- መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ
ፖለቲከኞች የመንግስት አሊያም የፓርቲያቸው ሃሳብ እንጂ የግሌ የሚሉት ሃሳብ ስለሌላቸው ፌስቡክ ላይ የግል ሃሳቤ እያሉ የሚጭኑት ነገር ማቆም አለባቸው ሲሉ መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ ተናገሩ።
ፖለቲከኞች ፌስቡክ ላይ የግል ሃሳቤ እያሉ የሚጭኑት ሃሳባቸውን እንዳይኖራቸው እመክራለሁ ያሉት መጋቤ ሃዲስ የፖለቲካ አመራሮች እና የመንግስት ሹመኞች የግል ሃሳቤ ነው እያሉ ፌስቡክ ላይ የሚጽፉት ሃሳብ ህዝብን ለስህተት ይዳርጋል ብለዋል።
ፖለቲከኞች እና አመራሮች የወከላቸውን ፓርቲና መንግስት ሃሳብ እንጂ የግል ሃሳባቸውን በአደባባይ ማራመድ የለባቸውም።
ለአብነት አንድ የከተማ መስተዳደር የግሌ የሚለው ሃሳብ ሳይሆን የወከለው መንግስትን ሃሳብ ስለሆነ የግል ሃሳቤ ነው እያለ ፌስቡክ ላይ መጻፍ አይኖርበትም ሲሉ ያስረዳሉ።
የግል ሃሳብ አለኝ የሚል የፖለቲካ አመራር ካለ ሃሳቡን ለባለቤቱ ወይም ለልጆቹ ይንገራቸው ያሉት መጋቤ ሃዲስ እሸቱ ፤ በግል ሃሳብ ሰበብ የፖለቲካ አስተሳሰብ መጫን ስሀተት መሆኑን ተናግረዋል።
የግል ሃሳብ ካላቸውም ስራቸውን ወይም ፖለቲካ አባልነታቸውን ሲለቁ ማስተላለፍ አለባቸው የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ።
ካለበለዚያ ግን ፌስቡክ ላይ እየወጡ የግል ሃሳቤ እያሉ ህዝብን ማደናገራቸው ትርጉም የለውም፤ ለችግርም እየዳረገን ነው ሲሉ ተችተዋል።
አሁን ላይ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለሚታየው ልዩነትን የሚያሰፋ እና ግጭትን የሚቀሰቅስ
አካሄድ ከአጠቃቀም ችግር የመጣ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ሲሉም መልዕክት አዘል መረጃቸውን አጋርተዋል።
No comments:
Post a Comment