በኢትዮጵያ
ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ አባል እና
የጦር አርበኛዋ ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ አፄ
ኃይለስላሴ ፊት ቀርበዋል። በልባቸው ያሰቡት
እውን እንዲሆን ጃንሆይን እያነጋገሩ ነው።
ወይዘሮዋ ለድሆች እና ለአካል ጉዳተኞች የሚሆን
ቦታ እፈልጋለሁ እና ይፈቀድልኝ፤ ቦታው ላይም
የእደጥበብ ውጤቶች ለማምረት የሚያስችል
ስልጠና ልሰጥበት ስለሆነ ቦታ ተፈልጎ አዲስ
አበባ ላይ ይሰጠኝ ብለው ይጠይቃሉ። ለቅዱሱ
ዓላማ ንጉሱ ቦታውን ይፈቅዳሉ፤ የተፈቀደውም
ቦታ አፍንጮበር አካባቢ የሚገኝ አንድ ግቢ
ነበር።
![]() |
| ስንዱ ገብሩ እና አጼ ኃይለስላሴ ፊት ለፊት |
የጎንደር
ከንቲባ የነበሩት የአቶ ገብሩ ደስታ ልጅ
በሁኔታው ተደስተው አፍንጮ በር ወደሚገኘውና
አሁን ላይ መስማት የተሳናቸው ወጣቶችን መደበኛ
ትምህርት ቤትነት ወደተቀየረው ስፍራ ያመራሉ።
የአርበኛው መሸሻ ገብሩ እና የታዋቂዋ የሙዚቃ
ቀማሪና የክላሲካል ፒያኖ ተጫዋች እማሆይ
ጽጌ ማርያም ወይም የውብዳር ገብሩ እህት
የሆኑት ወይዘሮ ስንዱ አስር የሚሆኑ ወጣቶችን
በግቢው ሰብስበው በ1959
ዓ.ም
ሀ ብለው ስራቸውን ጀመሩ። ከመደበኛ ስራቸው
እና ከድርሰት ስራቸው ላይ እየቀነሱ በሚያገኟት
ሰዓትም ከአካል ጉዳተኞች እና ድሃ ሆነው
የአካል ጉዳት ከሌለባቸው አስር ወጣቶችን
ስለዕደጥበብ ሙያዊ ስልጠና እንዲያገኙ
ያደርጋሉ።
ይህ
ወሬ እና የስልጠናው ጥቅም በመላ ከተማዋ
በመዳረሱም የዕደጥበብ ስልጠናውን ፈላጊዎች
ቁጥር ከአቅማቸው በላይ ሆነ። በመሆኑም ሰፊ
ቦታ በማስፈለጉ የሚተባበር ሰው ይፈለጋል።
በወቅቱም ሽሮሜዳ አካባቢ አንድ አዛውንት
ልጃቸውን ሊድሩበት ያዘጋጁትን ግድግዳውም
ጣሪያውም ቆርቆሮ የሆነ አዳራሽ ለዕደጥበብ
ሰልጣኞች በመፍቀዳቸው 405
ሰዎች
ለስልጠናው ዝግጁ ሆኑ። አፄ ኃይለስላሴ በይፋ
የወይዘሮ ስንዱን መልካም ስራ ለመመረቅ
በ1960
ዓ.ም
ወደ ሽሮሜዳው አዳራሽ አመሩ።
በወቅቱም
ንጉሱ የዕደጥበብ ውጤቶች እዚህም እዚያም
ተሰርተው ተሰናድተው ሲያዩም በመደሰታቸው
የዕደጥበብ ስልጠናው ቦታን «የችግራችን
መርጃና ማቋቋሚያ»
የሚል
ስያሜ ሰጡት። ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ደግሞ
በወይዘሮ ስንዱ የተቋቋመው የስልጠና ማዕከል
ወደ ሀገር ጥበብ ማደራጃ ድርጅትነት ተቀይሮ
መገናኛ ከእስራኤል ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው
ቢሮው የእዮቤልዩ በዓሉን ሰሞኑን አክብሯል።
ዛሬም ድረስ አካል ጉዳተኞች እና ገቢያቸው
አነስተኛ የሆኑ አካል ጉዳተኛ ያልሆኑ ዜጎች
ውብ ዕደጥበባትን ማምረታቸውን ቀጥለዋል።
አቶ
አለማየሁ ምስጋናው አይነስውር ቢሆኑም
አዕምሮዋቸው ጥበብን ቀስሟልና በዲዛይናቸው
ያማሩ ስጋጃ ምንጣፎችን እያመረቱ በየቤቱ
እና በየቤተመንግስቱ ደጃፍ ላይ የጥበብ
አሻራቸውን እያሳረፉ ይገኛል። ለእርሳቸው
ስጋጃ ማዘጋጀት የስራ ምድባቸው እና ገቢያቸው
ብቻ ሳይሆን መስራት እንደሚችሉ ለዓለም
ያሳዩበት የህይወት መንገድ ነው። በዲዛይናቸው
ያማሩ ውብ ምንጣፎችን ሲመለከቱ አይደለም
አይነስውር አይናማውም ቢሆን ሊሰራው ይከብዳልና
እንዴት ጥልፎቹን አውቀው በስጋጃው ላይ
ተጠበቡባቸው?
ስል
ጥያቄዬን አቀረብኩላቸው። ስጋጃውን ሊሰሩ
ሲዘጋጁ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የዲዛይን መሪ
የሆኑ አይናማ ሰዎች እንደሚያግዟቸው አጫወቱኝ።
«ዶርማት»
የሚባለውን
የስጋጃ አይነት ማለትም ጎኑ 50
ሳንቲሜትር
ቁመቱ ደግሞ 90
ሳንቲ
ሜትር የሆነውን ምንጣፍ ግማሹን
መስራት እንደሚችሉና በረዳቶቻቸው አማካኝነት
በሚሰጣቸው የቁጥር ኮድ እየታገዙ ዲዛይኑን
እንደሚያሳምሩት አስረዱኝ። ድር እየተከረረ
በቁጥር አንድጊዜ ፣ ሁለት ጊዜ ና ሶስት ጊዜ
እየተባለ፤ ከመንዝ በሚመጣው ጥሬ እቃ አማካኝነት
እየተፈተለ በጥራት እንደሚሰራም አክለው
አስረዱኝ።

No comments:
Post a Comment