Saturday, December 9, 2017
Friday, December 8, 2017
የኤሌክትሪክ ፍጆታ ስሌት ልዩነት አለውን?
አቶ
መንግስቱ አለሙ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ
ናቸው። በመኖሪያ ግቢያቸው ውስጥ አንድ
አነስተኛ የፍራፍሬ መሸጫ ሱቅ እና አምስት
መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ። የፍራፍሬ መሸጫ ሱቋን
ገንብተው ካከራዩ አስር ወራት የተቆጠረ ቢሆንም
ከሶስት ወራት ወዲህ ግን የኤሌክትሪክ ወጪያቸው
እያየለ መምጣቱን ይናገራሉ። በተለይም ከአራት
እና አምስት ወራት በፊት ይከፍሉ የነበረው
500 ብር
ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ በተከታታይ
ለሶስት ወራት ከእጥፍ ላይ 1500
ብር የሚጠጋ
ገንዘብ አስወጥቷቸዋል። ለንግድ ቤቱ እና
ለመኖሪያ ቤቶቹ የሚጠቀሙበት አንድ ቆጣሪ
ቢሆንም የክፍያ ጭማሪውን ምክንያቱን ለማወቅ
ይጥራሉ። በተከራዮች ከፍተኛ ፍጆታ የተከሰተ
መሆኑን ለማጣራትም ሌት ተከን ቢታትሩም ምንም
አይነት የአጠቃቀም ለውጥ በተከራዮቻቸው ላይ
ሊያገኙ አልቻሉም።
ጉዳዩን
ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲዘዋወሩ ግን በግቢያቸው
ውስጥ አንድ የንግድ ሱቅ በመኖሩ ምክንያት
የኤሌክትሪክ ፍጆታ አቆጣጠሩ ከመደበኛ መኖሪያ
ቤት ወደ ንግድ ቤት ታሪፍ መቀየሩ ይነገራቸዋል።
ከሶስት ወራት በፊት ጀምሮ በቆጣሪ አነባበብ
ላይ የተደረገው የአሰራር ለውጥ በእያንዳዱ
የንግድ ቤት ያለው ግለሰብ ላይ የሚደረግ
አሰራር መሆኑም ይነገራቸዋል። አቆጣጠሩ
የተቀየረውም ቆጣሪ አንባቢዎች ባደረሱት
መረጃ መሰረት መሆኑን እና ቀደም ብሎ ንግድ
ሱቁ እንደተከፈተ ቢታወቅ ደግሞ የታሪፍ ቅያሪው
ከአስር ወራት በፊት መቀየር እንደነበረነት
ይነገራቸዋል።
ነገር
ግን አቶ መንግስቱ ለአንድ ንግድ ቤት ተብሎ
ቀሪዎቹ አምስት መኖሪያ ቤቶች በታሪፍ አሰራሩ
ወደ ንግድ ቤት የተጠቃለሉበት ሁኔታ ግርታን
ፈጥሮባቸዋል። እንደ እርሳቸው ተመሳሳይ
ችግር ያለባቸው የተለያዩ የንግድ ቤት የያዙ
መኖሪያ ቤት ባለቤቶችን አነጋግረው ንግድ
ቤት ላይ የቆጣሪ አነባበቡ የተለየ ስለሚሆን
ከመኖሪያ ቤት ተመሳሳይነት ላለው የኤሌክትሪክ
ፍጆታ በመጠን ከፍ ያለ ክፍያ መፈጸም የተለመደ
መሆኑ ይነገራቸዋል።
ወይዘሮ
እስከዳር አሊ ደግሞ አንድ መኖሪያ ቤት ያላቸው
ቢሆንም በግቢያቸው ውስጥ ሁለት ንግድ ቤቶች
አከራይተዋል። ንግድ ቤቶቹን ያከራዩት ከሁለት
አመታት በፊት ቢሆንም የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን
የሚከፍሉት በካርድ በሚሰራ የቆጣሪ መሳሪያ
በመሆኑ ተከራዮቻቸው ወጪውን ይሸፍናሉ።
በመሆኑም በተከራዮች ለሚሞላው የኤሌክትሪክ
ክፍያ መጠን መጨመርና መቀነስ አሳስቧቸው
አያውቅም። ነገር ግን ተከራዮቻቸው የፍጆታ
ክፍያ መጨመር ላይ ቅሬታ አንስተው ስለማያውቁ
በእርሳቸው ስም በተመዘገበው ቆጣሪ ምክንያት
አድርገው በኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽህፈት
ቤት ቀርበው ጥያቄ አቅርበው አያውቁም።
የአቶ
መንግስቱን ቅሬታ ሲሰሙ ግን 'አዲስ
አሰራር ተዘርግቶ ይሆን'
የሚል ሃሳብ
ገብቷቸዋል። ተከራዮችም ይህን አይነት ያልተጣራ
ወሬ ጆሯቸው ከደረሰ በኋላ ወጪውን ለማካካስ
በሚል የሽያጭ እቃዎቻቸው ላይ ጭማሪ ስለማድረጋቸው
ማጣራት እስካልተደረገ ድረስ ማንም እርግጠኛ
መሆን ይከብደዋል።
የአሰራር
ሁኔታውን ለማጣራት ወደ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
አገልግሎት የኮሚዩኒኬሽን
ዳይሬክተር አቶ
ገብረእግዚያብሄር ታፈረ ደወልን። እርሳቸው
እንደሚናገሩት፤ በአገሪቷ ውስጥ ምንም አይነት
የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ጭማሪ የለም።
የሚቀየር የክፍያ አገልግሎት አሰራር ቢኖር
እንኳን በመንግስት ደረጃ ፍቃድ ተደርጎበትና
ለህብረተሰቡ በይፋ ተገልጾ እንጂ በድብብቆሽ
የሚከናወን ጉዳይ አይኖርም። በኢትዮጵያ
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ ዝቅተኛ በሚባል
ዋጋ እየቀረበ ይገኛል። ደንበኞቹ የሚያነሱት
ጉዳይ ከአጠቃቀም ለውጥ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ
እና ከቆጣሪ ብልሽት ጋር ተያይዞ የተከሰተ
ስለመሆኑ በቅድሚያ ማጣራት ያስፈልጋል።
ነገር ግን በመኖሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ የንግድ
ቤት ያለው ሰው በጋራ ለሚጠቀምበት ቆጣሪ
እንዲከፍል
የሚጠየቀው የአገልግሎት ክፍያ ለመኖሪያ ቤት
ከሚጠየቀው ጋር ሲነጻጸር ልዩነት አለው።
ለቤት
አገልግሎት የሚጠቀሙት ላይ እስከ 50
ኪሎ
ዋት ኤሌክትሪክ ፍጆታ ድረስ ሲገለገሉ በኪሎ
ዋት 0 ነጥብ
273 ሳንቲም
እንደሚጠየቅ ይጠቁማሉ።
ከ50
ኪሎ
ዋት በላይ ሲጨምር ግን የክፍያ ስሌቱ የመጨመር
አዝማሚያ /progressive/
ባህሪ
እንዳለው ያስረዳሉ።
የንግድ ቤቶች ላይ ደግሞ እስከ 50
ኪሎ
ዋት ኤሌክትሪክ ፍጆታ ድረስ ሲገለገሉ 0
ነጥብ
6088 ሳንቲም
እንዲከፍሉ ይደረጋል። ፍጆታው በንግድ ቤቶች
ላይ ከ50
ኪሎ
ዋት ሲበልጥ ግን የክፍያ ስሌቱ አጨማመር
አነስተኛ /semi
progressive/ እየሆነ
እንደሚሄድ ይገልፃሉ።
እንደ
አቶ ገብረእግዚአብሔር ማብራሪያ፤ የመኖሪያ
ቤታቸው ውስጥ በሚገኝ የንግድ ቤት ምክንያት
የኤሌክትሪክ ክፍያ ስሌቱ ጨምሯለ የሚል ቅሬታ
ያላቸው ሰዎች ከዚህ ቀደም ሲሰራበት የቆየ
ስሌት በመሆኑ ምንም የተፈጠረ አዲስ አሰራር
አለመሆኑን ማወቅ ይገባቸዋል። ለቤት አገልገሎት
ሲሰራበት የነበረው የግለሰቦች ቆጣሪ የንግድ
ቤት በመክፈታቸው ምክንያት ወደ ንግድ እንዲዞር
ይደረጋል። ነገር ግን ለንግድ ቤቱ እና ለመኖሪያ
ቤታቸው ባስገጠሙት አንድ ቆጣሪ ምክንያት
ሁሉም ክፍያ በንግድ ቤት የቆጣሪ ስሌት
ተጠቃሎብኛል የሚል ቅሬታ ያላቸው ሰዎች በህጋዊ
መንገድ የተለያየዩ ቆጣሪዎችን በማስገጠም
መጠቀም ይኖርባቸዋል። ለንግድ ቤቱ እና
ለመኖሪያ ቤታቸው የተለያየ ቆጣሪ ከፋፍለው
የሚጠቀሙ ከሆነም የመኖሪያ ቤቶቹን ኤሌክትሪክ
ክፍያ በአነስተኛ ታሪፍ ሊጠቀሙ ይችላሉ።
የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ ፍርድ
የኦሮሚያ
ጸረ ሙስና ኮሽን በከባድ የሙስና
ወንጀል ክስ
መስርቶባቸው የነበሩት በምክትል ፕሬዝዳንት
ማዕረግ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ
ኃላፊ አቶ ዘላለም
ጀማነህ የስድስት
አመት ጸሁ እስራት ተፈረደባቸው።
በፊንፊኔ
ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ትናንትና በዋለው ችሎት በምክትል ፕሬዚዳንት
ማዕረግ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ
ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ እና ቤተሰባቸውን
ጨምሮ በ12
ሰዎች
ላይ በተመሰረተው ክስ ላይ ብይን ሰጥቷል።
አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ጀማነህ ላይ ምንጩ
ያልታወቀ ሃብት በማፍራት፤ ያልታወቀ ሃብትን
እውነተኛ በማስመሰል መሞከር እና ሃሰተኛ
የመንግስት ሰነዶችን ህጋዊ በማስመሰል ጥቅም
ላይ ማዋል በሚሉ ሶስት ክሶች ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ
አድርጓቸዋል። በተከሳሹ ላይም የስድስት
አመት ጸኑ እስራት እና የ11
ሺ
ብር ቅጣት አስተላልፏል። ለቅጣት ማቅለያነት
ከተቀመጡ ምክንያቶች ውስጥ ተከሳሹ ከዚህ
በፊት ከማንኛውም ወንጀል ነጻ እንደነበሩ
እና በመንግስት ካፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያገለገሉ
እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች እንዳለባቸው
የህክምና ማስረጃ ማቅረባቸውን በፍርድ ወቅት
ተገልጿል።
በፍርድ
ብይኑ መሰረት፤ ከከባድ ሙስና ወንጀሉ ጋር
በተያያዘ በአዲሰ አበባ ኮልፌ ክፍለ ከተማ
የሚገኝ መኖሪያ ቤት እና መኪና እንዲሁም
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝ
ኮንዶሚኒየም ቤትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ እና በአዋሽ ባንክ የነበሩ የተከሳሽ
ገንዘብ ወደ መንግስት ገቢ እንዲሆኑ ተወስኗል።
ፍርድ
ቤቱ በአቶ ዘላለም የቀድሞ ባለቤትና በሁለተኛ
ተከሳሽ ላይ የቅጣት ማቅለያዎችን በመመልከት
በነጻ አሰናብቷቸዋል። አንደኛ እና ሁለተኛ
ተከሳሾች አሁን ላይ የተፋቱ መሆኑን ጠቅሶ
ሁለተኛ ተከሳሽ ልጆቻቸውን ለማሳደግ
በእናትነታቸው ሃላፊነት እንዳለባቸው በመጠቆም
በነጻ ሲለቀቁ እስከ ሁለት አመት ድረስ በማንኛውም
ወንጀል ተሳታፊ ሆነው ከተገኙ ግን አምስት
አመት የሚደርስ እስራት እንደሚጸናባቸው
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ተገልጿል። ከሶስተኛ
እስከ አምስተኛ እንዲሁም ስምንተኛ እና ዘጠነኛ
ተከሳሾን በተመለከተ እስከ አምስት አመት
በሚደርስ የተለያየ የእስር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
የክልሉ
ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በኦሮሚያ
ክልል ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ከስልጣናቸው
የተነሱት እና በስተኋላም በሙስና ወንጀል
የታሰሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ እና ቤተሰቦቻቸውን
ጨምሮ 12
ግለሰቦች
ላይ 14
ክሶችን
መስርቶ ከአንድ አመት በላይ መረጃዎች ሲጣሩ
ቆይተዋል።
የቀድሞው
የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የክልሉ
የግብርና ቢሮ ኃላፊ ሰኔ 2
ቀን
2008
ዓ.ም
አስቸኳይ ስብሰባ ባደረገው የጨፌ ኦሮሚያ
ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ከተደረገ
በኋላ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ የሚታወስ
ነው። የክልሉ መንግስትና ድርጅት አመራር
በነበሩበት ወቅት የመንግስት እና የህዝብ
ንብረቶችን በስማቸው በማዞር፣ በህግ ወጥ
መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ
መያዝ እና ከገቢ በላይ ሀብት ማፍራት የመሳሰሉትን
ከክሶቹ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
ሁለት ጊዜ የደረቀው ሃይቅ - ሐሮማያ
ሐይቆች በተለያየ
ምክንያት ይደርቃሉ። በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው
የሐሮማያ ሐይቅ ደግሞ ከሌሎች ውሃ አካላት
በተለየ ሁናቴ ሁለት ጊዜ ደርቋል። ለዚህ
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ሐይቁን መልሶ
ለማግኘት ምን ያስፈልጋል?
በሐሮማያ
ዪኒቨርሲቲ የአግሮኖሚ መምህር ዶክተር የሆኑት
አብዱለጢፍ አህመድ ፤ ሐሮማያ ሃይቅ ሰባት
ኪሎሜትር የሚሸፍን ርዝመት እና 14
ሜትር ጥልቀት
የነበረው ሃይቅ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ሜዳ
ሆኖ ውሃው ሊደርቅ የቻለው በአንድ ጊዜ የመጣ
ክስተት አለመሆኑን ይናገራሉ። ከጊዜ ወደ
ጊዜ ምህረት የለሽ እና ቁጥር የሌለው የውሃ
ብዝበዛ ሲካሄድበት ቆይቶ ከአምስት አመታት
በፊት ሃይቁ መድረቁን ይገልጻሉ። በአካባቢው
ያሉ አርሶ አደሮች በርካታ ውሃ ከሃይቁ እየተጠቀሙ
ውሃው ሲቀንስ እና ሃይቁ በደለል ሲሞላ የእርሻ
ቦታቸውን ወደ ሃይቁ እያስጠጉ መሄዳቸውንም
ያስረዳሉ። በመቀጠልም የሃይቁን ድንበር
ጥሰው ደለሉ ላይ ምርት በመጀመራቸው ውሃ
እንዳይተኛ አይነተኛ ምክንያት መሆኑን
ይጠቁማሉ።
እንደ
መምህር አብለጢፍ ገለጻ፤ በቀጣይ ህብረተሰቡን
በማስተባበር እና ስለ ውሃ አጠቃቀም ያላቸውን
እውቀት በመጨመር የሚገኘውን ውሃ በቁጠባ
እንዲጠቀሙ ማድረግ ይገባል። አርሶአደሮቹም
ለእርሻ ስራቸው የጠብታ መስኖ እንዲጠቀሙ
ጥብቅ እገዛ ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚህ
በተጨማሪ አምራቾቹ በእያንዳንዳቸው እርሻ
ውስጥ የሚቆፍሩትን የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ
በማስቀረት በአንድ ጉድጓድ ለጋራ እንዲጠቀሙ
በማድረግ የከርሰምድር ውሃውን ብክነት መቀነስ
ይገባል። ይህም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጣው
ጎርፍ አሰባስቦ ሃይቁ ቦታ ላይ እንዲቆይ
ለማድረግና ተከማችቶ የቆየ የመሬት ውስጥ
ውሃ ወደ ላይኛው የመሬት አካል እንዲወጣ
ለማድረግ ያግዛል። ይህ ስራ በቀጣዮቹ አመታት
በቁጥጥር ከተሰራ ሃይቁ መልሶ የማይመጣበት
ምክንያት የለም። የሃይቁን መልሶ መሙላት
የሚወስደውን ጊዜ ለመገመት ግን የዝናብ ሁኔታው
ወሳኝነት አለው። ድርቅ ተደጋግሞ የሚከሰት
ከሆነ የሃይቁ መፈጠር ሊራዘም ይችላል።
የሐሮማያ
ተፋሰስ ልማት መልሶ የማልማት ቴክኒክ አስተባባሪ
አቶ ተፈሪ ታደሰ እንደሚናገሩት፤ ለሐረማያ
ሃይቁ መጥፋት በመንስኤ የሆነው ዋነኛ ምክንያቱ
የአካባቢው መሬት መራቆት ነው። በተጨማሪም
የመሬት አጠቃቀም ለውጥ ለውሃው መመናን
አስተዋጽኦ አድርጓል። ለማሽላ፣ ለጥራጥሬ
እህሎች እና ለፍራፍሬ የሚውል የነበረ የአካባቢው
መሬት ለጫት ምርት እየዋለ ይገኛል። የምርት
አይነቱ በአንደ ጊዜ በመቀየሩም ምክንያት
የአፈር እጥበቱ በከፈተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
በአካባቢው የሚሸረሸረው አፈር ደግሞ በቀጥታ
ወደ ሃይቁ በመግባት ከተቀመጠ በኋላ የሃይቁን
ውሃ ቦታ ይዟል። በመሆኑም በአሁኑ ወቅተ
በቦታው ላይ ደለል እንጂ የውሃ አካል አይገኝም።
ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው እየተስፋፋ የመጣው
የጫት ተክል ለማደግ በርካታ ውሃ የሚያስፈልገው
በመሆኑ የሃይቁን ውሃ በስፋት ጥቅም ላይ
እንዲውል በር ከፍቷል። ይህም የሃይቁን ውሃ
በማመናመን እንዲደርቅ ምክንያት ሆኗል።
ከሶስት
አመታት በፊት የደረቀው የሃሮማያ ሐይቅ መልሶ
ውሃ እንዲይዝ ለማድረግ ፕሮጀክት ተነድፎ
ነበር። በሃይቁ አካባቢ የሚገኘው የላይኛው
የተፋሰስ ክፍል ላይ የአፈር እና ውሃ እቀባ
ስራ ዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በዚህ ውስጥ
አካባቢውን መልሶ የማልማት እና የውሃ ሃብት
አጠቃቀም ላይ ውጤታማ ስራዎች በተወሰነ ደረጃ
ማከናወን ተችሏል። የመጀመሪያው ሃይቅ በተፈጥሮ
የነበረና እና ጥልቀት ያለው ሲሆን ከደረቀ
በኋላ መልሶ ለማልማት በተደረገው ጥረት
አነስተኛ ውሃ በክረምት ወቅት እንዲይዝ ተደርጎ
ነበር። ነገር ግን ያለው የውሃ አጠቃቀም
የተዛባ በመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲደርቅ
አስተዋጽኦ አድርጓል። መልሶ ውሃ እንዲይዝ
ለሚደረገው ጠረትም ውሃውን ከአቅሙ በላይ
የመጠቀም ልምድ ሊስተካከል ይገባል። በመሆኑም
ዋነኛው መፍትሄ የአካባቢውን የጫት ምርት
በሌሎች ተችሎች በመቀየር የተመጣጠነ የውሃ
አጠቃቀም ስርዓት እንዲስፍን ማድረግ ይገባል።
በዚህም ከስድስት መቶ ሄክታር በላይ የሆነውን
የሃይቁን ይዞታ መልሶ በማልማት ውሃ እንዲዝ
ማድረግ ይቻላል። በአግባቡ ከተሰራም በአምስት
እስከ አስር አመታት ባሉት ጊዜ ውስጥ ሃይቁን
መልሶ ማግኘት የሚቻልበት እድል ሰፊ ነው።
በአካባቢው የሚገኘውን ጥንቄ ሃይቅን እንዲሁም
ሃረጂቶ የተባሉ አነስተኛ ሃይቆች ተፈጥረዋል።
«ማንኛውም
ተክል ውሃ ይፈልጋል ጫት ስለተተከለ ብቻ
ከፍተኛ ውሃ ከሃይቁ ላይ ተወስዷል ብሎ መደምደም
አይቻልም»
የሚሉት
ደግሞ በእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር
የተፈጥሮ ሃብት ልማት አጠቃቀም ዳይሬክተር
አቶ ተፈራ ታደሰ ናቸው። ጫት ከፍተኛ ውሃ
ስለሚወስድ ለሃይቁ መድረቅ አስተዋጽኦ አለው
ለማለት ጥናት እንደሚያስፈልግ
ይገልጻሉ። ነገር ግን የሃይቁ ውሃ የሚከማችበት
ጉድጓዳማ ስፍራ በተለያዩ ደለሎች እየተሞላ
ሲሄድ ውሃው የመያዝ አቅሙ እንደሚቀንስ
ይገልጻሉ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከሐይቁ
ዙሪያ የሚገኘው የላይኛው ተፋሰስ አካባቢ
ለአፈር መከላት የተጋለጠ በመሆኑ እንደተከሰተ
ያስረዳሉ። በመሆኑም የተፋሰሱን የእጽዋት
ሽፋኑን በማሳደግ እና በመንከባከብ በጎርፍ
ወቅት አፈር ተሸርሽሮ ወደ ሃይቁ እንዳይገባ
መጣር ዋነኛ ተግባር
መሆን እንደሚገባው
ይጠቁማሉ።
እንደ
አቶ ተፈራ ገለጻ፤ የአካባቢው
ህብረተሰብ የአፈር መሸርሸርን የሚከላከሉ
የግብርና ዘዴዎችን እና ቴክኖሊጂዎችን
እንዲጠቀም
ማበረታታት
አስፈላጊ ነው።
ይህ ከተከናወነ ሃይቁ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጎድጓዳማው
አካባቢ በአፈር እየተሞላ ወደ ዝርግ መሬት
የሚቀየርበትን ሂደት ያስቀረዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ወደ ሜዳነት የተቀየረውን
እና ውሃ ለመያዝ አስቸጋሪ የሆነውን
ደለላላ ቦታ ለማስተካከል
በተለያዩ አማራጮች ከሃይቁ
ቦታ ላይ
ደለሉ ቦታ እንዲለቅ
ማድረግ ያስፈልጋል። ይህም በዝናብ እና በጎርፍ
የሚገኘውን ውሃ እንዲጠራቀም
ቦታ ይከፍታል።ሁለት
ጊዜ የደረቀ ሐይቅ
Subscribe to:
Comments (Atom)
Featured post
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደር...
-
ባህል የአንድን ማህበረሰብ የእምነት ፍልስፍና ጥበብ የአስተሳሰብ እሴቶች ያካተተ ነው። ውስብስቡ እሳቤ በቁሳዊ ባህሎቹ እና ልማዶቹ በማህበራዊ ግንኙነቶቹ እና በተለያዩ ትውፊቶቹ አማካኝነት ተጨባጭ አሰራር ይኖረዋል።...
-
ድካም ድካም ያላቸው « ዘመን ተሻጋሪዋ እናት » Abebech Gobena <<Africa's Mother Theresa>> ሴትየዋ ጠንካራ ናቸው። ውልደታቸው በ 1938 ዓ . ...
-
እንኳን ሰው ይቅርና እግር እና እግር ይጋጫል እንደሚሉ አበው በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ህይወት አለመግባባት ሊከሰት ይችላል። ግጭት ካልበረደ ደግሞ አካላዊ፣ስነልቦናዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ብቻ ሳይሆን ክቡር የሆነዉን የሰ...
-
By Getnet Tesfamariam The issue of universal food security is at the heart of many of the ethical issues related to GM technol...
-
ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በ 1917 ዓ . ም ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትን ሲመርቁ እንዲህ ብለው ነበር የሀገሩን ትምህርት ጽህፈት ቋንቋ እንደሚገባው የማያውቅ የውጭውን እማራለሁ የሚል ምሳሌው ቀዛፊ እንደሌለው ታንኳ ነው...
-
Domadol Addicted drug in Ethiopian Schools ሱስ ም እንደፋሽን ተከታዩ በዝቷል :: ትውልድ ም እንደቀልድ ለሙከራ በጀመረው ስህተት አየተጠለፍ በሱስ ሰንሰለት ታስሮ መውጫ ቀዳዳ አጥቶ ...
-
ነቀምቴ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ትገኛለች። እንደ አካባቢው አባቶች የስሟ ትርጓሜ «የታጨች» እንደማለት ነው። በከተማዋ ከሚገኙ መስህቦች ውስጥ ደግሞ ባለ ግርማ ሞገሱ እና ሁለት ነጥብ አምስት...
-
በመኪኖች ጭስ እንደታፈኑ ውለው ከሚያድሩት የአዲስ አበባ ሃውልቶች እና ቅርሶች መካከል የሚመደበው የ አፄ ቴዎድሮስ አደባባይ ዙሪያ ገባውን በላስቲክ ሸራ ተሸፍኗል። አይን የለውም እንጂ አይን ቢኖረውማ እዚህም እዚያ...
-
ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደውን የአስፋልት መንገድ ይዘው ሲጓዙ ፍቼ፣ ደብረ ጉራቻ፣ጎሀ ጽዮን ከተሞችን አልፈው የዓባይን በረሃ ካጠናቀቁ በኋላ የደጀን ከተማን ያገኛሉ፡፡...
-
የኪነጥበብ ስራዎች ልክ እንደ መስታወት በዘመናቸው ያለውን ከሃድ ቁልጭ አድረግው ያሳያሉ ። መስታወቅ ጉድፍንም ውበትንም በግልጽ ፊት ለፊት እነደሚያቀርብልን የሥነጽሁፍ ስራዎችም እነዲሁ ናቸው። እ ን ደ ሐዲስ አለ...

