Saturday, December 9, 2017

Traditional Medicine In Ethiopia

Plants have been used as a source of medicine in Ethiopia from time immemorial to treat different ailments. This is often linked to ethnic and cultural diversity coupled with an array of unique flora and fauna that are employed as the prime-tools in the fight against numerous health problems. Even with the advent of modern medicine, this indigenous health care delivery system is the major source of care for an estimated 80% of the population. More than 95% of traditional medical preparations are of plant origin The Ethiopian flora is estimated to contain between 6500 and 7000 species of higher plants of which about 12% are endemic. The Directorate of Traditional and Modern Medicine (TMMRD) within EPHI conducting operational and basic research on the quality, efficacy and safety of traditional and modern medicine including the factors affecting the rational utilization and factors determine drug resist stance for the major health problems of the country.

Friday, December 8, 2017

የኤሌክትሪክ ፍጆታ ስሌት ልዩነት አለውን?

አቶ መንግስቱ አለሙ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በመኖሪያ ግቢያቸው ውስጥ አንድ አነስተኛ የፍራፍሬ መሸጫ ሱቅ እና አምስት መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ። የፍራፍሬ መሸጫ ሱቋን ገንብተው ካከራዩ አስር ወራት የተቆጠረ ቢሆንም ከሶስት ወራት ወዲህ ግን የኤሌክትሪክ ወጪያቸው እያየለ መምጣቱን ይናገራሉ። በተለይም ከአራት እና አምስት ወራት በፊት ይከፍሉ የነበረው 500 ብር ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ በተከታታይ ለሶስት ወራት ከእጥፍ ላይ 1500 ብር የሚጠጋ ገንዘብ አስወጥቷቸዋል። ለንግድ ቤቱ እና ለመኖሪያ ቤቶቹ የሚጠቀሙበት አንድ ቆጣሪ ቢሆንም የክፍያ ጭማሪውን ምክንያቱን ለማወቅ ይጥራሉ። በተከራዮች ከፍተኛ ፍጆታ የተከሰተ መሆኑን ለማጣራትም ሌት ተከን ቢታትሩም ምንም አይነት የአጠቃቀም ለውጥ በተከራዮቻቸው ላይ ሊያገኙ አልቻሉም።
ጉዳዩን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲዘዋወሩ ግን በግቢያቸው ውስጥ አንድ የንግድ ሱቅ በመኖሩ ምክንያት የኤሌክትሪክ ፍጆታ አቆጣጠሩ ከመደበኛ መኖሪያ ቤት ወደ ንግድ ቤት ታሪፍ መቀየሩ ይነገራቸዋል። ከሶስት ወራት በፊት ጀምሮ በቆጣሪ አነባበብ ላይ የተደረገው የአሰራር ለውጥ በእያንዳዱ የንግድ ቤት ያለው ግለሰብ ላይ የሚደረግ አሰራር መሆኑም ይነገራቸዋል። አቆጣጠሩ የተቀየረውም ቆጣሪ አንባቢዎች ባደረሱት መረጃ መሰረት መሆኑን እና ቀደም ብሎ ንግድ ሱቁ እንደተከፈተ ቢታወቅ ደግሞ የታሪፍ ቅያሪው ከአስር ወራት በፊት መቀየር እንደነበረነት ይነገራቸዋል።
ነገር ግን አቶ መንግስቱ ለአንድ ንግድ ቤት ተብሎ ቀሪዎቹ አምስት መኖሪያ ቤቶች በታሪፍ አሰራሩ ወደ ንግድ ቤት የተጠቃለሉበት ሁኔታ ግርታን ፈጥሮባቸዋል። እንደ እርሳቸው ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው የተለያዩ የንግድ ቤት የያዙ መኖሪያ ቤት ባለቤቶችን አነጋግረው ንግድ ቤት ላይ የቆጣሪ አነባበቡ የተለየ ስለሚሆን ከመኖሪያ ቤት ተመሳሳይነት ላለው የኤሌክትሪክ ፍጆታ በመጠን ከፍ ያለ ክፍያ መፈጸም የተለመደ መሆኑ ይነገራቸዋል።
ወይዘሮ እስከዳር አሊ ደግሞ አንድ መኖሪያ ቤት ያላቸው ቢሆንም በግቢያቸው ውስጥ ሁለት ንግድ ቤቶች አከራይተዋል። ንግድ ቤቶቹን ያከራዩት ከሁለት አመታት በፊት ቢሆንም የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን የሚከፍሉት በካርድ በሚሰራ የቆጣሪ መሳሪያ በመሆኑ ተከራዮቻቸው ወጪውን ይሸፍናሉ። በመሆኑም በተከራዮች ለሚሞላው የኤሌክትሪክ ክፍያ መጠን መጨመርና መቀነስ አሳስቧቸው አያውቅም። ነገር ግን ተከራዮቻቸው የፍጆታ ክፍያ መጨመር ላይ ቅሬታ አንስተው ስለማያውቁ በእርሳቸው ስም በተመዘገበው ቆጣሪ ምክንያት አድርገው በኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ቀርበው ጥያቄ አቅርበው አያውቁም።
የአቶ መንግስቱን ቅሬታ ሲሰሙ ግን 'አዲስ አሰራር ተዘርግቶ ይሆን' የሚል ሃሳብ ገብቷቸዋል። ተከራዮችም ይህን አይነት ያልተጣራ ወሬ ጆሯቸው ከደረሰ በኋላ ወጪውን ለማካካስ በሚል የሽያጭ እቃዎቻቸው ላይ ጭማሪ ስለማድረጋቸው ማጣራት እስካልተደረገ ድረስ ማንም እርግጠኛ መሆን ይከብደዋል።
የአሰራር ሁኔታውን ለማጣራት ወደ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ገብረእግዚያብሄር ታፈረ ደወልን። እርሳቸው እንደሚናገሩት፤ በአገሪቷ ውስጥ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ጭማሪ የለም። የሚቀየር የክፍያ አገልግሎት አሰራር ቢኖር እንኳን በመንግስት ደረጃ ፍቃድ ተደርጎበትና ለህብረተሰቡ በይፋ ተገልጾ እንጂ በድብብቆሽ የሚከናወን ጉዳይ አይኖርም። በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ ዝቅተኛ በሚባል ዋጋ እየቀረበ ይገኛል። ደንበኞቹ የሚያነሱት ጉዳይ ከአጠቃቀም ለውጥ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ እና ከቆጣሪ ብልሽት ጋር ተያይዞ የተከሰተ ስለመሆኑ በቅድሚያ ማጣራት ያስፈልጋል። ነገር ግን በመኖሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ የንግድ ቤት ያለው ሰው በጋራ ለሚጠቀምበት ቆጣሪ እዲከፍል የሚጠየቀው የአገልግሎት ክፍያ ለመኖሪያ ቤት ከሚጠየቀው ጋር ሲነጻጸር ልዩነት አለው።
ለቤት አገልግሎት የሚጠቀሙት ላይ እስከ 50 ኪሎ ዋት ኤሌክትሪክ ፍጆታ ድረስ ሲገለገሉ በኪሎ ዋት 0 ነጥብ 273 ሳንቲም እንደሚጠየቅ ይጠቁማሉ። ከ50 ኪሎ ዋት በላይ ሲጨምር ግን የክፍያ ስሌቱ የመጨመር አዝማሚያ /progressive/ ባህሪ እንዳለው ያስረዳሉ። የንግድ ቤቶች ላይ ደግሞ እስከ 50 ኪሎ ዋት ኤሌክትሪክ ፍጆታ ድረስ ሲገለገሉ 0 ነጥብ 6088 ሳንቲም እንዲከፍሉ ይደረጋል። ፍጆታው በንግድ ቤቶች ላይ ከ50 ኪሎ ዋት ሲበልጥ ግን የክፍያ ስሌቱ አጨማመር አነስተኛ /semi progressive/ እየሆነ እንደሚሄድ ይገልፃሉ
እንደ አቶ ገብረእግዚአብሔር ማብራሪያ፤ የመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በሚገኝ የንግድ ቤት ምክንያት የኤሌክትሪክ ክፍያ ስሌቱ ጨምሯለ የሚል ቅሬታ ያላቸው ሰዎች ከዚህ ቀደም ሲሰራበት የቆየ ስሌት በመሆኑ ምንም የተፈጠረ አዲስ አሰራር አለመሆኑን ማወቅ ይገባቸዋል። ለቤት አገልገሎት ሲሰራበት የነበረው የግለሰቦች ቆጣሪ የንግድ ቤት በመክፈታቸው ምክንያት ወደ ንግድ እንዲዞር ይደረጋል። ነገር ግን ለንግድ ቤቱ እና ለመኖሪያ ቤታቸው ባስገጠሙት አንድ ቆጣሪ ምክንያት ሁሉም ክፍያ በንግድ ቤት የቆጣሪ ስሌት ተጠቃሎብኛል የሚል ቅሬታ ያላቸው ሰዎች በህጋዊ መንገድ የተለያየዩ ቆጣሪዎችን በማስገጠም መጠቀም ይኖርባቸዋል። ለንግድ ቤቱ እና ለመኖሪያ ቤታቸው የተለያየ ቆጣሪ ከፋፍለው የሚጠቀሙ ከሆነም የመኖሪያ ቤቶቹን ኤሌክትሪክ ክፍያ በአነስተኛ ታሪፍ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ ፍርድ


የኦሮሚያ ጸረ ሙስና ኮሽን በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው የነበሩት በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ የስድስ አመት ጸሁ እስራት ተፈረደባቸው።
በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንትና በዋለው ችሎት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ እና ቤተሰባቸውን ጨምሮ በ12 ሰዎች ላይ በተመሰረተው ክስ ላይ ብይን ሰጥቷል። አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ጀማነህ ላይ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት፤ ያልታወቀ ሃብትን እውነተኛ በማስመሰል መሞከር እና ሃሰተኛ የመንግስት ሰነዶችን ህጋዊ በማስመሰል ጥቅም ላይ ማዋል በሚሉ ሶስት ክሶች ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ አድርጓቸዋል። በተከሳሹ ላይም የስድስት አመት ጸኑ እስራት እና የ11 ሺ ብር ቅጣት አስተላልፏል። ለቅጣት ማቅለያነት ከተቀመጡ ምክንያቶች ውስጥ ተከሳሹ ከዚህ በፊት ከማንኛውም ወንጀል ነጻ እንደነበሩ እና በመንግስት ካፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያገለገሉ እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች እንዳለባቸው የህክምና ማስረጃ ማቅረባቸውን በፍርድ ወቅት ተገልጿል።
በፍርድ ብይኑ መሰረት፤ ከከባድ ሙስና ወንጀሉ ጋር በተያያዘ በአዲሰ አበባ ኮልፌ ክፍለ ከተማ የሚገኝ መኖሪያ ቤት እና መኪና እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ኮንዶሚኒየም ቤትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአዋሽ ባንክ የነበሩ የተከሳሽ ገንዘብ ወደ መንግስት ገቢ እንዲሆኑ ተወስኗል።
ፍርድ ቤቱ በአቶ ዘላለም የቀድሞ ባለቤትና በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ የቅጣት ማቅለያዎችን በመመልከት በነጻ አሰናብቷቸዋል። አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች አሁን ላይ የተፋቱ መሆኑን ጠቅሶ ሁለተኛ ተከሳሽ ልጆቻቸውን ለማሳደግ በእናትነታቸው ሃላፊነት እንዳለባቸው በመጠቆም በነጻ ሲለቀቁ እስከ ሁለት አመት ድረስ በማንኛውም ወንጀል ተሳታፊ ሆነው ከተገኙ ግን አምስት አመት የሚደርስ እስራት እንደሚጸናባቸው ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ተገልጿል። ከሶስተኛ እስከ አምስተኛ እንዲሁም ስምንተኛ እና ዘጠነኛ ተከሳሾን በተመለከተ እስከ አምስት አመት በሚደርስ የተለያየ የእስር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ከስልጣናቸው የተነሱት እና በስተኋላም በሙስና ወንጀል የታሰሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ 12 ግለሰቦች ላይ 14 ክሶችን መስርቶ ከአንድ አመት በላይ መረጃዎች ሲጣሩ ቆይተዋል።
የቀድሞው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ሰኔ 2 ቀን 2008 . አስቸኳይ ስብሰባ ባደረገው የጨፌ ኦሮሚያ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ከተደረገ በኋላ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ የሚታወስ ነው። የክልሉ መንግስትና ድርጅት አመራር በነበሩበት ወቅት የመንግስት እና የህዝብ ንብረቶችን በስማቸው በማዞር፣ በህግ ወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ መያዝ እና ከገቢ በላይ ሀብት ማፍራት የመሳሰሉትን ከክሶቹ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

ሁለት ጊዜ የደረቀው ሃይቅ - ሐሮማያ


ሐይቆች በተለያየ ምክንያት ይደርቃሉ። በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የሐሮማያ ሐይቅ ደግሞ ከሌሎች ውሃ አካላት በተለየ ሁናቴ ሁለት ጊዜ ደርቋል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? ሐይቁን መልሶ ለማግኘት ምን ያስፈልጋል


በሐሮማያ ዪኒቨርሲቲ የአግሮኖሚ መምህር ዶክተር የሆኑት አብዱለጢፍ አህመድ ፤ ሐሮማያ ሃይቅ ሰባት ኪሎሜትር የሚሸፍን ርዝመት እና 14 ሜትር ጥልቀት የነበረው ሃይቅ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ሜዳ ሆኖ ውሃው ሊደርቅ የቻለው በአንድ ጊዜ የመጣ ክስተት አለመሆኑን ይናገራሉ። ከጊዜ ወደ ጊዜ ምህረት የለሽ እና ቁጥር የሌለው የውሃ ብዝበዛ ሲካሄድበት ቆይቶ ከአምስት አመታት በፊት ሃይቁ መድረቁን ይገልጻሉ። በአካባቢው ያሉ አርሶ አደሮች በርካታ ውሃ ከሃይቁ እየተጠቀሙ ውሃው ሲቀንስ እና ሃይቁ በደለል ሲሞላ የእርሻ ቦታቸውን ወደ ሃይቁ እያስጠጉ መሄዳቸውንም ያስረዳሉ። በመቀጠልም የሃይቁን ድንበር ጥሰው ደለሉ ላይ ምርት በመጀመራቸው ውሃ እንዳይተኛ አይነተኛ ምክንያት መሆኑን ይጠቁማሉ።
እንደ መምህር አብለጢፍ ገለጻ፤ በቀጣይ ህብረተሰቡን በማስተባበር እና ስለ ውሃ አጠቃቀም ያላቸውን እውቀት በመጨመር የሚገኘውን ውሃ በቁጠባ እንዲጠቀሙ ማድረግ ይገባል። አርሶአደሮቹም ለእርሻ ስራቸው የጠብታ መስኖ እንዲጠቀሙ ጥብቅ እገዛ ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ አምራቾቹ በእያንዳንዳቸው እርሻ ውስጥ የሚቆፍሩትን የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ በማስቀረት በአንድ ጉድጓድ ለጋራ እንዲጠቀሙ በማድረግ የከርሰምድር ውሃውን ብክነት መቀነስ ይገባል። ይህም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጣው ጎርፍ አሰባስቦ ሃይቁ ቦታ ላይ እንዲቆይ ለማድረግና ተከማችቶ የቆየ የመሬት ውስጥ ውሃ ወደ ላይኛው የመሬት አካል እንዲወጣ ለማድረግ ያግዛል። ይህ ስራ በቀጣዮቹ አመታት በቁጥጥር ከተሰራ ሃይቁ መልሶ የማይመጣበት ምክንያት የለም። የሃይቁን መልሶ መሙላት የሚወስደውን ጊዜ ለመገመት ግን የዝናብ ሁኔታው ወሳኝነት አለው። ድርቅ ተደጋግሞ የሚከሰት ከሆነ የሃይቁ መፈጠር ሊራዘም ይችላል።
የሐሮማያ ተፋሰስ ልማት መልሶ የማልማት ቴክኒክ አስተባባሪ አቶ ተፈሪ ታደሰ እንደሚናገሩት፤ ለሐረማያ ሃይቁ መጥፋት በመንስኤ የሆነው ዋነኛ ምክንያቱ የአካባቢው መሬት መራቆት ነው። በተጨማሪም የመሬት አጠቃቀም ለውጥ ለውሃው መመናን አስተዋጽኦ አድርጓል። ለማሽላ፣ ለጥራጥሬ እህሎች እና ለፍራፍሬ የሚውል የነበረ የአካባቢው መሬት ለጫት ምርት እየዋለ ይገኛል። የምርት አይነቱ በአንደ ጊዜ በመቀየሩም ምክንያት የአፈር እጥበቱ በከፈተኛ ሁኔታ ጨምሯል። በአካባቢው የሚሸረሸረው አፈር ደግሞ በቀጥታ ወደ ሃይቁ በመግባት ከተቀመጠ በኋላ የሃይቁን ውሃ ቦታ ይዟል። በመሆኑም በአሁኑ ወቅተ በቦታው ላይ ደለል እንጂ የውሃ አካል አይገኝም። ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው እየተስፋፋ የመጣው የጫት ተክል ለማደግ በርካታ ውሃ የሚያስፈልገው በመሆኑ የሃይቁን ውሃ በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውል በር ከፍቷል። ይህም የሃይቁን ውሃ በማመናመን እንዲደርቅ ምክንያት ሆኗል። 
 
ከሶስት አመታት በፊት የደረቀው የሃሮማያ ሐይቅ መልሶ ውሃ እንዲይዝ ለማድረግ ፕሮጀክት ተነድፎ ነበር። በሃይቁ አካባቢ የሚገኘው የላይኛው የተፋሰስ ክፍል ላይ የአፈር እና ውሃ እቀባ ስራ ዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በዚህ ውስጥ አካባቢውን መልሶ የማልማት እና የውሃ ሃብት አጠቃቀም ላይ ውጤታማ ስራዎች በተወሰነ ደረጃ ማከናወን ተችሏል። የመጀመሪያው ሃይቅ በተፈጥሮ የነበረና እና ጥልቀት ያለው ሲሆን ከደረቀ በኋላ መልሶ ለማልማት በተደረገው ጥረት አነስተኛ ውሃ በክረምት ወቅት እንዲይዝ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ያለው የውሃ አጠቃቀም የተዛባ በመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲደርቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። መልሶ ውሃ እንዲይዝ ለሚደረገው ጠረትም ውሃውን ከአቅሙ በላይ የመጠቀም ልምድ ሊስተካከል ይገባል። በመሆኑም ዋነኛው መፍትሄ የአካባቢውን የጫት ምርት በሌሎች ተችሎች በመቀየር የተመጣጠነ የውሃ አጠቃቀም ስርዓት እንዲስፍን ማድረግ ይገባል። በዚህም ከስድስት መቶ ሄክታር በላይ የሆነውን የሃይቁን ይዞታ መልሶ በማልማት ውሃ እንዲዝ ማድረግ ይቻላል። በአግባቡ ከተሰራም በአምስት እስከ አስር አመታት ባሉት ጊዜ ውስጥ ሃይቁን መልሶ ማግኘት የሚቻልበት እድል ሰፊ ነው። በአካባቢው የሚገኘውን ጥንቄ ሃይቅን እንዲሁም ሃረጂቶ የተባሉ አነስተኛ ሃይቆች ተፈጥረዋል።
«ማንኛውም ተክል ውሃ ይፈልጋል ጫት ስለተተከለ ብቻ ከፍተኛ ውሃ ከሃይቁ ላይ ተወስዷል ብሎ መደምደም አይቻልም» የሚሉት ደግሞ በእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ታደሰ ናቸው። ጫት ከፍተኛ ውሃ ስለሚወስድ ለሃይቁ መድረቅ አስተዋጽኦ አለው ለማለት ጥናት እደሚያስፈልግ ይገልጻሉ። ነገር ግን የሃይቁ ውሃ የሚከማችበት ጉድጓዳማ ስፍራ በተለያዩ ደለሎች እየተሞላ ሲሄድ ውሃው የመያዝ አቅሙ እንደሚቀንስ ይገልጻሉ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከሐይቁ ዙሪያ የሚገኘው የላይኛው ተፋሰስ አካባቢ ለአፈር መከላት የተጋለጠ በመሆኑ እደተከሰተ ያስረዳሉ። በመሆኑም የተፋሰሱን የእጽዋት ሽፋኑን በማሳደግ እና በመንከባከብ በጎርፍ ወቅት አፈር ተሸርሽሮ ወደ ሃይቁ እዳይገባ መጣር ዋነኛ ተግባር መሆን እንደሚገባው ይጠቁማሉ።
እንደ አቶ ተፈራ ገለጻ፤ የአካባቢው ህብረተሰብ የአፈር መሸርሸርን የሚከላከሉ የግብርና ዘዴዎችን እና ቴክኖሊጂዎችን እዲጠቀም ማበረታታት አስፈላጊ ነው። ይህ ከተከናወነ ሃይቁ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጎድጓዳማው አካባቢ በአፈር እየተሞላ ወደ ዝርግ መሬት የሚቀየርበትን ሂደት ያስቀረዋል። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ወደ ሜዳነት የተቀየረው እና ውሃ ለመያዝ አስቸጋሪ የሆነው ደለላላ ቦታ ለማስተካከል በተለያዩ አማራጮች ከሃይቁ ቦታ ላይ ደለሉ ቦታ ዲለቅ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህም በዝናብ እና በጎርፍ የሚገኘውን ውሃ እዲጠራቀም ቦታ ይከፍታል።ሁለት ጊዜ የደረቀ ሐይቅ

Tuesday, November 14, 2017

እንቦጭ እና አባይ ሳይገናኙ...

የአባይ ተፋሰስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ የወንድወሰን መንግስቱ የአንቦጭ አረም የአባይ ግድብ ላይ ከደረሰ አገዳው የከፋ እንደሚሆን ያስጠነቅቃሉ፤ በፍጥነት የመራባት ተፈጥሯዊ ባህሪ ያለው እንቦጭ አረም የህዳሴ ግድብ ላይ ሊራባ የሚችልበት እድል አለ ይላሉ። ጣና ሐይቅ እና አባይ ወንዝ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ በቀጣይ ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረለት ወደ ህዳሴው ግድብ የማይደርስበት ምክንያት አይኖርም። በተለይም የአረሙ በስፋት ግድቡ ላይ ከተራባ ውሃውን ከመሻማት በተጨማሪ ወደ ሃይል ማመንጫ ተርባይኖች በመግባት የኃይል መቆራረጥ እክል የመፍጠር አቅም አለው። በመሆኑም ለመጤ አረም መስፋፋና ለስነምህዳሩ መጎዳት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የሚከሰቱ የተከላ መሬቶችን እና ትላልቅ ደለሎችን በአባይ ወንዝ ተፋሰስ ላይ ከወዲሁ እንዲያገግሙ ማድረግ ይገባል።

 

አሁን ላይ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በእጅ የሚከናወን እንቦጭ አረም የማጥፋት ተግባር ለአረሙ መራባት እድል እንደሚሰጥ ነው፤ አረም ነቀላው በልማዳዊ መንገድ መከናወኑ ደግሞ ስሮቹና ቅጠሎቹ በቀላሉ በእጅ ተበጥሰው ውሃ ውስጥ እንዲንሳፈፉ ያደርጋል። አረሙ በባህርይው በስሩ፣ በቅጠሉ፣ እና በግንዱ እንዲሁም አበባ ሲያብብ ደግሞ
በፍሬው የሚራባ በመሆኑ በሚነቀልበት ወቅት በቀላሉ ከሐይቁ ወደ ወንዙ ተፋሰስ ክፍል እንዲጓጓዝ እድል ሊፈጠር ይችላል።

በመሆኑም አረሙ ከሐይቁ ግድቡ ለመድረስ ከ800 በላይ ኪሎመትሮች የሚፈጅበት ቢሆንም በውሃ ላይ አካሉ የሚጣል ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግድቡ ክልል የመድረስ እድል አለው። በኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቡ አካባቢ አነስተኛ ደለል የሚያገኝ ከሆነ በቀላሉ ሊራባ ይችላል። በመሆኑም ቅድመ ጥንቃቄው ስራ በተፋሰሱ አካባቢ እና በግድቡ ላይ ማጠንከር ይገባል። በተለይ በየትኛውም የተፋሰሱ አካባቢ አነስተኛ መጠን ያለው አረም በሚታይበት ወቅት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ እግር በእግር እየተከታተሉ ተቀናጅቶ ማጥፋት ተገቢ ነው። ለዚህም በቀጥታ ከሚመለከታቸው አካላት በተጨማሪ ህብረተሰቡ ዋነኛውን ድርሻ ሊይዝ ይገባል።

በቀጣይም እንቦጭን የስርጭት አድማሱን እንዳታስፋፋ የአባይ ወንዝ መፍሰሻ አቅጣጫን ተከትሎ ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል። ክትትሉን በማጠናከርም የትኛው ቦታ ላይ እየተራባ እንደሚገኝ በመለየት የመራባት ሂደቱን መቀነስ ይቻላል። ስራው በሰዎች እጅ ብቻ መከናወኑም ስርጭቱን ሊያባብሰው ስለሚችል የማጥፋት ስራው በዕውቀትና በቴክኖሎጂ ሊደገፍ ይገባል። በህብረተሰብ ንቅናቄ ብቻ ችግሩን ለመቅረፍ የማይቻል በመሆኑ ስሩ በአግባቡ እንዲነቀልና ከተነቀለም በኋላ አረሙ በአግባቡ የሚወድምበት መንገድ መመቻቸት አለበት። ህብተሰቡ መንግስም ሆነ በውጭ የሚገኙ ሰዎች አረሙን ለማጥፋት እያደረጉት ያለው ጥረት አበረታች ነው። የአማራ ክልል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ማሽን መረጣና ግዢ እያከናወነ በመሆኑ ማሽኖቹ ሲገቡ የችግሩ ጉዳት ለመቀነስ እንደሚረዳ ይጠበቃል።

የደጃች ኩምሳ ሞረዳ ቤተመንግስት

 

ነቀምቴ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ትገኛለች። እንደ አካባቢው አባቶች የስሟ ትርጓሜ «የታጨች» እንደማለት ነው። በከተማዋ ከሚገኙ መስህቦች ውስጥ ደግሞ ባለ ግርማ ሞገሱ እና ሁለት ነጥብ አምስት ሄክታር ላይ ያረፈው የንጉስ ደጃዝማች ኩምሳ ሞረዳ ቤተመንግስት ዋነኛው ነው። ንጉሱ የነቀምቴ ከተማ መስራች እንደሆኑ የሚታመን ሲሆን ከ1881ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1916 ዓ.ም. ድረስ የቀድሞ ወለጋ ጠቅላይ ግዛትን ያስተዳድሩ የነበሩ ንጉሥ ናቸው። ንጉሱ ቤተመንግስታቸውንም ያስገነቡት በ1981 ዓ.ም ነበር።
    የኩምሳ ሞረዳ ቤተመንግስት የኦሮሞ አምስት ገዳዎችን ለመወከል ታስቦ አምስት በሮች አሉት።  ከአምስቱ በሮች በየትኛው መግባት ይፈልጉ ይሆን?። 
    አንደኛው በር የንጉሱ እና ቤተሰባቸው መግቢያ ሲሆን ሁለተኛው በር ደግሞ የሰራተኞች መግቢያ ነበር። ሶስተኛው በር የቤት እንስሳት ከመስክ ወደ ግቢው ከግቢው ወደ ውጪ የሚመላለሱበት ሲሆን፤ አራተኛው በር ደግሞ ለግቢው ሰራተኞች መተላለፊያነት ብቻ ያገለግላል። አምስተኛው በር የእንግዶች በመሆኑ ለአገሩና ለቤተመንግስቱ አዲስ ከሆኑ በወቅቱ ሊጠቀሙ የሚችሉት በዚሁ መግቢያ እንደሆነ ያስቡ።
    ቤተ-መንግስቱን አስር ህንጻዎችን በሁለት ግቢዎች አጠቃሎ ይዟል። ግንባታው በኢትዮጵያውያን ሰራተኞችና በግሪካውያን አማካሪዎች የተከናወነ መሆኑን ታሪክ ያስረዳናል። ሁሉም ህንጻዎች በእንጨት፣ በኖራ ድንጋይና አፈር ብቻ የተዋቀሩ ናቸው።   
    በመጀመሪያ የንጉሱን ማረፊያ ክፍሎችን ቃኘት ቢያደርጉ በጣውላ ምንጣፍ የተሰሩ እና የእሳት ማሞቂያ የተሰራላቸው የእንግዳ ቤት፣ የመኝታ ክፍሎችና የምግብ ማቅረቢያ ክፍሎችን በአማረ የስነህንጻ ጥበብ ተውበው ይመለከታሉ። በመስኮቶቹ አሽንቀጥረው ቢመለከቱ ደግሞ ለንጉሱ ባህሉን የጠበቀ ምግብ የሚዘጋጅበት ማዕድ ቤትና የፈረንጅ እንግዶች እንዳይቸገሩ በማሰብ የተዘጋጀውን የውጭ አገር ምግብ ማሰናጃ ቤቶችን ያገኛሉ። ለንግድ እና ለተለያዩ ጉዳዮች የንጉሱን ደጅ የሚረግጡ የውጭ አገር ዜጎች በምግብ ችግር እንዳያጋጥማቸው ታስቦ የተገነባው ማዕድ ማዘጋጃ የአገሪቷን እንግዳ ተቀባይነት አጉልቶ የሚያሳይ ነው።     


    ከቤቶቹ ፊት ለፊቱ ደግሞ ሰፊ አዳራሽ ያገኛሉ። ወደ አዳራሹ ሲገቡ እነደ ኪስ የተሰሩ ሶስት በሮች ያላቸው ክፍሎች ይገኛሉ። አነስተኛ ክፍሎቹ ወደ ታዳሚው የሚዳረሱትን ምግብና መጠጥ  የሚቀመጥባቸው ቦታዎች ሲሆኑ፤ ለእያንዳንዱ ክፍል አንድ አንድ አሳላፊ ተመድቦላቸው ንጉሱ ግብር ያበሉበታል።
    ከዋናው ሳሎኑ አለፍ እንዳሉ ደግሞ ሌላ ውብ የንህጻ ዲዛይን ያረፈበት የፍርድ ችሎት ያገኛሉ። ችሎቱ በክብ ቅርጽ የተሰራ ህንጻ ነው። ባለ አንድ ወለል ከፍታም አለው። የላይኛው ወለል አንድ መግቢያ እና ሶስት ከበር የማይተናነሱ መስኮቶች ተዘጋጅታውለታል። ንጉስ ኩምሳ ብቻቸውን ተቀምጠው ፍርድ የሚሰጡበት ቦታ ነው። ከእርሳቸው በትክክል ወደታች ያለው ክፍል ደግሞ የተከሳሾች ዶሴ የሚደራጅበት ሚስጥራዊ ክፍል ሲሆን የሚከፈተውም ሆነ የሚዘጋው ንጉሱ ለዳኝነት በሚቀርቡባቸው ጊዜያት ብቻ ነበር።
    በምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው የፍርድ መስጫው የታችኛው ወለል ረቡዕ ዕለት ብቻ የፍትሐብሔር ተከሳሾች ቆመው ጉዳያቸውን ይከታተሉበታል። በተቃራኒው አቅጣጫ ደግሞ አርብ ዕለት የወንጀል ፍርድ የሚሰጣቸው ተከሳሾች በቦታው እንዲቀርቡ ይደረጋል። በወቅቱም ነጻ መውጣት እና አለመውጣታቸው እስኪታወቅ ድረስ ከሳሽ የተከሳሽን ቀለብ እና የተለያዩ ወጪዎች ችሎ የፍርድ ሂደቱን እንዲከታተሉ ይደረጋል። ፍርድ የተጣለባቸው ተከሳሾችን ለማጎር በግቢው ውስጥ የተገነባ ድቅድቅ ጨለማ የዋጠው እስር ቤት አለ። ጨለማ ቤቱ በጾታ የተከፋፈለ ነው። በአብዛኛው ጊዜ በጨለማ ክፍሉ የሚታሰሩ ሴቶች ንጉሱን በዘፈን እና በወሬ የሚያናድዱ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። 
    ሌላኛው ክፍል የስጦታ እቃዎች በክብር የሚቀመጡበት ቦታ ነው። የተለያዩ መጎናጸፊያዎች እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች ተሽቆጥቁጠው ይቀመጣሉ። በአሁኑ ወቅት ግን አብዛኛዎቹ የንጉሱ ንብረቶች የነቀምቴ ከተማ ሙዚየም ውስጥ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነው ይገኛሉ።
    በሌላ በኩል ንጉሱ ዘመናዊ ትምህርት ካላቸው ፍቅር የተነሳ ለልጆቻቸው መማሪያ ክፍሎችን አዘጋጅተዋል። የውጭ አገር ዜጎች ተቀጥረው የቤተሰብ አባላቱን ያስተምሩ ነበር። ንጉሱ የኋላ ኋላ ስማቸውን ወደ ደጃዝማች ገብረእግዚአብሔር ማስቀየራቸውን እና የክርስትና እምነት ተከታይ መሆናቸውን የታሪክ ድርሳናችው ያስረዳናል።
    በግቢው ውስጥ አስደናቂ ታሪክ የሚማሩባቸው ክፍሎች ደግሞ ንጉሱ ለአንደኛ እና ሁለተኛ ሚስቶቻቸው ያስገነቧቸው ክፍሎች ናቸው። የመጀመሪያዋ ሚስታቸው ክፍል ከአንድ ወጥ እንጨት የተሰራ በግምት ስምንት ሜትር የሚደርስ ቁመት ያለው ምሰሶ ከመሃል ቤቱ ላይ ተተክሏል። የሁለተኛዋ ሚስታቸው ቤት ግን ምሰሶ የሚባል ነገር የለውም። ወንድ ልጅ ለአንድ ሴት ብቻ ባል መሆን እንደሚችልና ከአንድ በላይ ለሆነ ቤተሰብ ምሰሶ መሆን እንደማይችል ለማሳየት ታስቦ የተደረገ መሆኑን ታሪክ አዋቂዎች ያስረዳሉ።     ምሰሶውም የኦሮሞን ገዳዎች በዕድሜ በየስምንት አመት እንደሚለያዩ ለትውልጾ ቀርጾ ለማስተላለፍ ስምንት ጠርዞችን እንዲይዝ ተደርጎ ተቀርጿል። ይህን ቤተመንግስት ከጅማው አባጅፋር ጋር የሚያመሳስለው ቅርጽ አለው። ቤተመንግስቱን በመጎብኘት ታሪክዎን የበለጠ ይወቁ!!!

Saturday, October 28, 2017

Eliminate Lead Content Paint For Health

    

A research on the lead content of solvent-based or oil paints for home and construction use in Ethiopia is released by the PAN-Ethiopia organization. The research shows that more than 75 percent of the analyzed paint brands sold have one or more paint that contained dangerously high total lead content greater than 10,000 parts per million(ppm).

     The third study on lead content in Ethiopian household decorative paints since 2012. Two orange paints contained 100,000 ppm lead or 10 percent of the paint’s content, more than 1,100 times the allowed threshold limit of 0.009 percent (90 ppm) established standard in many countries for lead in paint. And Ethiopia is in the process of law for lead content standard and expected to be ratified in 2018.

      The exposure to lead can have a wide range of health effects on a child’s development and behavior. many researchesshow that humans with high lead levels in their bodies may also have problems with learning and reading, delayed growth and hearing loss.

       Children who have reached on such kind of paints they touch into their mouths becoming highly vulnerable to the health risks. Use of lead in paint in hospitals,Schools and toys will damage heath of childrens.

       In the reasearch total of 36 cans of solvent-based paint intended for home use representing 11 brands and produced by different manufacturers from various stores in Ethiopia. Samples from these paints were analyzed by an accredited laboratory in the United States of America for total lead content.

And in result a majority (75 percent) of the solvent-based paints contained lead concentrations above 90 ppm. 

       Moreover, 42 percent of paints contained dangerously high lead concentrations above 10,000 ppm.The highest lead concentration detected was 130,000 ppm in orange color paints sold for home and construction use. Specially Yellow and orange paints were the most hazardous with 82 percent of yellow paints and 71 percent of orange paints containing lead concentrations greater than 10,000 ppm. 

      It is also still problem in some developing countries. And reserches call the need for immediate action to eliminate lead paint in Ethiopia and other countries with lead content materials.

Thursday, July 20, 2017

Bt Technology


The Economic Impacts of Introducing Bt Technology in Smallholder Cotton Production Systems of West Africa: A Case Study from Mali



Africa has been slow to respond to biotechnology even as its pest management grows increasingly obsolete and insects remain a major adversary of its farming. Opponents of biotechnology cite concerns over the scientific boundaries and potential North-South domination that transgenic crops could bring. An economic model was developed to predict the economic impacts to consumers and producers from the introduction of BT crops in the smallholder cotton farms of Mali. Since farmers rotate cotton and maize in three-year rotations, the analysis considered the introduction of both Bt cotton and Bt maize. Results from an economic model indicate that the potential economic impacts to West African consumers and producers would be significant, potentially reaching $89 million in an average year. For Bt cotton, the benefits would primarily accrue to producers. At a technology premium of $60 per hectare, where seed company revenue is maximized, Malian producer would capture 74% of the benefits and the seed company would capture the other 26%. The model found that the adoption of Bt maize was weaker than Bt cotton. If Malian maize producers were charged the same technology premium as South African producers, the model found that adoption would be less than 10%. The introduction of Bt maize in the region is likely to require complementary changes in maize markets and technology in order to boost profitability.

Saturday, June 10, 2017

3rd African cup of nation hosted by Ethiopia & Ethiopia won the tournament የ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኢትዮጵያ

መቅደላ አምባ የታሪክ ማህደር


               መቅደላ አምባ





«መቅደላ አፋፉ ላይ ጩ ከት በረከተ የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ» የተባለላት መቅደላ አምባ ከአካባቢው ተራሮች በላይ እራሷን ጎፍራ ተቀምጣለች። የመቅደላ አምባ ዙሪያውን የሚገኙ ስፍራዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መልከአምድር የያዘ በመሆኑ ጦርነት ለመምራት መቺ እንደሆነ መገመት ይቻላል። የጻውሎስ ኞኞ አፄ ቴዎድሮስ መጽሃፍ እንደሚያትተው ከቦታው ጥንታዊ የብራና መጽሃፍት፣ የወርቅና ብር ዋንጫዎች፣ አክሊሎችና ሌሎች የአፄ ተዎድሮስ እና ንጉስ ሚካኤል ቅርሶች ከመቅደላው ጦርነትና ከአፄ ቴዎደሮስ እረፍት በኋላ በናፒዬር የተመራው የእንግሊዝ ጦር በግመል አስጭኖ ወደ አገሩ ወስዷቸዋል። በአሁኑ ጊዜም በእንግሊዝ አገር የተለያዩ መዘክሮች ውስጥ ተቀምጠው ከሚገኙ ቅርሶች ውጪ መድፎች እና የቤተመንግስቱ ፍርስራሶች በቦታው ይገኛሉ።


ታሪካዊው የመቅደላ አምባ ተራራማው በሆነው የአማራ ክልል ተንታ ወረዳ ውስጥ ይገኛል። ቦታው ለመድረስም ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ አቅጣጫ 157ኪሎ ሜትር ርቀት መጓዝ ይጠይቃል። በቦታው እንግሊዞችን የተዋጉባቸው መድፎች መካከለል አንዱ በቆርቆሮ በተሸፈነ አጥር ተከልሎ ይገኛል። አጥሩ ዙሪያውን ሐረግ የወረሰው ሲሆን ጽዳት እንደሚያስፈልገው ያየው ሁሉ ይመሰክራል። አምባው ላይ ሲወጡ የአፄ ቴዎደሮስ እራሳቸውን ያጠፉበት ቦታ ተከለሎ ያገኙታል። በ2000 .ም የተገነባው መቃብራቸውም በአካባቢው ታሪክን ያወሳል። የንጉሱ እቃ ግምጃ ቤትና እንግሊዞች በርካታ ብራና መጻህፍትን የዘረፉበት የመቅደላ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያንም ፍርስራሹ ብቻ በቦታው ይገኛል። በአካባቢው እንደ አስጎብኚም እንደ ጥበቃም ሆነው የታዩት የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው።

Friday, May 5, 2017

ከድጡ ወደ ማጡ የሆነው የትምህርት ጥራት

ከድጡ ወደ ማጡ የሆነው የትምህርት ጥራት 

በኢትዮጵያ በግሉም ሆነ በመንግስት የትምህርት ተቋማት የተማረ የሰው ኃይል ለማፍራት ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ይሁንና የትምህርት ጥራ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ባለሙያዎች ይገለፃሉ። ሰሞኑንም በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት በተካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ጉባኤ ላባለሙያዎች በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳብ አቅርበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ ሙህዬ፣ የትምህርት ጥራት በሚጠበቀው ደረጃ አለመሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች እየተገኙ መሆኑን ይጠቁማሉ። ለዚህም ማሳያው በ2008.ም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከሶስት ነጥብ ሁለት በላይ አምጥተው የተመረቁ ተማሪዎች ላይ ፈተና መሰጠቱን ይጠቁማሉ። ለፈተና ከተቀመጡ ስድስት ሺ ተመራቂዎች መካከል 50 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ማምጣት የቻሉት ግን 24 በመቶ ብቻ ናቸው። የተሻለ ነጥብ ያላቸው ተመራቂዎች አነስተኛ ውጤት ካሳዩ ቀሪዎቹ በዩኒቨርሲቲ ውጤታማነታቸው ደካማ የነበሩት ተማሪዎች በባሰ መልኩ አነስተኛ ውጤት እንደሚኖራቸው መገመት እንደሚቻል ያስረዳሉ።
እነደ ዶከተር ተሰፋዬ ገለጻ፤ የተሰጠው ፈተና በገለልተኛ አካላት የወጣ ቢሆንም አንዳንድ ነባር ዩኒቨርሲቲዎች አነስተኛ ተመራቂዎቻቸው ብቻ ማለፍ ችለዋል። ዪኒቨርሲቲዎቹ ለፈተናው ያቀረቡት ተማሪዎች ቁጥር የተለያየ ቢሆንም ፈተናውን ካለፉ ተመራቂዎች መካከል በመቶኛ ሲሰላ ከተቋቋሙ ጥቂት ጊዜ ያስቆጠሩ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከነባር ዩኒቨርሲቲዎች በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ታውቋል። ይህም አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች በአግባቡ ከሰሩ ጥራት ያለው ተማሪ ማፍራት እንደሚችሉ ያሳየ አጋጣሚ ነበር። ይሁንና እንደ አጠቃላይ ፈተናውን ማለፍ የቻሉት ቁጥራቸው አነስተኛ መሆኑ ሲታይ የአገሪቷነ የጥምህርት ጥራት አደጋ ላይ መውደቁን የሚያሳይ ሆኗል። መንግስት ለ2009 .ም ለዩኒቨርሲቲዎች ከ36 ቢሊዮን ብር መድቧል። የተለያዩ መመሪያዎችን በማውጣት እና ተከታታይ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን መገንዘብ ይቻላል።
በመሆኑም በቀጣይ ጊዜያት የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ቁርጠኝነት ያስፈልጋል የሚሉት ዳይሬክተሩ፤ በተለይም ቀጥተኛ የስራ አጀንዳዎችን በመያዝ ወደትግበራ መግባት እነደሚያስፈልገ ይጠቁማሉ። እነደ እርሳቸው በዋናነትም የመምህራንን የአዕምሮ ዝግጁነት ማዳበር ያስፈልጋል። መምህራኑ በዕውቀት እና በምግባር ከተማሪው ከፍ ብለው በመገኘት አርአያ ሆነው መቅረበ አለባቸው። በዚህም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ መምህራን ለተማሪዎቻቸው የሞራል ውድቀት የሚያስተላልፉ እንዳይሆኑ ጥረት ማድረግ ይገባል። የስራ ፍቅር ያለው መምህር በሌለበት ተቋም የሚማሩ ወጣቶች የትምህርት ፍቅር ሊያድርባቸው አይችልም። በመሆኑም በመጀመሪያ መምህሪ ለስራው ፍላጎት እና ፍቅር እንዲኖረው ማድረግ የእያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ አመራር ቀጣይ ስራ ይሆናል። በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የውስጥ ግንኙነት መጠናከር አለበት። በዚህም ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀምሮ እሰከ ትምህርት ክፍል ድረስ በመግባባት እና በጋራ የመስራት መንፈስ ሊዳብር ይገባል። በሌላ በኩል የሚኘውን ግብዓት እና የአካባቢውን ሃብት በማጣመር ተገቢው የሃብት አጠቃቀም መተግበር ጥራቱ የተጠበቀ ትምህርት ለመስጠት ዋነኛ አሰራር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ከስዊድኑ አፕሳላ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ በበኩላቸው፤ በቀድሞ ጊዜ ትምህርት ጥራት ቢኖረውም ተገቢነት ያለው ትምህርት እንዳልነበረ ያስታውሳሉ። በ1960ዎቹ ላይ በአገሪቷ የተመረቁ የኮሌጅ ተማሪዎች ስድስት ሺ ብቻ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት ተገቢው እና ከአገሪቷ ሁኔታ ጋር የሚያያዝ ትምህርት እየተሰጠ ሲሆን በሚሊዮኖች ተመራቂ ተማሪዎች እንደሚገኙ ይገልፃሉ። ነገር ግን ትምህርት በኢትዮጵያ በብዛት ላይ እንጂ በጥራት ላይ ያልተመሰረተ ሆኗል ባይ ናቸው። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት በእንግሊዘኛ ቢሆንም በአብዛኛው የመግባቢያ ቋንቋው አማርኛ መሆኑን ማጥናታቸውን ያስረዳሉ።
«አማርኛ በትምህርት ተቋማት በጓዳ በር ገብቶ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማድረግም በትክክለኛው መንገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስተማሪያ ቋንቋ ተደርጎ ቢወሰድ ለትምህርት ጥራት መሻሻል አስተዋጽኦው ከፍተኛ ይሆናል»ይላሉ። 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርትና ጥናት ምርምር ተቋም የትምህርት ዘርፍ አጥኚ የሆኑት ዶክተር ዋና ሌቃ በበኩላቸው እንደሚገልፁት፤ የትምህርት ጥራት መጓደል የተከሰተው የተማሪው ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ነው። ለሶስት ሰው የተዘጋጀ ምግብ ለሃያ ሰው ቢቀርብ ጥራቱ የተጓደለ እንደሚሆን ሁሉ የትምህርት ዘርፉ ላይ ተማሪው ቁጥሩ ሲያድግ የማስተማሪያ ግብአቶች በዛው ልክ ማደግ ይኖርባቸዋል። በተመሳሳይ የአስተማሪዎች እና የመማሪያ ክፍሎች በመጣጣኝ ሁኔታ መቅረብ ይኖርበታል። ተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን በየጊዜው በመስራት እና ብቁ መምህራንን በብዛት በማፍራት ጥራቱን ማስተካከል ይቻላል። በሌላ በኩል የተማሪውን ፍላጎት እና አስተዳደግ ከግምት ውስጥ ባስገገባ መልኩ ትምህርቱን በማስቀጠል የተማሪውን የመቀበል ችሎታ ማሳደግ ይቻላል። በዚህም ጥራቱን የተሻሻለ ትምህርት ለማቅረብ ይቻላል።

ጠንካራ ሰራተኛ ማህበራት አሉን?


ጠንካራ ሰራተኛ ማህበራት አሉን?


በርካታ ተቋማት የሰራተኛ ማህበር የላቸውም። ያላቸውም ቢሆኑ ስለሚያከናውኑት ስራ አንዳንድ ሰራተኞች ጥያቄ ያነሳሉ።
በርካታ የግል ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ስለሚደርስባቸው ጫና እና የስራ ችግር የሚከላከልላቸው ማህበር የላቸውም። በተለይም በአንዳንድ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ላይ የሚሰሩ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል ለማን አቤት እንደሚባል እንኳን አያውቁም። መብታቸውን እስከምን ደረጃ እንደሚያስጠብቁ መረጃ የላቸውም። በቦታው ያለው የሰራተኛ ማህበርም ለሰራተኞች ተደራድሮ ጥቅም የማስከበር ጉዳይ ላይ ደካማ ነው።
በአገሪቷ ውስጥ የሚገኙ የሰራተኛ ማህበርም ሆነ የማህበራቱ ኮንፌዴሬሽን ጠንካራ ናቸው ለማለት አያስደፍርም። ለዚህም ማሳያው ለሰራተኛው ችግር ከመቅረፍ አኳያ አርአያ ሆነው መቅረብ የቻሉ የሰራተኛ ማህበራት ማየት አለመቻሉ ነው።
ስንቱ ነው የሰራተኞች ቀንን /ሚያዚያ 23/ ዝግ የስራ ቀን ስለሆነ ብቻ የሚወደው። አብዛኛው ሰው እረፍት ስለሚኖር እንጂ ስለቀኑ ደንታ የሚሰጠው የለም።
ጠንካራ ሰራተኛ ማህበራት ባለመኖራቸው በተለያዩ ተቋማት ሰራተኛው መብት ላይ ለሚፈጸሙ በደሎች የሚከራከር እና ለውጥ የሚያመጣ አካል አይኖርም። በመሆኑም መብት ለማስከበር ከበላይ ሃላፊዎች ጋር የሚኖረውን ውጥረት በመፍራት እና ጥያቄ ካነሳሁ ያለአግባብ ከስራ ልባረር እችላለሁ ብሎ የሚሰጋ ተቀጣሪ በዝቷል። አንድ ሰራተኛ በግሉ ከአመራሮች ጋር የመብት ጥያቄ አንስቶ ቢከራከረ አመታት ሊወስድበት ይችላል። የቤተሰብ አስተዳዳሪ የሆነ ሰራተኛ ደግሞ ሶስት እና አራት አመታት ከስራ ውጭ ሆኖ የመከራከር ኢኮኖሚያዊ አቅም ስለማይኖረው መብቱን አጥቶ እንዲሰራ ይገደዳል። እንደዚህ አይነት ችግር ላለመግባት ደግሞ አብዛኛው ሰራተኞች ከማኔጅመንት አካላት ጋር እውነተኛ ያልሆነ ግንኙነት በመፍጠር እና እያጎበደዱ መሰራትን ምርጫቸው ያደርጋሉ። ይህም መንፈሱ የተሰበረ ትውልድ እንዲፈጠር እያደረገ ይገኛል።
አንዳንምድ አሰሪዎችም ጠንካራ ተከራካሪ እና ስለመብት ጠያቂ አካል ያለመኖሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰራተኛው ላይ እንደፈለጉ ሲፈነጩ ይታያል። በተለይም የእራሳቸው እስር ቤት ያላቸው እና ሰራተኛን በእርግጫ እና በኩርኩመ የሚያቀዱ እንዳሉ መታዘብ ይቻላል።ይህ ጉዳይ በተለይ በውጭ አገራት ባለሃብቶች በሚተዳደሩ የጨርቃጨርቅ እና ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎች ላይ በብዛት የሚታይ ችግር ነው። ይህም በአብዛኛው ጊዜ ሰራተኛውን ተጎጂ ሲያደርገው ይስተዋላል። በመሆኑም በአግባቡ የሰራተኛውን መብት የሚያስከብር ማህበር ስለማቋቋም ሊታሰብ ይገባል። ከአሰሪዎች ጋር ስለደምዎዝዎ፣ የሥራ ሰዓት እና ሌሎች ማናቸውም የሥራ ቅጥር ግዴታዎችና ደንቦችን በተመለከተ በማህበር ተደራጅቶ የመደራደር አሰራር አልተለመደም። ጥያቄ ያለው ሰራተኛ ጉዳዩነ በግሉ ይዞ ያስፈጽማል።
የሰራተኛ ማህበራትን ጥቅም የሚረዳ ሰራተኛ ባለመኖሩ በተቋሙ ውስጥ ማህበሩን አደራጅቶ ለመሳተፍ ፍላጎት የሚያሳይ ሰራተኛ እምብዛም ነው። ሰራተኛ ማህበር ቢቋቋም ግን ጥቅሙ ለሰራተኛው ብቻ ሳይሆን ለአሰሪዎችም ጭምር ነው። ምክንያቱም በተደራጀ ሁኔታ በማህበር የሚነሱ የሰራተኛውን ጥያቄዎች ማስተናገድ እና መፍታት ከተቻለ የባንኩን እድገት ለማፋጠን ይረዳል። በግለሰብ ደረጃ የሚመጡ ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች ማስተናገድ ግን ከጊዜም ሆነ ከወጪ አኳያ ተመራጭ አይደለም። በመሆኑም ሰራተኞች ብቻ ሳይሆን አሰሪዎችም የሰራተኛ ማህበር ለማቋቋም ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል።

Featured post

ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል

                    የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደር...