Thursday, July 7, 2022

ኢሰመኮ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ብሔራዊ ሕዝባዊ ምርመራ (National Public Inquiry) በሐዋሳ ከተማ አካሄደ

 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አዘጋጅነት ነታቸውን አግባብ እና በዘፈቀደ የተነፈጉ ሰዎች መብቶች ላይ ያተኮረ፣ በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነ ብሔራዊ ምርመራ አካል የሆነውን ሕዝባዊ የአቤቱታ ቅበላ መድረክ ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በሃዋሳ ከተማ መካሄዱን አሳውቋል

ሕዝባዊ የአቤቱታ ቅበላ መድረክ ግልጽ እና ሕዝባዊ ተሳትፎ የሚደረግበትየመብቶች ጥሰቶች የደረሰባቸው ተጎጂዎች፣ ምስክሮች፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላትንዲሁም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በአንድ መድረክ በተገኙበት የሚከናወን የምርመራ ስልት መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል።


በሃዋሳ ከተማ የተከናወነው የመጀመሪያው ብሔራዊ ምርመራ ነፃነታቸውን አላአግባብ እና በዘፈቀደ የተነፈጉ ሰዎች መብቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ በዋሳ ከተማ የተካሄደው ብሔራዊ ምርመራ በይበልጥ ትኩረት ያደረገው በሕገ ወጥ እና በዘፈቀደ ነነታቸውን ተነፈጉ ሰዎች እና በተያያዙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ እንደሆነ ታውቋል።

ሕዝባዊ የአቤቱታ ቅበላ መድረኩን የመሩት የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽር ራኬብ መሰለየሲቪል፣ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጂብሪል እና የሴቶች እና ሕናት መብቶች ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ ሲሆኑ፣ ሌሎች የኮሚሽኑ አመራሮች፣ ባለሙያዎችአማካሪዎች ከዚሁ መድረክ ጋር የተያያዙ በርካታ ተግባራቶችን በማከናወን ተሳትፈዋል

በዝግጅቱ የመክፈቻ ንግግር ያሰሙት የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ “ይህ የሕዝብ አቤቱታ መቀበያ መድረክ ስልታዊ እና ተደጋጋሚ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር፣ ተገቢ እና ዘርፈ ብዙ እርምጃዎች እንዲወሰዱባቸው ለማድረግ እንዲሁም ስለሰብአዊ መብቶች በማስተማር ረገድ ውጤታማ ዘዴ እንደሆነ በሌሎች ሀገራት የታየው ተሞክሮ ተስፋ ሰጪ ነውብለዋል።

አክለውም ብሔራዊ ምርመራ የፍርድ ሂደት ሳይሆን በሰዎች ላይ የደረሰውን የመብቶች ጥሰቶች በመስማት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር መፍትሔ የሚፈለግበት መንገድ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ኮሚሽኑ በሕዝባዊ የአቤቱታ መቀበያ መድረኩ ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በመመዘን በዓለም አቀፍ አጣሪ ኮሚሽኖች ጥቅም ላይ የሚውለውን “ምክንያታዊ አሳማኝነት” ተብሎ የሚታወቀውን የማስረጃ ምዘና መስፈርትን በመጠቀም የሚሰንድና የመፍትሔ አቅጣጫ የሚጠቁሙ ምክረ ሃሳቦች ያቀርባልበማለት መርኃ ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

በመድረኩ ኢሰመኮ ከ30 በላይ ተጎጂዎችን አቤቱታና ደርሶብናል ያሏቸውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ያመጠ ሲሆንከነዚህም መካከል ያለክስ እና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በተደጋጋሚ እና ለረጅም ጊዜ የታሰሩየፓለቲካ ልዩነትን መሰረት ያደረገ” መሆኑ የተገለጸ እና ከሕግ አግባብ ውጪ እና በዘፈቀደ በተደጋጋሚ እና የተራዘመ ቅድመ ክስ እስር የተዳረጉ፣ ጭካኔ የተሞላበትና አሰቃቂ አያያዝ እንደደረሰባቸው የገለጹ፣ እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያ እና በማረሚያ ቤት ቆይታ በተደጋጋሚ ሕክምና ተከልክለው ለጤና እክል የተዳረጉ  ይገኙበታል

በዚህ ሕዝባዊ የአቤቱታ ቅበላ መድረክ የተሳተፉ ተጎጂዎች የነነት መብታችን አግባብ ተነፍጓል ያሉ ሰዎች አቤቱታ ኮሚሽኑ  ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና ለሕዝብ ማካፈል እንዲችሉ እና በቀጣይ ይህንን ዓይነቶቹ ተደጋጋሚ እና ውስብስብ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመቀነስ፣ እንዲሁም መሰል ጥሰቶች ተፈጽመው ሲገኙ ተጎጂዎች የሚካሱበት እና አጥፊዎች ተጠያቂ የሚደረጉበት ጠንካራ ሕግ፣ ተቋም እንዲሁም አራር እንዲኖር ለማድረግ ኮሚሽኑ የሚያደርገውን ጥረት አመስግነዋል፡፡

በተጨማሪም በመድረኩ የተሳተፉ የዩኒቨርስቲ ተወካዮች እና የሃይማኖት አባቶች በክልሉ ከሕግ አግባብ ውጪ እና በዘፈቀደ በተደጋጋሚ እና ስልታዊ በሆነ መልኩ የሚፈጸመውን እስር ለመከላከል ሁሉም ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸው፣ ኮሚሽኑ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርገውን ራ ለማገዝ ዝግጁ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ከተለያዩ ዞኖች እና ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የተውጣጡ  የመንግሥት ተወካዮች በበኩላቸው ይህ ዓይነቱ መድረክ በክልሉ ላሉ የሰብአዊ መብቶች ችግሮች አስፈላጊ ስለመሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡  

የመንግሥት አካላት ተወካዮቹ ለተገለጹት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት የሆኑት መልስ ያላገኙ የማንነትእና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎች መፍትሔ የሚሹ መሆኑን አውስተውየተወሰኑትን አቤቱታዎች ተቀብለው መፍትሔ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡ ለተቀሩት ቀጣይ ውይይቶችና ምርመራ እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ 

መሰል ብሔራዊ ምርመራዎች በሌሎች ክልሎችም እንደሚካሄድ የገለጹት የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ምርመራውን ተከትሎ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዴት መለየት፣ መገምገም፣ መተንተን እና በተናጠል ጉዳዮች ላይ ስልታዊ የሆኑ ባሕሪያትን መለየት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ግኝቶችን እና ምክረ ሃሳቦችን የያዘ ሪፖርት፤ የዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጨምሮ ለሚመለከታቸው የፍትሕ አካላትና በየደረጃው ለሚገኙ የመንግሥት መዋቅሮች በዝርዝር እንደሚቀርብ አስረድተዋል።

No comments:

Post a Comment

Featured post

ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል

                    የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደር...