Friday, December 8, 2017

የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ ፍርድ


የኦሮሚያ ጸረ ሙስና ኮሽን በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው የነበሩት በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ የስድስ አመት ጸሁ እስራት ተፈረደባቸው።
በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንትና በዋለው ችሎት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ እና ቤተሰባቸውን ጨምሮ በ12 ሰዎች ላይ በተመሰረተው ክስ ላይ ብይን ሰጥቷል። አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ጀማነህ ላይ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት፤ ያልታወቀ ሃብትን እውነተኛ በማስመሰል መሞከር እና ሃሰተኛ የመንግስት ሰነዶችን ህጋዊ በማስመሰል ጥቅም ላይ ማዋል በሚሉ ሶስት ክሶች ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ አድርጓቸዋል። በተከሳሹ ላይም የስድስት አመት ጸኑ እስራት እና የ11 ሺ ብር ቅጣት አስተላልፏል። ለቅጣት ማቅለያነት ከተቀመጡ ምክንያቶች ውስጥ ተከሳሹ ከዚህ በፊት ከማንኛውም ወንጀል ነጻ እንደነበሩ እና በመንግስት ካፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያገለገሉ እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች እንዳለባቸው የህክምና ማስረጃ ማቅረባቸውን በፍርድ ወቅት ተገልጿል።
በፍርድ ብይኑ መሰረት፤ ከከባድ ሙስና ወንጀሉ ጋር በተያያዘ በአዲሰ አበባ ኮልፌ ክፍለ ከተማ የሚገኝ መኖሪያ ቤት እና መኪና እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ኮንዶሚኒየም ቤትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአዋሽ ባንክ የነበሩ የተከሳሽ ገንዘብ ወደ መንግስት ገቢ እንዲሆኑ ተወስኗል።
ፍርድ ቤቱ በአቶ ዘላለም የቀድሞ ባለቤትና በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ የቅጣት ማቅለያዎችን በመመልከት በነጻ አሰናብቷቸዋል። አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች አሁን ላይ የተፋቱ መሆኑን ጠቅሶ ሁለተኛ ተከሳሽ ልጆቻቸውን ለማሳደግ በእናትነታቸው ሃላፊነት እንዳለባቸው በመጠቆም በነጻ ሲለቀቁ እስከ ሁለት አመት ድረስ በማንኛውም ወንጀል ተሳታፊ ሆነው ከተገኙ ግን አምስት አመት የሚደርስ እስራት እንደሚጸናባቸው ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ተገልጿል። ከሶስተኛ እስከ አምስተኛ እንዲሁም ስምንተኛ እና ዘጠነኛ ተከሳሾን በተመለከተ እስከ አምስት አመት በሚደርስ የተለያየ የእስር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ከስልጣናቸው የተነሱት እና በስተኋላም በሙስና ወንጀል የታሰሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ 12 ግለሰቦች ላይ 14 ክሶችን መስርቶ ከአንድ አመት በላይ መረጃዎች ሲጣሩ ቆይተዋል።
የቀድሞው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ሰኔ 2 ቀን 2008 . አስቸኳይ ስብሰባ ባደረገው የጨፌ ኦሮሚያ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ከተደረገ በኋላ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ የሚታወስ ነው። የክልሉ መንግስትና ድርጅት አመራር በነበሩበት ወቅት የመንግስት እና የህዝብ ንብረቶችን በስማቸው በማዞር፣ በህግ ወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ መያዝ እና ከገቢ በላይ ሀብት ማፍራት የመሳሰሉትን ከክሶቹ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

Featured post

ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል

                    የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደር...