ በፊት ግን ህብረተሰቡ ስለባዮቴክኖሎጂ ያለውን አመለካከት ማቃናት እንደሚያስፈልግ ይታመናል።

ለዚህ
ስራ ደግሞ የባዮቴክኖሎጂ
ትምህርት ማስፋፋት አስፈላጊ
ነው። በተለይ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት
ስለባዮቴክኖሎጂ ጥቅም እና
አስፈላጊነት የሚያስረዱ በምስል እና በጽሁፍ
የታገዙ ትምህርቶች ለወጣቶች ማዳረስ ይገባል።
ትምህርቱም ወደባለሙያዎች እና ወጣቶቹ እየሰረጸ
ሲሄድ የቴክኖሎጂው አስፈላጊነት በእራሱ ጊዜ
ከህዝብ ጥያቄ አማካኝነት ሊመጣ የሚችልበት
እድል ይኖራል። በሌላ በኩል አምራቹን ወይም
አርሶአደሩን ባሳተፈ መልኩ ስለባዮቴክኖሎጂ
ምርቶች ጥቅም የሚያስረዳ አንድ ኮሜቴ በመንግስት
ደረጃ በማዋቀር ግንዛቤውን ማሳደግ ያስፈልጋል።
አልፎ
ተርፎም
ከባዮቴክኖሎጂው ዘርፍ ጥሩ ተጠቃሚነት ያላቸውን
አገራት ተሞክሮ ለአምራቹ በተለይም ለግብርና
ኢንቨስተሮች በማሳየት በሰፋፊ እርሻዎች ላይ
ተግባራዊ እንዲሆን መጣር ያስፈልጋል። ይህ
ሲሆን በአንድ ሄክታር ላይ ይገኝ የነበረውን
ምርት በእጥፍ እና ከዚያም
በላይ በማሳደግ የኢትዮጵያን የምግብ ፍላጎት
ማሟላት የሚያስችል ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ
ለማከናወን ይቻላል። በዚህ
ስራ ውስጥ ደግሞ ባለሥልጣኖች፣
የቴክኖሎጂ ተቋማት፣ የግብርና አካላት እና
ሌሎችም ማህበራዊ ሃላፊነት ያለባቸው ተቋማት
ሊሳተፉበት የሚገባ ጉዳይ ነው።
ይህን
አሰራር መተግበር ከተቻለ እና ዘርፉን በመንግስት
እና በግል ኢንቨስተሮች መደገፍ ከተቻለ
የባዮቴክኖሎጂ ምርቶችን ለኢትዮጵያውያን
ብሎም ለምስራቅ አፍሪካ አገራት ማቅረብ የማይቻልበት
ምንም ምክንያት አይኖርም።

Thanks for Your fruitful information,Bt is vital for our envelopment and food sustainability.
ReplyDeleteጥሩ መረጃ ነው። ባዮ ቴክኖሎጂ ብዙ አየታወቅመ በኢትዮጵያም ያለው አጠቃቀም ምን ደረጃ ላይ እነዳለ እምብዛም አይታወቅም በመሆኑምን እነደዚህ አይነት ጽሁፎች ቢበዙልን ጥሩ ነው"
ReplyDeleteWell Bt is good Tec For Developing countries,this is good kind of information that i read in your blog. Keep Doind and write more this kind of articles
ReplyDelete